Discover millions of ebooks, audiobooks, and so much more with a free trial

Only $11.99/month after trial. Cancel anytime.

ወደ ቅባቱ የሚያደርሱ እርምጃዎች
ወደ ቅባቱ የሚያደርሱ እርምጃዎች
ወደ ቅባቱ የሚያደርሱ እርምጃዎች
Ebook181 pages1 hour

ወደ ቅባቱ የሚያደርሱ እርምጃዎች

Rating: 4.5 out of 5 stars

4.5/5

()

Read preview

About this ebook

መቀባት ትፈልጋለህ? በዚህ ታሪካዊ መጽሐፍ ውስጥ፣ ዶ/ር ዳግ ሂዋርድ ሚልስ ቅባቱን ለመቀበል የሚያስችሉ በርካታ እርምጃዎችን ያካፍላሉ፡፡ ይህ መጽሐፍ በጣም በእርግጠኝነት ለአንተ እና ለአገልግሎትህ በረከት ይሆናል፡፡ ለመቀባት ልትወስድ የሚገባህን እርምጃዎች ድረስበት!

Languageአማርኛ
Release dateJul 27, 2016
ISBN9781613954454
ወደ ቅባቱ የሚያደርሱ እርምጃዎች
Author

Dag Heward-Mills

Bishop Dag Heward-Mills is a medical doctor by profession and the founder of the United Denominations Originating from the Lighthouse Group of Churches (UD-OLGC). The UD-OLGC comprises over three thousand churches pastored by seasoned ministers, groomed and trained in-house. Bishop Dag Heward-Mills oversees this charismatic group of denominations, which operates in over 90 different countries in Africa, Asia, Europe, the Caribbean, Australia, and North and South America. With a ministry spanning over thirty years, Dag Heward-Mills has authored several books with bestsellers including ‘The Art of Leadership’, ‘Loyalty and Disloyalty’, and ‘The Mega Church’. He is considered to be the largest publishing author in Africa, having had his books translated into over 52 languages with more than 40 million copies in print.

Related to ወደ ቅባቱ የሚያደርሱ እርምጃዎች

Related ebooks

Reviews for ወደ ቅባቱ የሚያደርሱ እርምጃዎች

Rating: 4.5 out of 5 stars
4.5/5

2 ratings1 review

What did you think?

Tap to rate

Review must be at least 10 words

  • Rating: 5 out of 5 stars
    5/5
    Can I download the soft copy of this book please? Regards, GBU!!!

Book preview

ወደ ቅባቱ የሚያደርሱ እርምጃዎች - Dag Heward-Mills

ወደ ቅባቱ የሚያደርሱ እርምጃዎች

ዳግ ሂዋርድ ሚልስ

ካልተገለፀ በቀር፣ በዚህ መጽሐፍ ውስጥ ያሉ ጥቅሶች ሁሉ የተወሰዱት በ1954 ዓ.ም. ከታተመው የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ ነው።

አርትዖት፡- ሬቨረንድ አማኑኤል ቶማስ

Find out more about Dag Heward-Mills

Healing Jesus Crusade

Write to: evangelist@daghewardmills.org

Website: www. daghewardmills.org

Facebook: Dag Heward-Mills

Twitter: @EvangelistDag

ስለ ዳግ ሂዋርድ ሚልስ የበለጠ መረጃ ከፈለጉ

በዚህ ኢሜይል ይጻፉ፡- evangelist@daghewardmills.org

ዌብሳይታቸውን ይጎብኙ፣ www.daghewardmills.org.

በፌስቡክ፣ Facebook: Dag Heward-Mills

በትዊተር፣ Twitter: @EvangelistDag

ISBN: 978-1-61395-445-4

ላይትሃውስ ቻፕል ኢንተርናሽናል

መ.ሳ ቁጥር 15134

አዲስ አበባ

ኢትዮጵያ

ይህንን መጽሐፍ በሙሉም ሆነ በከፊል ያላሳታሚው ፈቃድ ማባዛት የተከለከለ ነው፡፡

ማውጫ

መቀባትህ ግድ የሚሆንበት ሰባት ምክንያቶች 1

ቅባት በአገልግሎትህ ላይ ያለው አሥራ አምስት ኃይለኛ ተጽዕኖዎች 7

ወደ ቅባቱ አንድ እርምጃ 16

በዮርዳኖስ ውስጥ፣ ወደ ቅባት የተደረጉ ሰባት እርምጃዎች 21

በምድረ በዳ ውስጥ፣ ወደ ቅባት የተደረጉ ሰባት እርምጃዎች 29

በቆርኔሌዎስ ቤት፣ ወደ ቅባት የተደረጉ ሰባት እርምጃዎች 41

ቅባቱ መሥራት እስኪጀምር ድረስ እንዴት መጽናት ይገባል 51

በሰገነቱ ላይ፣ ወደ ቅባት የተደረጉ ሰባት እርምጃዎች 60

በገዛ ወገኖችህ መካከል ወደ ቅባቱ የሚደረጉ ሰባት እርምጃዎች 68

በቅዱስ ተራራ ላይ ወደ ቅባት የተደረጉ እርምጃዎች 77

ስሜቱ ሊሰማህ ወደሚችል ቅባት የሚያመሩ ሰባት እርምጃዎች 86

የነቢያትና የጻድቃን ቅባት 94

በተቀባው ሰው ላይ የተጣሉ ገደቦች 102

ንጉሣዊ ቅባት 115

የነቢዩ ኢሳይያስ ቅባት 122

በጌታ የተቀባ ማለት ምን ማለት ነው? 129

ከቅባት የሚያርቁ እርምጃዎች 135

ወደ ቅባቱ የሚወስድ መንገድ 144

እጥፍ ድርሻ ለማግኘት የሚደረግ ውጊያ 152

የተቀባ ሰው ሕይወት 166

በተቀባሁ ጊዜ መቀባቴን እንዴት አውቃለሁ? 172

አገልግሎትህን ፈጽም 177

ምዕራፍ 1

መቀባትህ ግድ የሚሆንበት ሰባት ምክንያቶች

ልትቀባ ያስፈልጋል ምክንያቱም ማንም ሰው በመንፈስ ቅዱስ ካልሆነ በስተቀር በተፈጥሮው ችሎታው ወይም ደግሞ በሰብአዊ ጉልበት አገልግሎቱን ከግብ ሊያደርስ አይችልምና ነው፡፡

መልሶም፡- ለዘሩበቤል የተባለው የእግዚአብሔር ቃል ይህ ነው፡- በመንፈሴ እንጂ በኃይልና በብርታት አይደለም፣ ይላል የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር፡፡

ዘካርያስ 4፡6

እውነተኛ አገልግሎት ስኬታማ ሊሆን የሚችለው በመንፈስ ቅዱስ ኃይል ብቻ ነው፡፡ ሀሰተኛ አገልግሎት ደግሞ የሚሠራው በትምህርት አስተማሪ ደረጃ፣ በዩኒቨርስቲ አስተማሪ ደረጃ ወይም በስሜት ቀስቃሽ ተናጋሪነት በኩል ነው። እንግዲህ ለመቀባትና ወደ እውነተኛ አገልግሎት ለመግባት ወስን፡፡

አገልግሎትህን በቅባቱ ኃይል አሳድገው፡፡ ያለቅባቱ ምንም ነገር ልታደርግ አትችልም፡፡

መቀባት አለብህ ምክንያቱም ጌታ ኢየሱስ አገልግሎቱን ከመጀመሩ በፊት እስኪቀባ ድርስ ቆይቷል፡፡

ሕዝቡም ሁሉ ከተጠመቁ በኋላ ኢየሱስ ደግሞ ተጠመቀ፡፡ ሲጸልይም ሰማይ ተከፈተ፣ መንፈስ ቅዱስም በአካል መልክ እንደ እርግብ በእርሱ ላይ ወረደ፤ የምወድህ ልጄ አንተ ነህ፣ በአንተ ደስ ይለኛል የሚል ድምፅም ከሰማይ መጣ።

ኢየሱስም ሊያስተምር ሲጀምር እድሜው ሰላሳ ዓመት ያህል ሆኖት ነበር . . .

ሉቃስ 3÷21-23

ይህ ክስተት የኢየሱስን አገልግሎት ጅማሬ ያመላከተ ነበር፡፡ እስከ ሰላሳ ዓመቱ ድረስ ስለ እርሱ አንሰማም፡፡ ከዚህ በኋላ ማለትም መንፈስ ቅዱስ (ቅባቱ) ከወረደበት በኋላ ጌታ ኢየሱስ መስበክ፣ ማስተማርና መፈወስ ጀመረ፡፡

መቀባት አለብህ ምክንያቱም ሐዋርያትም እንኳን አገልግሎት ከመጀመራቸው በፊት መንፈስ ቅዱስን (ቅባቱን) እንዲጠብቁ ታዘው ነበር፡፡

ከእነርሱም ጋር አብሮ ሳለ ከኢየሩሳሌም እንዳይወጡ አዘዛቸው፣ ነገር ግን ከእኔ የሰማችሁትን አብ የሰጠውን ተስፋ ቃል ጠብቁ፤

ሐዋርያት 1፡4

ያለ መንፈስ ቅዱስ ምን ዓይነት አገልግሎት ይኖረኛል ብለህ ታስባለህ? ከኢየሱስ ጋር ይጓዙ የነበሩ ታላላቅ ሐዋሪያት እንኳ በአገልግሎት የተሳካላቸው ይሆኑ ዘንድ የመንፈስ ቅዱስ ቅባትን መቀበል አስፈልጓቸው ነበር፡፡

መቀባት አለብህ ምክንያቱም እንደ ኤልሳዕ ያሉ ታላላቅ ነቢያት የሚፈልጉትን ነገር የመጠየቅ ዕድል በተሰጣቸው ጊዜ ቅባቱን ለምነው ነበር፡፡

ኤልሳዕ አገልግሎት ስኬታማ የሚሆነው በቅባት ብቻ እንደ ሆነ ተረድቶ ነበር፡፡ ኤልያስ ምን እንደሚፈልግ በጠየቀው ጊዜ ቅባቱ ሁለት እጥፍ እንዲሆንልኝ ፈልጋለሁ አለ፡፡

ከተሻገሩም በኋላ ኤልያስ ከአንተ ሳልወስድ አደርግልህ ዘንድ የምትሻውን ለምን አለው፤ አልሳዕም፡- መንፈስህ በእኔ ላይ ሁለት እጥፍ ይሆን ዘንድ እለምሃለሁ አለ፡፡

2ኛ ነገሥት 2፡9

ብዙ ነገሮች መጠየቅ ይችል ነበር፡፡ የኤልያስን መልካም ስም፣ ገንዘብ፣ የኤልያስን ንብረት፣ የኤልያስን መኪና እና ሚስትም ሊጠይቅ ይችል ነበር፡፡ ነገር ግን ኤልሳዕ ብዙ ዓመታት ከኤልያስ ጋር ከተጓዘ በኋላ የአገልግሎት ምስጢር የቱጋ እንዳለ አወቀ፡፡ ዋናው ነገር ቅባት መሆኑን ተረዳ ስለዚህም እጥፍ ቅባት ለመነ። ታላላቅ ነቢያቶች ስለ ቅባት ሲለምኑ አንተ ታዲያ ለምን ስለ ሌላ ነገር ትለምናለህ?

መቀባት አለብህ ምክንያቱም ንጉሥ ሳኦል እስኪቀባ ድረስ ሌላ ሰው ወደ መሆን አልተለወጠም ነበር፡፡

ሳኦል በተቀባ ጊዜ ከተራ ሰውነት ወደ ንጉሥነት ተለውጦ ነበር። በተመሳሳይ መንገድ አንተም ስትቀባ በእግዚአብሔር መንግሥት ውስጥ ባለ ሥልጣን (ንጉሥ) ትሆናለህ፡፡

ሰዎችን ለመግዛትና ለመቆጣጠር የተለያዩ ብልሃቶችን ልትጠቀም ትችል ይሆናል፣ ግን ያለ ቅባት ባለ ሥልጣን ልትሆን አትችልም፡፡

የመንፈስ ቅዱስ ቅባት ሌላ ሰው ወደ መሆን ይለውጥሃል፡፡

ሳሙኤልም የዘይቱን ብርሌ ወስዶ በራሱ ላይ አፈሰሰው፣ ሳመውም፣ እንዲህም አለው፡- በርስቱ ላይ አለቃ ትሆን ዘንድ እግዚአብሔር ቀብቶሃል፤

1ኛ ሳሙኤል 10፡1

የእግዚአብሔር መንፈስ በኃይል የወርድብሃል፣ ከእነርሱም ጋር ትንቢት ትናገራለህ፣ እንደ ሌላ ሰውም ሆነህ ትለወጣለህ፡፡

1ኛ ሳሙኤል 10:6

መቀባት አለብህ ምክንያቱም የተቀባው ዘማሪና የቅዱሳት መጽሐፍት ፀሐፊው ንጉሥ ዳዊት የበረከቶቹ ሁሉ ምንጭ ቅዱሱ ቅባት እንደሆነ ገልጻDል፡፡

ዳዊት መላ የሕይወቱን ገጽታ ከቅባቱ ጋር አቆራኝቷል፡፡ በጣም መንፈሳዊ የሆኑ ሰዎች በሕይወታቸው የተለያዩ አቅጣጫዎች ላይ የመንፈስ ቅዱስ ቅባት ያመጣውን ተጽእኖ ያስተውላሉ፡፡

ንጉሥ ዳዊት በሰማኒያ ዘጠነኛው መዝሙር ውስጥ በጣም ውብ ከሆኑ ዝማሬዎቹ አንዱን ሲዘምር እናገኛለን፡፡ በዝማሬው ውስጥ በሕይወቱ ላይ የቅባቱን ኃይለኛ ተጽዕኖ ይገልጣል፡፡ እርደታ፣ ብርታት፣ ፅናት፣ ክብር እና ሥልጣን ከቅባት እንደሚገኙ ተናግሮአል፡፡ የተቀባው ዘማሪ እነዚህን ነገሮች ሁሉ ከቅባቱ ካገኘ አንተ ታዲያ እንዴት እነዚህን ሁሉ ያለ ቅባት ለማግኘት ትጠብቃለህ? ንጉሥ ዳዊት፣ ቅዱስ መንፈስህን ከእኔ አትውሰድ፡፡፣ ብሎ ቢጮህ ትፈርድበታለህ?

ከፊትህ አትጣለኝ፣ ቅዱስ መንፈስህንም ከኔ ላይ አትውሰድብኝ

መዝሙር 51÷11

ለእርሱ መንፈስ ቅዱስ (ቅባት) እጅግ በጣም ውድ ነገር ነበር፡፡

ቅባት ወሳኝ ነው ምክንያቱም ያለ እርሱ ሙሴ በአገልግሎቱ ለመቀጠል እምቢ አለ፡፡

ሙሴ እንኳን ያለ ቅባት አንድ እርምጃ ያልተራመደ ከሆነ፣ አንተ ታዲያ እንዴት ያለ እርሱ ኃላፊነት ለመቀበል ትደፍራለህ?

በዘጸአት መጽሐፍ እግዚአብሔር የእርሱን ኃይል እና ቅባት ከእርሱ የሚወስድ ከሆነ፣ ኃላፊነቱን ለመወጣት እንዴት እምቢ እንደሚል እናያለን፡፡

ሙሴ ስለ እግዚአብሔር መገኘት ሲናገር ስለ ቅባት እና ስለ እግዚአብሔር ኃይል እየተናገረ ነው፡፡

እርሱም፡- አንተ ከኛ ጋር ካልወጣህስ፣ ከዚህ አታውጣን፡፡ በምድርም ፊት ካለው ሕዝብ ሁሉ እኔና ሕዝብህ የተለየን እንሆን ዘንድ አንተ ከእኛ ጋር ካልወጣህስ፣ እኔና ሕዝብህ በአንተ ዘንድ ሞገስ ማግኘታችን በምን ይታወቃል? አለው፡፡

እግዚብሔርም ሙሴን፡- በፌቴ ሞስ ስላገኘህ በስምህም ስላወቅሁህ ይህን ያልከውን ነገር አደርጋለሁ አለ፡፡ እርሱም፡- እባክህ ክብርህን አሳየኝ አለው፡፡ እግዚአብሔርም፡- እኔ መልካምነቴን ሁሉ በፊትህ አሳልፋለሁ የእግዚአብሔርንም ስም በፊትህ አውጃለሁ ይቅርም የምለውን ይቅር እላለሁ፣ የምምረውንም እምራለሁ አለ፡፡

ዘጸአት 33፡15-19

ምዕራፍ 2

ቅባት በአገልግሎትህ ላይ ያለው አሥራ አምስት ኃይለኛ ተጽዕኖዎች

በዚያን ጊዜ ለልጆችህ በራእይ ተናገረህ እንዲህም አልህ፡- ረድኤቴን በኃያል ላይ አኖርሁ፤ ከሕዝቤ የተመረጠውን ከፍ ከፍ አደርግሁ፡፡

ባሪያዬን ዳዊትን አገኘሁት፣ ቅዱስ ዘይትም ቀባሁት፡፡ እጄም ትረዳዋለች፣ ክንዴም ታጸናዋለች፡፡

መዝሙር 89÷19-21

ንጉሥ ዳዊት እጅግ በጣም ከተወደዱ ከብሉይ ኪዳን መዝሙሮች በአንዱ ውስጥ ከቅባቱ የተነሳ ስለተቀበለው በረከት ይዘምራል፡፡ ከልምድ እንዳየሁት በረከታቸውን ከእውነተኛ የበረከታቸው ምንጭ ጋር ለማገናኘት የቻሉ በጣም ጥቂት ሰዎች መሆናቸውን አይቻለሁ፡፡ ከወዴት እና እንዴት ያሉበት ቦታ እንደደረሱ እንዲሁም ያላቸውን ነገር እንዴት እንዳገኙ አያውቁም። ይህም ብዙውን ጊዜ መሠረቱ አመስጋኝ ካለመሆንና ዓመጸኛነት ነው። ስለ በረከት ሁሉ ምንጭ በጥልቀት ማሰብና እንዲሁም ማወቅ ትልቅ ብቃት እንደሆነ አስባለሁ፡፡ ዳዊት እንዴት አድርጎ የገጠሙት መልካም ነገሮች ምንጭ ቅባቱ እንደሆነ እንደሚገልጥ ማንበብ ድንቅ ነው፡፡ ዳዊት ቅባትን በጣም ያከብራል፡፡ አብዛኛውን ጊዜም ራሱን በጌታ የተቀባ ብሎ ይጠራል፡፡

እግዚአብሔር ዓይኖችህን ይከፈትና የቅባቱን ታላቅነት በሕይወትህና በአገልግሎትህ እንድታይ ይርዳህ!

ብዙ አገልጋዮች ቅባት ምን እንደሚሠራ ቢያዩ፣ ከማንኛውም ነገር በበለጠ ሊመኙትና ሊፈልጉት እንደሚችሉ አምናለሁ፡፡ ቅባቱ በዳዊት ሕይወት ላይ እንደዚህ

Enjoying the preview?
Page 1 of 1