Discover millions of ebooks, audiobooks, and so much more with a free trial

Only $11.99/month after trial. Cancel anytime.

ላይኮስ ተኢው ስው እር አንልግኤት
ላይኮስ ተኢው ስው እር አንልግኤት
ላይኮስ ተኢው ስው እር አንልግኤት
Ebook135 pages1 hour

ላይኮስ ተኢው ስው እር አንልግኤት

Rating: 0 out of 5 stars

()

Read preview

About this ebook

ላይኮስ የሚለው የግሪክ ትርጉሙ ክህሎት የሌለው ማለት ነው፡፡ታሪክ በተደጋጋሚ 'ልዩ ክህሎት' ባልተጎናጸፉ ሰዎች ታላላቅ ሁነቶች እንደተከወኑ ያስተምረናል በትርፍ ጊዜያቸው የሚገለግሊ ሰዎች በቤተክርስቲያን ውስጥ የማይሰሩ ከሆነ፣ ሸክምን በትርፍ ጊዜያቸው ለሚያገለግሉ ሰዎች ማካፈል እና ለምን የትርፍ ጊዜ አገልግሎትን ለመጠበቅ መዋጋት እንዳለብን በዚህ የዳግ ሂዋርድ ሚልስ ዓይነተኛ መጽሐፍ አማካኝነት ተማር፡፡

Languageአማርኛ
Release dateJul 28, 2016
ISBN9781613954386
ላይኮስ ተኢው ስው እር አንልግኤት
Author

Dag Heward-Mills

Bishop Dag Heward-Mills is a medical doctor by profession and the founder of the United Denominations Originating from the Lighthouse Group of Churches (UD-OLGC). The UD-OLGC comprises over three thousand churches pastored by seasoned ministers, groomed and trained in-house. Bishop Dag Heward-Mills oversees this charismatic group of denominations, which operates in over 90 different countries in Africa, Asia, Europe, the Caribbean, Australia, and North and South America. With a ministry spanning over thirty years, Dag Heward-Mills has authored several books with bestsellers including ‘The Art of Leadership’, ‘Loyalty and Disloyalty’, and ‘The Mega Church’. He is considered to be the largest publishing author in Africa, having had his books translated into over 52 languages with more than 40 million copies in print.

Related to ላይኮስ ተኢው ስው እር አንልግኤት

Related ebooks

Reviews for ላይኮስ ተኢው ስው እር አንልግኤት

Rating: 0 out of 5 stars
0 ratings

0 ratings0 reviews

What did you think?

Tap to rate

Review must be at least 10 words

    Book preview

    ላይኮስ ተኢው ስው እር አንልግኤት - Dag Heward-Mills

    ስለ ትርፍ ጊዜ አገልገሎት ማወቅ የሚገባህ ሰባት ነገሮች

    ካልተገለፀ በቀር፣ በዚህ መጽሐፍ ውስጥ ያሉ ጥቅሶች ሁሉ የተወሰዱት በ 1954 ዓ.ም. ከታተመው የአማርኛ መፅሐፍ ቅዱስ ነው፡፡

    Find out more about Dag Heward-Mills at:

    Healing Jesus Campaign

    Write to: evangelist@daghewardmills.org

    Website: www. daghewardmills.org

    Facebook: Dag Heward-Mills

    Twitter: @EvangelistDag

    Write to:

    Dag Heward-Mills

    P.o.Box 114

    Korle-Bu

    Accra

    Ghana

    ላይትሃውስ ቻፕል ኢንተርናሽናል

    ስልክ + 251912063821

    መ.ሳ ቁጥር 15134

    አዲስ አበባ

    ኢትዮጵያ

    ISBN: 9781613954386

    ይህን መጽሐፍ በሙሉም ሆነ በከፊል ያለ አሳታሚው ፈቃድ ማባዛት የተከለከተለ ነው፡፡

    Table of Contents

    ምዕራፍ 1. ሌይኮስ - 'ተራው ሰው'

    ምዕራፍ 2. የትርፍ ጊዜ እና የበጎ ፈቃድ አገልጋዮች ባይኖሩ ምን ይፈጠራል?

    ምዕራፍ 3. እግዚአብሔር በትርፍ ጊዜ ሰዎች የሚሰራበት ሰባት ምክንያቶች

    ምዕራፍ 4. ስለ ትርፍ ጊዜ አገልገሎት ማወቅ የሚገባህ ሰባት ነገሮች

    ምዕራፍ 5. ለምን የትርፍ ጊዜ መጋቢ መሆን እንደሚገባህ

    ምዕራፍ 6. የትርፍ ጊዜ አገልግሎትን በምን አይነት መልኩ እንዳገኘሁት

    ምዕራፍ 7. ሸክምን እንዴት ለትርፍ ጊዜ አገልጋዮች ማካፈል እንደሚቻል

    ምዕራፍ 8. ዓይነተኛ የትርፍ ጊዜ መጋቢ

    ምዕራፍ 9. ተገቢ የሆነ የትርፍ ጊዜ መጋቢ ባህሪ ምን ይመስላል?

    ምዕራፍ 10. ሁለት ሀሳብ የሆኑ የትርፍ ጊዜ መጋቢዎች

    ምዕራፍ 11. የትርፍ ጊዜ አገልግሎት የአገልግሎት ልኬት መሆኑን መረዳት

    ምዕራፍ 12. የትርፍ ጊዜ አገልግሎት የእገዛ አገልግሎት ዓይነት መሆን መረዳት

    ምዕራፍ 13. የትርፍ ጊዜ አገልግሎት ጉድለቶችን መረዳት

    ምዕራፍ 14. እግዚአብሔር የትርፍ አገልግሎት ለምን እንዲኖር እንደሚፈቅድ መረዳት

    ምዕራፍ 15. ለትርፍ ጊዜ መጋቢነት የሚረዱ አራቱ አስፈላጊ ክህሎቶች

    ምዕራፍ 16. የትርፍ ጊዜ መጋቢዎች ትግሎች

    ምዕራፍ 17. እራሳቸውን በፍቃዳቸው በሚሰጡ የአገልግሎት ተምሳሌት መሆን

    ምዕራፍ 18. ለምን የትርፍ ጊዜ አገልግሎትን ለመጠበቅ መዋጋት እንዳለብን

    ምዕራፍ 1.

    ሌይኮስ - 'ተራው ሰው'

    ተራ ሰው (ሌይ ማን) የሚለው ቃል 'ላይኮስ ከሚለው የግሪክ ስረወ ቃል የተገኘ ነው፡፡ ይህም ማለት 'ልዩ ክህሎት የሌለው ያልታደለ' ማለት    ነው፡፡ ታሪክ 'ልዩ ክህሎት' ባልተጎናጸፉ ሰዎች ታላላቅ ሁነቶች እንደተከወኑ ያስተምረናል፡፡ ተራ በሚባሉ ሰዎች አማካኝነት የታዩ ከፍተኛ ውጤቶች ላይ የወፍ በረር ቅኝት እንኳ ቢደረግ እነዚህን አይነት ሰዎች በአገልግሎት ውስጥ ለመጠቀም መነሳሳትን    ታገኛለህ፡፡ በተራ ሰዎች ብዙዎች ወደ ደህንነት መጥተዋል፤ በርካታ የቤት ህብረቶች ተመስርተዋል፤ አብያተ ክርስቲያናት አድገዋል፤ የእግዚአብሔርም ስራ ሰፍቷል፡፡

    የሚከተሉት ተራ ሰው (ሌይማን) ለሚለው ቃል የተሰጡ ቀራቢ ትርጉሞች ናቸው

    1.         ሌይ ማን (ተራ ሰው) የተለመደ አይነት ሰው ነው

    2.         ሌይ ማን (ተራ ሰው) መደዴ የሚባል አይነት ሰው ነው

    3.         ሌይ ማን (ተራ ሰው) ተደጋጋሚ አይነት ፊት ያለው ሰው ነው

    4.         ሌይ ማን (ተራ ሰው) ልማዳዊ አይነት ሰው ነው

    5.         ሌይ ማን (ተራ ሰው) መደበኛ አይነት ሰው ነው

    6.         ሌይ ማን (ተራ ሰው) ልዩነት የማይታይበት ሰው ነው

    7.         ሌይ ማን (ተራ ሰው) የአዘቦት ሰው ነው

    8.         ሌይ ማን (ተራ ሰው) 'ምንም አይልም የሚባል' ሰው ነው

    9.         ሌይ ማን (ተራ ሰው) 'ባለሙያ ያልሆነ ሰው ነው

    10.     ሌይ ማን (ተራ ሰው) ሊቅ ያልሆነ ሰው ነው

    11.     ሌይ ማን (ተራ ሰው) ያልተጠበበ ሰው የሚባል ነው

    12.     ሌይ ማን (ተራ ሰው) ልዩ ክህሎት የሌለው ሰው ነው

    13.     ሌይ ማን (ተራ ሰው) ያልሰለጠነ ሰው ነው

    14.     ሌይ ማን (ተራ ሰው) የምስክር ወረቀት የሌለው ሰው ነው

    ሌይ ማን (ተራ ሰው) የሙያ ፈቃድ ማረጋገጫ ወረቀት የሌለው ሰው ነው

    በቤተክርስቲያን ድባብ ውስጥ የተደረጉ ታላላቅ ክንውኖች

    1.             ተራ ሰዎች የታላቁ የቤተክርስቲያን ተሐድሶ አምዶች ናቸው

    ማርቲን ሉተር መጽሐፍ ቅዱስን ወደ ተራው ሰው ቋንቋ መተርጎሙ የዓለምን መልክ ለመቀየር አስችሎታል፡፡ በላቲን ቋንቋ የተጻፈውን የእግዚአብሔር ቃል በአፍ መፍቻ ቋንቋ ለህዝቡ እንዲደርስ አደረገ፡፡ እናም የመገለጥ እውቀት አንድ ጊዜ በተራ ሰዎች መዳፍ ስር ሲገባ አለምን መለወጥ ቻሉ፡፡ በዚህም ሰዎች ሁሉ ደህንነትን በእግዚአብሔር ጸጋ መውረስ እንደሚችሉ ሲገነዘቡ በብርታት እና በሐይል ከፍ ብለው በአሸናፊነት በመነሳት ተሐድሶ የምንለውን አስገኙ፡፡

    2.             ተራ ሰዎች ለታላቋ የሜቶዲስት ቤተክርስቲያን አምዶች ነበሩ

    በ20ኛው ክፍለ ዘመን አጋማሽ ሜቶዲዝም በዩናይትድ ስቴትስ አሜሪካ ውስጥ ትልቋ የፕሮቴስታንት ቤተእምነት ነበረች፡፡ ይህች ታላቅ ቤተክርስቲያን ታዲያ በብርታት መገስገስ የቻለችው በተራ ሰዎች ጫንቃ አማካኝነት ነበር፡፡ ጥንታዊው የሜቶዲስት ቤተክርስቲያን ልማድ 'ኡደት' በተባለ የሜቶዲስት ስብስብ ቤተክርስቲያናት ውስጥ የትርፍ ጊዜ ሰባኪን የአምልኮን አገልግሎት እንዲመራ ብሎም ቃሉን እንዲሰብክ መሾም ልማድ ነበር፡፡

    የትርፍ ጊዜ ሰባኪውም በእግሩ ወይም በፈረስ አማካኝነት የተሰጠው የስብከት ጣቢያ (ኡደት) በመጓዝ በተለመደው ስርዓትና ጊዜ ያከናውናል፡፡

    በዚህች ቤተ እምነት ከአገልጋዮችና መጋቢዎች መሾም በኋላም ይህ የትርፍ ጊዜ የስብከት አገልግሎት ልማድ 'የሜቶዲስት አገር በቀል ሰባኪያን' ተብለው የቀጠሉ ሲሆን በየአጥቢያ ቤተክርስቲያናቱ ይሾሙ ነበር፡፡ በምላሹም በየአቅራቢያው ባሉ ቤተክርስቲያናት ይጋበዙና ይሾሙ የነበር ሲሆን የአገልጋዩ ረዳት ወይም ደግሞ በተለየ አቅድ አገልጋዮች በሚቀሩበት ጊዜ አገልግሎቱን ባግባብ ይሸፍኑ ነበር፡፡

    3.             ተራ ሰዎች በዓለም ላይ በተናጠል ትልቅ ለሆነችው ቤተክርስቲያን አምድ ነበሩ፡፡

    የዮይዶ ፉል ጎስፕል ቤተክርስቲያን ከተመሰረተችበት መሰረታዊ መርሖች አንዱ በትርፍ ጊዜ አገልጋዮች አማካኝነት አገልግሎት መስጠት የሚል ነው፡፡

    የዮይዶ ፉል ጎስፕል ቤተክርስቲያን በዴቪድ ያንግ ቾ እና በአማቱ ቾይ ጃሺል አማካኝነት የተመሰረተ ሲሆን ሁለቱም ቀድሞ የአሴምብሊስ ኦፍ ጋድ መጋቢያን ነበሩ፡፡ የመጀመሪያውን የአምልኮ አገልግሎት ሜይ 15/1958 በቁጥር አራት ከሚሆኑ ልጃገረዶች ጋር በቾይ ጃ ሺል መኖሪያ ቤት አደረጉ፡፡ በ1977 የቤተክርስቲያናቱ አባላት ሐምሳ ሺህ ከደረሱ በኋላ በሁለት አመት ውስጥ እጥፍ ሆኑ፡፡ በኖቬምበር 30/1981 አባላቱ 200,000 የደረሱ ሲሆን በዚያኑ ጊዜ ሎሳንጀለስ ታይምስ የተባለው ጋዜጣ በዓለም ትልቁ አጥቢያ ቤተክርስቲያን በማለት አትቷል፡፡

    በ2007 የአባላቱ ቁጥር 830,000 የደረሰ ሲሆን የእሁዱ የአምልኮው መርሐ ግብር በ7 ፈረቃ ፣በ16 ቋንቋዎች እየተተረጎመ ይካሔዳል፡፡

    4.             ተራ ሰዎች በጋና እና ናይጄሪያ ከተነሱት ግዙፍ የቤተክርስቲያናት መረብ አምዶች ናቸው፡፡

    መቀመጫውን በናይጄሪያ ያደረገው የሪዲምድ ክርስቲያን ቸርች ኦፍ ጋድም ሆነ መናገሻውን ጋና ያደረገው ቸርች ኦፍ ፔንቴኮስት ሁለቱም ተራ ሰዎችን በአገልግሎት ውስጥ በሚገባ በማሰማራት ይታወቃሉ፡፡ እነዚህ ሁለቱም አግልግሎቶች ግዙፍ የሆነ የመያያዝ መረብ የፈጠሩ ሲሆን በመደበኛነት የትርፍ ጊዜ አገልግሎት ማለትም የወንጌል ስብከትም ሆነ የመጋቢነት አገልግሎት ይሰጣል፡፡

    የጴንጤቆስጤ ቤተክርስቲያን የተመሰረተችው ከእንግሊዝ ብራድፎርድ ከአፖስቶሊክ ቸርች ወደ ጎልድኮሰት (የአሁኗ ጋና) በተላከው አየርላንዳዊ ሚስዮናዊ ጄምስ ማኪዮን አማካኝነት ነው፡፡ ይህች ቤተክርስቲያን ከ 1.7 ሚሊዮን አባላት በላይ እስኪኖራት አድጋለች፡፡ የፔንቴኮስት ቤተክርስቲያን በአለም ላይ በ70 አገራት ውስጥ 13,000 አጥቢያ ቤተክርስቲያናት

    Enjoying the preview?
    Page 1 of 1