Discover millions of ebooks, audiobooks, and so much more with a free trial

Only $11.99/month after trial. Cancel anytime.

የአገልግሎትህን እስከ መጨረሻው እንዴት ማድረስ ትችላለህ
የአገልግሎትህን እስከ መጨረሻው እንዴት ማድረስ ትችላለህ
የአገልግሎትህን እስከ መጨረሻው እንዴት ማድረስ ትችላለህ
Ebook85 pages1 hour

የአገልግሎትህን እስከ መጨረሻው እንዴት ማድረስ ትችላለህ

Rating: 0 out of 5 stars

()

Read preview

About this ebook

ማናችንም በምድር የተሰጠንን ስራ ሳንጨርሰ በሰማዩ ቤታችን መግባት አንፈልግም። አንዳችንም ስንኳ!እግዚአብሔር ለኛ የሰጠንን ስራ መጨረስ እንፈልጋለን። ይህ መጽሐፍ እንዴት ማጠናቀቅ እንደምትችል ይነግርሃል። ይህ መጽሐፍ በዚያ ቀን ምንም አልጎድለኝም እንዳትል በህይወትህ ውስጥ ለሚያጋጥሙህ መለኮታዊ ወቅቶች እንዴት መመለስ እንዳለብህ ያሳይሃል። ስራህን አጠናቅቀህ እግዚአብሔር “ አንተ በጎ ታማኝ ባሪያ” ለመባል ያብቃህ!

Languageአማርኛ
Release dateAug 17, 2018
ISBN9781641348034
የአገልግሎትህን እስከ መጨረሻው እንዴት ማድረስ ትችላለህ
Author

Dag Heward-Mills

Bishop Dag Heward-Mills is a medical doctor by profession and the founder of the United Denominations Originating from the Lighthouse Group of Churches (UD-OLGC). The UD-OLGC comprises over three thousand churches pastored by seasoned ministers, groomed and trained in-house. Bishop Dag Heward-Mills oversees this charismatic group of denominations, which operates in over 90 different countries in Africa, Asia, Europe, the Caribbean, Australia, and North and South America. With a ministry spanning over thirty years, Dag Heward-Mills has authored several books with bestsellers including ‘The Art of Leadership’, ‘Loyalty and Disloyalty’, and ‘The Mega Church’. He is considered to be the largest publishing author in Africa, having had his books translated into over 52 languages with more than 40 million copies in print.

Related to የአገልግሎትህን እስከ መጨረሻው እንዴት ማድረስ ትችላለህ

Related ebooks

Reviews for የአገልግሎትህን እስከ መጨረሻው እንዴት ማድረስ ትችላለህ

Rating: 0 out of 5 stars
0 ratings

0 ratings0 reviews

What did you think?

Tap to rate

Review must be at least 10 words

    Book preview

    የአገልግሎትህን እስከ መጨረሻው እንዴት ማድረስ ትችላለህ - Dag Heward-Mills

     -ምዕራፍ 1

    አገልግሎትህን እንድትፈጽም የሚያደርጉህ መለኮታዊ ግብዓቶች

    አንተ ግን ነገርን ሁሉ በልክ አድርግ፥ መከራን ተቀበል፥ የወንጌል ሰባኪነትን ሥራ አድርግ፥ አገልግሎትህን ፈጽም። 2ኛ ጢሞ 4፡5

    አገልግሎትህን በሚገባ መፈጸም ትችላለህ፡፡ የኢየሱስ ክርስቶስ አገልግሎት ልትሳተፍበት የተገባ እጅግ አስፈላጊ የሆነ እንቅስቃሴ ነው፡፡ ለሰው ልጅ ከተሰጡት እድሎች ውስጥ ለእግዚአብሔርን መስራት ትልቁና ዋንኛው ሲሆን ይህም "አገልግሎት˝ ይባላል፡፡ አገልግሎትህን መፈጸም ደግሞ እጅግ ወሳኝ ነገር ነው፡፡ ጌታ በምድር ላይ  ትፈጽመው ዘንድ  የሰጠህን የትኛውንም ስራ ማጠናቀቅ እጅግ ጠቃሚ ነው፡፡ አገልግሎትህን በሚገባ ሳትፈጽም መሞት አይገባህም፡፡

    አገልግሎትህን በሚገባ ሳትፈጽም ወደ ሰማይ መንግስት ብትሄድ ደስታህን ልታጣጥመው አትችልም፡፡

    ዝግጅት ሳታደርግና ሳታጠና ፈተና መፈተን ማለት ምን ማለት እንደሆን ታውቃለህ! ለስራ ሳትዘጋጅ እና ንቁ ሳትሆን አለቃህ ሲያገኝህ አስበው፡፡

    ለአክሪጳም። በጌታ የተቀበልኸውን አገልግሎት እንድትፈጽሙው ተጠንቀቅ በሉልኝ። ቆላስያስ 4፡17

    በርካታ ሰዎች አገልግሎታቸውን መፈጸም አይደለም ጥሪያቸው ምን እንደሆነ ጠንቅቀው እንደማያውቁ ይናገራሉ፡፡ አገልግሎታቸውን እንዴት መፈጸም እንዳለባቸው ማወቅ ታዲያ እንዴት ይገባቸው! ይህ መጽሐፍ አገልግሎትን እንዴት መፈጸም እንዳለብን ያወሳል፡፡ ይህንን መጽሐፍ እያነበብክ ከሆነ አገልግሎት አለህ ማለት ነው፡፡ ጳውሎስ ለአክሪጳ የሰጠውን ብርቱ ማስጠንቀቂያ ልብ በል አገልግሎትህን እንድትፈጽም፡፡˝ በሌላ አነጋገር፣ አገልግሎትህን ስለመፈጸምህ እና ስለማጠናቀቅህ እርግጠኛ ሁን ማለት ነው፡፡

    ብዙ ሰዎች፣ ˝እንዳንተ አይነት ስጦታ የለኝም መንፈሳዊ የአገልግሎት ቢሮም አልታደልሁም ˝ ሲሉ ይደመጣሉ፡፡ የሚታየው እውነታ ብዙዎቻችን ለአገልግሎት በተለየ ሁኔታ ስጦታ እንዳለን አይሰማንም፡፡ ትክክለኛው ነገር ግን ብዙዎቻችን ለአገልግሎት በእግዚአብሔር ብንለይም ምላሽ ግን አልሰጠንም፡፡ ብዙ ሰዎች ለአገልግሎት ፍቅር እንዳላቸው ቢያሳዩም ለጥሪው ግን ምላሽ አልሰጡም፡፡

    ለእግዚአብሔር ጥሪ ምላሽ ከመስጠትህ በፊት መልዓክ ሲገለጥ እንደምታይ የምታስብ ከሆነ ፈጽመህ ለጥሪው ምላሽ እንደማትሰጥ ያሳያል፡፡

    አገልግሎትህን በሚገባ ለመፈጸም እግዚአብሔር እንዴት እንደሚጠራህ እና ወደ ፍሬያማነትም እንዴት እንደሚመራህ መረዳት ይኖርብሃል፡፡ አገልግሎትህን ለመፈጸም በህይወትህ ውስጥ ለሚሆኑት መለኮታዊ ክስተቶች ምላሽ መስጠት ግድ ይልሃል፡፡

    መለኮታዊ ክስተቶች

    አብዛኛው ሰው በመለኮት የተቀናበሩትን ክስተቶች አይገነዘባቸውም፡፡ ተረዳህም አልተረዳህ፣ በህይወትህ ለሚከናወኑት መለኮታዊ ክስተቶች ምላሽ ከነፈግህ አገልግሎትህን መፈጸም ይሳንሃል፡፡ ብዙ ሰዎችም አገልግሎታቸውን መፈጸም ያልቻሉበት ሚስጥር በመለኮታዊ አሰራር ለተቀናበሩ ክስተቶች ምላሽ ባለመስጠታቸው ነው፡፡ እነዚህ መለኮታዊ ክስተቶች ምንድን ናቸው? በህይወትህ የሚሆኑ መለኮታዊ ክስተቶች፡

    1.   መለኮታዊ ስበት፡፡ (ዮሐ. 6፡44)

    2.   መለኮታዊ መሻት፡፡ (1ኛ ጢሞ. 3፡1)

    3.   መለኮታዊ እርግጠኝነት፡፡ (ዮሐ. 16፡7-8)

    4.   መለኮታዊ ፍቅር፡፡ (ዘዳ. 6፡5)

    5.   መለኮታዊ የእግዚአብሔር ምህረት፡፡ (2ኛ ቆሮ 4፡1)

    6.   መለኮታዊ መለየት፡፡ (ዘዳ. 10፡8)

    7.   መለኮታዊ የእግዚአብሔር ፈቃድ፡፡ (ኤፌ. 1፡9)

    8.   መለኮታዊ ጥሪ፡፡ (ሮሜ. 1፡1)

    9.   መለኮታዊ ተልዕኮ፡፡ (ዮሐ. 1፡1-3)

    10.          መለኮታዊ ዕቅዶች፡፡ (ምሳ. 16፡4)

    11.          መለኮታዊ ራዕዮች፡፡ (ሐዋ. 26፡19)

    12.          መለኮታዊ የስጦታዎች ማካፈል (ሮሜ. 1፡11)

    13.          መለኮታዊ ጸጋ (2ኛ ጢሞ. 1፡8-9)

    14.          መለኮታዊ የአገልግሎት ቢሮ (ሮሜ 12፡4)

    በአገልግሎትህ ምን ማድረግ እንደሚገባህ ከማወቅህ በፊት ቀጥተኛ ድምጽ መስማት እንዳለብህ ማስመሰልህ ምንም አይነት ጥቅም የለውም፡፡ ማድረግ የሚገባህን ከማድረግህ በፊት ኢየሱስ እንዲገለጥልህ እየጠበቅህ እንደሆነ መመስከርህ ዋጋ የለውም፡፡ ወደ ትክክለኛው አገልግሎት የሚመራህ እና አገልግሎትህንም እንድትፈጽም የሚረዱህ በርካታ መለኮታዊ ክስተቶች አሉ፡፡ ሚስጥራዊው የእግዚአብሔር ፈቃድ፣ የእግዚአብሔር ዓላማ እና እግዚአብሔር በህይወትህ የሚያሳይህ ምህረቱ በቀጥታ ወደ አገልግሎት የሚመሩህ ብርቱ ህይወት ለዋጭ ክስተቶች ናቸው፡፡

    ለእግዚአብሔር ምህረት እና ፍቅር ምላሽ ሳትሰጥ አገልግሎት ውስጥ ልትሆን አትችልም፡፡ ጳውሎስ የእግዚአብሔር ፍቅር ግድ እንደሚለው ተናግሯል፡፡ ከቤተሰብህ፣ ከአገርህ እና ከህዝብህ መለየትህ በህይወትህ የተከናወነ አስፈላጊ መንፈሳዊ ክስተት ነው፡፡ ለእነዚህ መንፈሳዊ ክስተቶች በአግባብ ምላሽ መስጠት ደግሞ አገልግሎትህን እንድትፈጽም ያደርግሃል፡፡

    ምዕራፍ 2

    የሳበህን ተከተለው

    የላከኝ አብ ከሳበው በቀር ወደ እኔ ሊመጣ የሚችል የለም፥ እኔም በመጨረሻው ቀን አስነሣዋለሁ። ዮሐ. 6፡44

    የሳበህን አካል በመከተልህ አገልግሎትህን መፈጸም ይቻልሃል! በአንድ አካል መሳብህ ልዕለ ተፈጥሮአዊ ነው! የእግዚአብሔር ፍርሃት ይኑርህ፤ እግዚአብሔርም ወደሚስብህ ሰው ተገቢ የሆነ አክብሮትን ስጥ፡፡ ወደ ተሳብካቸውም ሰዎች ስትከተል፣ አገልግሎትህን መፈጸም ትችላለህ!

    1.   ወደ እግዚአብሔር ስትሳብ፣ ልዕለ ተፈጥሮአዊ ልምምድ ይኖርሃል፡፡

    ወደ እግዚአብሔር መሳብ  ልዕለ ተፈጥሮአዊ ነው፡፡ የሚስብህ አብ አባት ነው፡፡ ብዙ ሰዎች እግዚአብሔርን አይወዱትም! በርካታ ሰዎችም መጸለይም ሆነ መጾም አይፈልጉም፡፡ በዛ ያሉ ሰዎች መጽሐፍ ቅዱስን አይወዱም! ሌሎች ብዙዎችም ቤተክርስቲያንን አይወዱም፡፡ ወደሆነ ነገር መቅረብ በዚያ ነገር መሳብን ያመላክታል፡፡ እግዚአብሔር ወደ እርሱ እና ወደቤተክርስቲያን እንድትሳብ ይህን በልብህ አኑሯል!

    ወደ ቤተክርስቲያን፣ ወደ ክርስቲያን ነገሮች እና ወደ እግዚአብሔር ስትሳብ ራስህን አግኝተኸው ይሆናል፡፡ ወደ ምሽት ክበብ ሳይሆን ወደ ቤተክርስቲያን በስውር መሳብህ ምን ማለት እንደሆነ በቀላሉ ላታስተውለው ትችላለህ፡፡

    የተሳብክለትን ነገር መገንዘብ አስፈላጊ ነው፡፡ ሁላችን ወደተለያየ ነገር እንሳባለን፡፡ የተሳብክለትን ስትገነዘብ ጥሪህን መረዳት ከመጀመርህም በላይ አገልግሎትህን መፈጸም ትችላለህ፡፡

    2.   ወደ ሰው ስትሳብ፣ መንፈሳዊ ልምምድ ይኖርሃል፡፡

    ወደ አንድ ሰው በመሳብ እና የሆነን ነገር በመሻት መካከል ያለው ልዩነት ምንድን ነው? ወደ አንድ ሰው ስትቀርብ፣ ወደዚያ ሰው ስትሳብ ራስህን ታገኘዋለህ፡፡ ያ ሰው በሚናገረው እና በሚያደርገው ነገር ሁሉ ፍላጎት ያድርብሃል፡፡ የሆነ ነገር ስትሻ በውስጥህ ያንን ነገር ለማግኘት ጠንካራ ፍላጎት ያድርብሃል፡፡ ባንተ ላይ ብርቱ ተፅዕኖ የሚፈጥርብህ ታዲያ ከ"መሳብ˝ በላይ ጥልቅ ፍላጎት ነው፡፡

    3.   ወደሆነ አካል ስትሳብ ለመገንዘብ አስቸጋሪ ሊሆን ይችላል፡፡

    ወደሆነ አካል መሳብህን መገንዘብ ካሉት መንፈሳዊ ልምምዶች ሁሉ አስቸጋሪው ነው፡፡ ምክንያቱም ወደ እግዚአብሔር ስትሳብ ባንተ ላይ እየሆነ ያለውን ነገር በቀላሉ አታስተውለውም፡፡ ሆኖም ግን ራስህን ቤተክርስቲያን ውስጥ፣ ህብረት ውስጥ፣ ስብሰባ ውስጥ እንዲሁም በወንድሞች መካከል ታገኘዋለህ፡፡

    4.   አብ ወደመረጣቸው የእግዚአብሔር ሰዎች ትሳባለህ፡፡

    የላከኝ አብ ከሳበው በቀር ወደ እኔ ሊመጣ የሚችል የለም፥ እኔም በመጨረሻው ቀን አስነሣዋለሁ። ዮሐ. 6፡44

    ወደ እግዚአብሔር ሰው ልትሳብ ትችላለህ! እግዚአብሔር ከእነርሱ እንድትማር ወደሚፈልጋቸው ሰዎች ይስብሃል፡፡ በርካታ የእግዚአብሔር ሰዎች በገሚሱ ሲወደዱ በሌሎች ግን ደግሞ ይናቃሉ፡፡ ላንተ የተወደደው የእግዚአብሔር ሰው ሌሎች የሚበሳጩበት ሊሆን ይችላል፡፡

    አንተ እጅግ የምትመሰጥበት የእግዚአብሔር ሰው ሌላው ግን ሊያየው የማይፈልገው ሊሆን ይችላል፡፡ አብ ራሱ ካልሳበው በቀር ወደ አብ ሊመጣ የሚችል የለም፡፡ ዘወትር በአገልጋዩ አማካኝነት እጅግ ስውር እና ባልታወቀ መንገድ ወደራሱ የሚስብህ አብ አባት ነው፡፡ ኢየሱስ በግልጽ እንዳመለከተው እግዚአብሔር በዚያ ሰው ልብ ውስጥ ስራውን ካልሰራ እና ካልሳበው በቀር ወደ እርሱ የሚሳብ የለም፡፡ ኢየሱስ በሁሉም ሰው የሚወደድ አልነበረም፡፡ በስቅለቱ ጊዜ አብዛኞቹ አይሁዳውያን በዚያ ተሰብስበው ነበር፡፡ ሁሉም ታዲያ ታላቅ ሰው እንደሆነ የሚያስቡ አልነበሩም፡፡ ኢየሱስ ይህንን ሁናቴ ሲያብራራው ታዲያ "አብ ካልሳበው በቀር ወደ እኔ የሚመጣ የለም˝ በማለት ነው፡፡ ኢየሱስ ወደ እርሱ የሚመጣ እና የሚሳብ እያንዳንዱ ሰው በልዕለ ተፈጥሮአዊ አሰራር መሆኑን ያውቅ ነበር፡፡

    5.   በተለያየ ጊዜያት ወደተለያዩ ሰዎች ትሳባለህ፡፡

    Enjoying the preview?
    Page 1 of 1