Discover millions of ebooks, audiobooks, and so much more with a free trial

Only $11.99/month after trial. Cancel anytime.

ሌሎች
ሌሎች
ሌሎች
Ebook97 pages36 minutes

ሌሎች

Rating: 0 out of 5 stars

()

Read preview

About this ebook

መጽሐፍ ቅዱስ በፊሊጵስዮስ ፪፡፬ ላይ “እያንዳንዱ ለራሱ የሚጠቅመውን አይመልከት፥ ለባልንጀራው ደግሞ እንጂ።” ይላል። በዚህ ይጊዜው መጽሐፍ ውስጥ ዳግ ሂዋርድ ሚልስ ከራስህ ማሰብ አልፈህ ስለሌሎች ማስብ እንድትጀምር ያበረታታሃል። ሌሎችንም ደግሞ ወደድ!ደግሞም ሌሎችን አስብ! ለሌሎቸም ደግሞ ተጠንቀቅላቸው!ደግሞም ለሌሎቸ መኖር ጀምር! ኢየሱስ መጥቶ የሞተበት ምክንያት ለሌሎች በማሰብ ነው። እኔ እንደ እርሱ መሆን እፈልጋለሁ። እንደ ኢየሱስ መሆን ትፈልጋለህ?

Languageአማርኛ
Release dateAug 14, 2018
ISBN9781641348027
ሌሎች
Author

Dag Heward-Mills

Bishop Dag Heward-Mills is a medical doctor by profession and the founder of the United Denominations Originating from the Lighthouse Group of Churches (UD-OLGC). The UD-OLGC comprises over three thousand churches pastored by seasoned ministers, groomed and trained in-house. Bishop Dag Heward-Mills oversees this charismatic group of denominations, which operates in over 90 different countries in Africa, Asia, Europe, the Caribbean, Australia, and North and South America. With a ministry spanning over thirty years, Dag Heward-Mills has authored several books with bestsellers including ‘The Art of Leadership’, ‘Loyalty and Disloyalty’, and ‘The Mega Church’. He is considered to be the largest publishing author in Africa, having had his books translated into over 52 languages with more than 40 million copies in print.

Related to ሌሎች

Related ebooks

Reviews for ሌሎች

Rating: 0 out of 5 stars
0 ratings

0 ratings0 reviews

What did you think?

Tap to rate

Review must be at least 10 words

    Book preview

    ሌሎች - Dag Heward-Mills

    እያንዳንዱ ለራሱ የሚጠቅመውን አይመልከት፥ ለባልንጀራው ደግሞ እንጂ። በክርስቶስ ኢየሱስ የነበረ ይህ አሳብ በእናንተ ዘንድ ደግሞ ይሁን። 

    ፊል. 2፡4-5

    ከብዙ ዓመታት በፊት ታላቅ የሆነ የእግዚአብሔር መንግስት አገልጋይ የድነት ሰራዊት የተባለውን አገልግሎት መሰረተ፡፡ በርካታ የሆኑ መሪዎችን እና ለእግዚአብሔር መንግስትም ብዙ ፍሬ ያፈራ ነበረ፡፡ አንድ ቀን ለቡድኑ መሪዎች አስፈላጊ የሆነ የቴሌግራም መልዕክት ላከላቸው፡፡ የቴሌግራሙም መልዕክት በሚነበብበት ጊዜ ሁሉም መሪዎች እንዲኖሩ አሳሰባቸው፡፡ መሪዎቹም ምን አይነት መልዕክት ሊሆን እንደሚችል በማሰብ በታላቅ ጉጉት ሆነው በቴሌግራሙ ዙሪያ ተሰበሰቡ፡፡ ሁሉም ከተዘጋጁ በኋላ የታሸገውን የቴሌግራም መልዕክት ከፍተው ማንበብ ጀመሩ፡፡ በመልዕክቱ እጅግ ደነገጡ! ደብዳቤው በረጅም ትዕዛዝ እና መመሪያ ፈንታ አንድ ቃል ብቻ የያዘ ነበር፡፡ 

    ቃሉ ምን ይመስላችኋል? ሌሎች የሚል ነው፡፡

    የተሰበሰቡት የድነት ሰራዊት መሪዎች በተቀመጡበት ተገረሙ፡፡ መልዕክቱ ማለትም ሌሎች ምን እንደሆነ በግርምት ያስቡ ነበር! ዊልያም ቡዝ በዚህ ባልተለመደ መልዕክት ውስጥ ሊያስተላልፍ የፈለገው ሃሳብ ምን ነበር? በዚያ በጸጥታ በተቀመጡበት በርግጠኝነት እያንዳንዳቸውን እግዚአብሔር ተናግሯቸዋል፡፡ ሌሎች የሚለው ቃል ለክርስቲያኖች ሁሉ የተሰጠ መልዕክት ነው፡፡

    ሌሎች የሚለው መልዕክት

    1. ሌሎች የሚለው መልዕክት፤ ሌሎች ይኖራሉ ማለት ነው፡፡

    2. ሌሎች የሚለው መልዕክት፤ አዕምሮዋችን በሌሎች ላይ መሆን አለበት ማለት ነው፡፡

    3. ሌሎች የሚለው መልዕክት፤ ህይወታችንን ለሌሎች ማፍሰስ አለብን ማለት ነው፡፡

    4. ሌሎች የሚለው መልዕክት፤ ለሌሎች መኖር ይገባናል ማለት ነው፡፡

    5. ሌሎች የሚለው መልዕክት፤ ሌሎችን ማገልገል አለብን ማለት ነው፡፡

    6. ሌሎች የሚለው መልዕክት፤ህይወታችንን ስለሌሎች ማኖር አለብን ማለት ነው፡፡

    7. ሌሎች የሚለው መልዕክት፤ እግዚአብሔር የሰጠንን በረከት ሁሉ ሌሎችን ለመንከባከብ ልናውለው ይገባል ማለት ነው፡፡

    ስለሌሎች ማስታወስ የሚገባህ አራት ነገሮች

    በአዕምሮህ ስለ ሌሎች ልታስብ የሚገባህ አራት ዋና ዋና ነገሮች አሉ፡፡ እነዚህን አራት ነገሮች ማስታወስ ከቻልህ ስለሌሎች ትክክለኛ አስተሳሰብ ይኖርሃል፡፡

    1. ሌሎች ክርስቶስ ያስፈልጋቸዋል!

    ሴቲቱ። ክርስቶስ የሚባል መሲሕ እንዲመጣ አውቃለሁ፤ እርሱ ሲመጣ ሁሉን ይነግረናል አለችው።ኢየሱስ፦ የምናገርሽ እኔ እርሱ ነኝ አላት።በዚያም ጊዜ ደቀ መዛሙርቱ መጡና ከሴት ጋር በመነጋገሩ ተደነቁ፤ ነገር ግን። ምን ትፈልጊያለሽ? ወይም። ስለ ምን ትናገራታለህ? ያለ ማንም አልነበረም።ሴቲቱም እንስራዋን ትታ ወደ ከተማ ሄደች ለሰዎችም። ያደረግሁትን ሁሉ የነገረኝን ሰው ኑና እዩ፤ እንጃ እርሱ ክርስቶስ ይሆንን? አለች። ከከተማ ወጥተው ወደ እርሱ ይመጡ ነበር። 

    ዮሐ. 4፡25-30

    ሁልጊዜ ማስታወስ የሚገባህ ነገር ክርስቶስ የሚያስፈልጋቸው በርካታ ሰዎች አሉ፡፡ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ሰዎች ስለ ኢየሱስ ምንም የሚያውቁት ነገር የለም ምክንያቱም ቤተክርስቲያን ስለ ሌሎች ማሰብ በመዘንጋቷ ነው፡፡ ብዙ ክርስቲያኖች የሌሎች ክርስቶስን አለማወቅ አያሳስባቸውም፡፡ ክርስቶስን እና በቤተክርስቲያናቸው ያለውን ድንቅ ህብረት እያጣጣሙ በደስታ ይኖራሉ፡፡ እባክችሁን ይህን ልብ በሉ፤ በርካታ የሆኑ ሰዎች ንጹህ የሆነውን ወንጌል ለመስማት በጉጉት እየተጠባበቁ ነው፡፡ አንድ የሆነ ሰው ቢመሰክርላቸው ልባቸውን ለጌታ መስጠት በቻሉ ነበር፡፡ በርግጥም ሌሎች ክርስቶስ ያስፈልጋቸዋል!

    ሳምራዊቷ ሴት ሌሎችን በማሰብ እና በማሰብ ፈጣን ነበረች፡፡ ኢየሱስን በማውቅ ከተባረከች በኋላ በከተማዋ ኢየሱስን ለማያውቁ ሰዎች ሁሉ ማካፈል ፈለገች፡፡ ሳምራዊቷ ሴት ሌሎችን ለሚያስቡ ሰዎች ታላቅ ምሳሌ ነች፡፡ አብዛኛው ሰው አንድ መልካም የሆነ ነገርን ለመቀበል ደስተኛ ነው፤ ሆኖም ግን ያለውን ነገር ሌላው እንዲኖረው ለማሰብ አልታደለም፡፡

    2. ሌሎች እረኛ ያስፈልጋቸዋል

    ከዚህም በረት ያልሆኑ ሌሎች በጎች አሉኝ፤ እነርሱን ደግሞ ላመጣ ይገባኛል ድምፄንም ይሰማሉ፥ አንድም መንጋ ይሆናሉ እረኛውም አንድ።

     ዮሐ. 10፡16

    ሌሎች በጎች አሉኝ! ይህ ማለት በሌላ ስፍራ እረኛ የሚጠብቁ በርካታ በጎች አሉ ማለት ነው፡፡ ኢየሱስ በመደበኛነት የእርሱን ጥበቃ፣ ፍቅር እና እንክብካቤ ለሚፈልጉ ሁሉ ንቁ ነበር፡፡ ኢየሱስ የበርካቶችን የመሰማራት እና መጋቢያዊ ትምህርት ለመስጠት በንቃት ይከታተላል፡፡ አንተስ የሌሎችን የእረኛ እና እረኛዊ እንክብካቤ ለመስጠት በተጠንቀቅ አለህን?

    ብዙ ክርስቲያኖች እረኛ እንደሚሹ ማስታወስ አስፈላጊ ነገር ነው፡፡ ድነት አንድ ነገር ነው፤ በሚገባ መመገብ እና የእረኝነት አገልግሎት ማግኘት ደግሞ ሌላ ነገር ነው፡፡

    Enjoying the preview?
    Page 1 of 1