Discover millions of ebooks, audiobooks, and so much more with a free trial

Only $11.99/month after trial. Cancel anytime.

መርገሞችን እንዴት ማክሸፍ ይቻላል
መርገሞችን እንዴት ማክሸፍ ይቻላል
መርገሞችን እንዴት ማክሸፍ ይቻላል
Ebook410 pages3 hours

መርገሞችን እንዴት ማክሸፍ ይቻላል

Rating: 4 out of 5 stars

4/5

()

Read preview

About this ebook

ይህ የሚያስደንቅ መጽሐፍ እየሰራ ያለውን መርገም እንድንቋቋም እና ታላቅነትህን እየተዋጋህ ያለውን መርገም ጸጥ ማሰኘት እንድትችል ይረዳሃል። ማንም ብትሆን እግዚአብሔር ላንተ ትልቅ የህይወት ፍጻሜ አለው። የእርግማንን ሃይል ለምቋቋም ይህን መጽሐፍ እንደ ትልቅ መሳሪያ ተጠቀምበት።

Languageአማርኛ
Release dateJan 15, 2019
ISBN9781641357869
መርገሞችን እንዴት ማክሸፍ ይቻላል
Author

Dag Heward-Mills

Bishop Dag Heward-Mills is a medical doctor by profession and the founder of the United Denominations Originating from the Lighthouse Group of Churches (UD-OLGC). The UD-OLGC comprises over three thousand churches pastored by seasoned ministers, groomed and trained in-house. Bishop Dag Heward-Mills oversees this charismatic group of denominations, which operates in over 90 different countries in Africa, Asia, Europe, the Caribbean, Australia, and North and South America. With a ministry spanning over thirty years, Dag Heward-Mills has authored several books with bestsellers including ‘The Art of Leadership’, ‘Loyalty and Disloyalty’, and ‘The Mega Church’. He is considered to be the largest publishing author in Africa, having had his books translated into over 52 languages with more than 40 million copies in print.

Related to መርገሞችን እንዴት ማክሸፍ ይቻላል

Related ebooks

Reviews for መርገሞችን እንዴት ማክሸፍ ይቻላል

Rating: 4.111111111111111 out of 5 stars
4/5

9 ratings0 reviews

What did you think?

Tap to rate

Review must be at least 10 words

    Book preview

    መርገሞችን እንዴት ማክሸፍ ይቻላል - Dag Heward-Mills

     ክፍል 1

    የመርገሞች እውነታ

     ምዕራፍ 1

    ስለ መርገሞች መጻፍ ለምን አስፈለገ?

    ስለዚህ መርገም ምድርን ትበላለች በእርስዋም የተቀመጡ ይቀጣሉ፤ ስለዚህ የምድር ሰዎች ይቃጠላሉ ጥቂት ሰዎችም ይቀራሉ።

    ኢሳይያስ 24: 6

    ከላይ ካለው ጥቅስ እንደምንረዳው፣ ምድርን የሚያጠፏት እርኩሳን መናፍስት ወይም አጋንንት ሳይሆኑ እርግማን ነው።

    1. ዘመናዊ ክርስቲያኖች ለመርገሞች ተገቢ ቦታ ሊሰጡት ይገባል።

    ትእዛዝህን ሁሉ ስመለከት በዚያን ጊዜ አላፍርም።

    መዝሙር 119: 6 

    ዘመናዊ ክርስቲያኖች ከእርግማን በላይ ስለ እርኩሳን መናፍስት እና አጋንንቶች በበለጠ ይረዳሉ። ዘመናዊ ክርስቲያኖች የአጋንንትን የመኖር እውነታ ያከብራሉ፣ ነገር ግን የመርገም እውነታው አያስፈራቸውም አንዲሁም ቦታ አይሰጡትም።

    ይህንን መጽሐፍ በምታነቡበት ጊዜ ለመርገሞች እውነታ ተገቢና ጤናማ አክብሮት ማዳበር እንድትችሉ ጸሎቴ ነው። በአጋንንት፣ በክፉ መናፍስት እና በዲያብሎስ ስለ መኖራቸው እውነታ አምናለሁ። በየቀኑ አስራቸዋለሁ እንዲሁም ከህይወቴ አስወጣቸዋለሁ። ስለ አጋንንት ብዙ መጻሕፍትን ጽፌያለሁ። ሆኖም ግን፣ በእርኩሳን መናፍስት አመካይነት ተስፋ መቁረጥን፣ ክፋትንና ሞትን  እንዲያመጡ የሚያደርገው እርግማን እንደሆነም አምናለሁ። እርግማንን የሚያስፈጽሙት እርኩሳን መናፍስት ናቸው! መርገሞች ክፉ መናፍስት ክፋታቸውን ለማከናወን እንዲችሉ ህጋዊ መንገድን ይሰጣሉ። በእርግማን መኖርም ብታምኑም ሆነ ባታምኑ የመርገሞች መኖር እውን ነው!

    ዛሬ እኛ የምናየው የሰዎች ህይወት ያሉበትብን ሁኔታ የሚወሰነው እና የሚቀረጸውን እርግማን መኖሩን አትኩሪት መስጠት አለብህ! ዛሬ የምናልፍበትን አብዛኛው ነገሮቻችን ከዓመታት በፊት በተነገሩት እርግማንና በረከቶች የተወሰነ ነው። በእርግጥም፣ ከዋነኞቹ የመንግስተ ሰማያት መገለጫዎች አንዱ በዚያ እርግማን አለመኖሩ ነው።

    ይህን ያደረገውን ግን አልተመለከታችሁም፣ ቀድሞ የሠራውንም አላያችሁም።

    ኢሳይያስ 22: 11

    2. እርግማን ሲገኝ መጠቆም የእግዚአብሔር አገልጋይ ኃላፊነት ነው።

    አንድ መጋቢ እርግማን መኖሩን መለየቱ ስህተት አይደለም። የእግዚአብሔርን ቃል አትዋጋ! የእግዚአብሔር ቃል በደንብ የሚያሳንን እርግማን፣ እንተ እርግማን የለም ብለህ አትካድ። አንድ መጋቢ አንድ ሰው ወይም የተወሰኑ ሰዎች በእርግማን ስር እየለፉ እንደሆነ መናገር ወይም ማወጅ ምንም ስህተት የለውም! አንድ እግዚአብሔርን የሚያገለግል መልካም ሰው እግዚአብሔር ለእርሱ መርገሞችን በሚያሳየው ጊዜ፣ መለየት የእርሱ ኃላፊነት መሆኑ እርግጥ ነው። ነቢዩ ሚልክያስ ለእስራኤል ህዝብ የተናገረውን አድምጡ። እንዲህ አላቸው፣ በእርግማን ርጉሞች ናችሁ!። እርግማኑን በማሳየቱ አልተሳሳተም። እርግማን እውን እንደሆነ እና በዚያ ስፍራ መኖሩን በመለየቱ ያደረገው ትክክል ነበር ። እርግማን ማሸነፍ የምትችለው ለይተህ ስታወጣው ብቻ ነው። እርግማን የለም ብለህ የምትክድ ከሆን፣ እንዴት አድርገህ መከላከል ወይም ማክሸፍ ትችላለህ?

    እናንተ፣ ይህ ሕዝብ ሁሉ፣ እኔን ሰርቃችኋልና በእርግማን ርጉሞች ናችሁ።

    ሚልክያስ 3: 9

    3. እርግማን ተለይቶ ሲወጣ እና ሲጠቆምህ አትናደድ።

    በሚልክያስ ዘመን፣ የእግዚአብሔር ሕዝብ እርግማን ስለመኖሩ ሲነግራቸው አልተቆጡም ነበር። በዚህ መጽሐፍ ውስጥ መርገም በተለያዩ የህብረተሰብ ህዝቦች ላይ ያለውን ተፅእኖ በምጽፍበት በማንኛውመም ነገር አትናደዱ። እነዚህን ነገሮች የምጽፈው ማንኛውንም ህብረተሰብ ለመጣል ሳይሆን እርግማን መኖሩን ለይቶ በማወቅ ማክሸፍ እንዲቻል ነው። የዚህ መጽሐፍ አብዛኛው ክፍል እርግማኑን ማክሸፍ እና ማሸነፍ ላይ ያተኮረ ነው። በእግዚአብሔር ቃል ውስጥ ስለ መርገሞችና በረከቶች ያለውን እውነታ ሳካፍላችሁ ጠላታችሁ አታድርጉኝ።

    ነቢዩ ሚልክያስ እውነቱን እንደተናገረ እና ህዝቡም ከእርግማን በታች እንደነበሩ እንደነገራቸው፣ እኔም ስለ እርግማን መኖር እየነገርኳችሁ ነው።

    እንኪያስ እውነቱን ስለ ነገርኋችሁ ጠላት ሆንሁባችሁን?

    ገላትያ 4: 16

    4. እያንዳንዱ እርግማን ሊከሽፍ ይችላል።

    ሁሉም መርገሞች ሊከሽፉ እንደሚችሉ አምናለሁ! ይህን መጽሐፍ የምጽፈው ለእግዚአብሔር ቃል ክፍት የሆነ ሰው ሁሉ እርግማን መለየት እንዲችል እና በእግዚአብሔር ጥበብ እርግማንን ማሸነፍ እንዲችል ነው። አንድ ነገር የለም የምትል ከሆነ እንዴት ልታከሽፈው ትችላለህ? የእርግማንን መኖሩን አለመቀበልህ ትልቅ ድክመትህ ነው!

    የዚህን መጽሐፍ ትምህርት ማንኛውንም ህብረተሰብ ለማዋረድ፣ ለመስደብ ወይም ለማንቋሸሽ አትጠቀምበት። ያ ስህተት ነው። የዚህን መጽሐፍ ትምህርት ሰዎችን ከታወቁ መርገሞች ሁሉ ለማውጣት ተጠቀምበት።

    ይህ የተስፋ መጽሐፍ ነው! ይህ የድል መጽሐፍ ነው! በእግዚአብሔር ጥበብ እና በእግዚብሔር ኃይል በእርግማን ላይ ያለህን የበላይነት የሚያውጅ መጽሐፍ ነው። በዓለም ላይ ያሉ ሁሉም የህብረተሰብ ክፍሎች፣ ሀብታሞች፣ ድሆች፣ ወንዶች፣ ሴቶች፣ አይሁዶች፣ አይሁድ ያልሆኑ፣ ጥቁሮችና ነጮች በእግዚአብሔር የተከበሩ ናቸው እንዲሁም በህይወታቸው ውስጥ የሚሰራውን እርግማን ሁሉ ለማምለጥ እና ለማሸነፍ እድል አላቸው ብዬ አምናለሁ። እግዚአብሔር ያከብርሃል ተነስተህም ታላቅ እንድትሆን ይጠብቃል።

    መጽሐፉን ማንንም ሰው ለማጭበርበር፣ ለማሰር ወይም ለመዝረፍ አትጠቀምበት። እንዲህ የምታደርግ ከሆነ የተረገምህ ትሆናለህ! እባካክህ ይህንን መጽሐፍ በህይወትህ ውስጥ እየሰራ ሊኖር ለሚችለው ማንኛውንም ዓይነት መርገም ለማሸነፍ፣ ለማክሸፍ፣ እንዳይሰራ ለማድረግ እና ለማጥፋት ተጠቀምበት። ከዚህ በታች ያለውን ጥቅስ አንብብ እና የእግዚአብሔር ፈቃዱ አንተ ከሁሉም ሰዎች ጋር እኩል እንደሆንህ እና በእርግማን ሁሉ ላይ ባለ ድል መሆንህን ልብ ብለህ ተረዳ።

    ጴጥሮስም አፉን ከፍቶ እንዲህ አለ። እግዚአብሔር ለሰው ፊት እንዳያደላ ነገር ግን በአሕዛብ ሁሉ እርሱን የሚፈራና ጽድቅን የሚያደርግ በእርሱ የተወደደ እንደ ሆነ በእውነት አስተዋልሁ።

    የሐዋርያት ሥራ 10: 34 – 35

     ምዕራፍ 2

    እርግማን ምንድን ነው?

    ከእንግዲህም ወዲህ መርገም ከቶ አይሆንም። የእግዚአብሔርና የበጉም ዙፋን በእርስዋ ውስጥ ይሆናል፣ ባሪያዎቹም ያመልኩታል፣ ፊቱንም ያያሉ፣

    ራእይ 22:3

    በምድር ላይ ህይወት ተደጋጋሚ ተስፋ መቁረጥ፣ ቋሚ ደስታ ማጣት፣ ያልታወቀ አደጋ፣ ሞት፣ ባዶነት፣ ተደጋጋሚ ጥቃት፣ ግራ መጋባት፣ ከንቱነት፣ ጦርነት፣ ቋሚ ግጭት እና ድህነት የተሞላ ነዉ። እንዲህ ዓይነቱ መግለጫ አንድ ትርጉም ብቻ ነው ያለዉ - እርግማን

    ብዙ ሰዎች በምድር ውስጥ መርገሞች መኖራቸዉን እንኳን አያውቁም። ይህ መጽሐፍ በምድር ላይ ያሉትን መርገሞች ለመለየት እና ለእነሱ ተገቢው ትኩረት እንዲኖራችሁ ለማገዝ የታሰበ ነው። ለመርገሞች ተገቢ የሆነ አክብሮት የሌለው ማንኛውም ሰው በመጨረሻ ሊጸጸት ይችላል።

    በዛሬው ጊዜ በምድር ላይ በጣም ተንሰራፍተው ከሚገኙ ነገሮች አንዱ ‘እርግማን' እና አስከፊው ውጤቱ ነው። በስራ ላይ ያሉ በርካታ ጥንታዊ መርገሞች እንዲሁም በሺዎች የሚቆጠሩ አዳዲስ እና ዘመናዊ መርገሞች አሉ። በዚህ ምድር ላይ ህይወት ምን እንደሚመስል አስቡና በምድር ላይ እርግማን መኖሩን ወዲያውኑ ትቀበላላችሁ። እርግማንን ለመግለጽ ቀላል አይደለም፤ስለዚህ ትክክለኛዉን ገለጻ ለማግኘት ወደ መጽሐፍ ቅዱስ ፊታችሁን ዘወር አድርጉና እርግማን ምን እንደ ሆነ ተመልከቱ። አሥር የመጽሐፍ ቅዱስ ትርጓሜያዊ ፍቺዎችን እንመልከት እስቲ።

    አሥር መጽሐፍ ቅዱሳዊ የእርግማን ትርጓሜዎች

    1. እርግማን በሆነ ሰው ላይ ጥቃት ወይም ሞት እንዲመጣ ለልዕለ ተፈጥሮአዊ ኃይል የሚደረግ ልመና ነዉ። የሞዓብ ንጉሥ ባላቅ በእስራኤል ላይ እርግማን እንዲናገር በለዓምን ጠይቆት ነበር።

    በአንድ ሰው ላይ እርግማን አለ ማለት በዚያ ሰዉ ላይ ደስ የማይሉ ነገሮች እንዲከሰቱ የሚያደርግ ልእለ ተፈጥሮአዊ የሆነ ኃይል ያለ ይመስላሉ ማለት ነው። እርግማንን እንደ ትልቅ ችግር እና ጉዳት የሚያመጣ ነገር ልትመለከተው ትችላለህ። ትልቅ ችግርና ጉዳት ሊያደርስብህ ከሚችል እርግማን አሁን ነፃ ወጥተሃል !

    ምሳሌውንም ይመስል ጀመር፣እንዲህም አለ፦  ባላቅ ከአራም አመጣኝ፣ የሞዓብ ንጉሥ ከምሥራቅ ተራሮች፤ ና፣ ያዕቆብን ርገምልኝ፤ ና፣ እስራኤልን ተጣላልኝ ብሎ።

    እግዚአብሔር ያልረገመውን እንዴት እረግማለሁ? እግዚአብሔር ያልተጣላውን እንዴት እጣላለሁ?

    ዘኍልቍ 23:7-8

    2. እርግማን ማለት የሆነ ዓይነት አደጋ ወይም ጥፋት የሆነ ሰዉ ላይ እንዲመጣ በግልጽ የተነገረ ምኞት ነዉ። በተለይም ‘መርገም' ማለት በማንኛውም ልዕለ ተፈጥሮአዊ ኃይል ማለትም በእግዚአብሔር ወይም በአስማት፣ በጥንቆላ፣ በጸሎት ወይም በመናፍስት በሌላ ሰው ላይ ጉዳት ወይም መቅሰፍት እንዲያስከትል ታስቦ የሚነገር ምኞት ነው። እርግማንን መለወጥ ወይም ማስወገድ እርግማንን መስበር ወይም ማክሸፍ ሲሆን ብዙውን ጊዜ በእኩል ደረጃ የተራቀቁ ሥርዓቶች ወይም ጸሎቶች እንደሚጠይቅ ይታመናል።

    እግዚአብሔር ጣዖትን በሚያመልኩ ሰዎች ሁሉ ላይ እርግማን አድጎባቸዋል። ከጣዖት ጋር ከተያያዙ ነገሮች ጋር ምንም አታድርግ በምድር ላይም ካሉ አደገኛ መርገሞች ታመልጣለህ። ገንዘብን አታገልግል! ገንዘብን አታምልክ! ስለ ገንዘብ ብለህ ምንም ነገር አታድርግ ከኃይለኛም እርግማን ትድናለህ! 

    በእግዚአብሔር ዘንድ የተጠላ የሠራተኛ እጅ ሥራን የተቀረጸ ወይም ቀልጦ የተሠራ ምስልን የሚያደርግ፣ በስውርም የሚያቆመው ሰው ርጉም ይሁን፤ ሕዝቡም ሁሉ መልሰው አሜን ይላሉ።

    ዘዳግም 27:15

    3. መረገም ማለት ለውድቀት እና ለዝቅተኛነት መዳረግ ነው። እባቡ በእግዚአብሔር በመረገሙ ምክንያት ከከፍታው ወርዶ ለውድቀት እና ለዝቅተኛነት ተጋልጧል። በእግዚአብሔር ፀጋ እንደ እባብ ለውድቀት እና ለዝቅተኛነት በፍፁም አትዳረግም! እባብ ወደ ምድር ዝቅተኛ ቦታ እንዲጣል ተፈረደበት። በተጨማሪ እባቡ ለዘላለም ከምድር አፈር እንዲበላ ተፈርዶበታል። ይህ ማንኛውም ፍጥረት ሊወርድ የሚችልበት የመጨረሻ ዝቅታ ነው። የተረገምክ ስትሆን ወደ ዝቅተኛው ቦታ ትወርዳለህ። እስከመጨረሻው ወደታች እና ለመውደቅ ትዳረጋለህ። አሁን እግዚአብሔር አንተን በኃይሉ ለማንሳት ወደ ህይወትህ እየገባ ነው።

    እግዚአብሔር አምላክም እባቡን አለው። ይህን ስላደረግህ ከእንስሳት ከምድር አራዊትም ሁሉ ተለይተህ አንተ የተረገምህ ትሆናለህ፤ በሆድህም ትሄዳለህ፣ አፈርንም በሕይወትህ ዘመን ሁሉ ትበላለህ።

    ዘፍጥረት 3:14

    4. የተረገመ መሆን ማለት በተደጋጋሚ ሃዘን ዉስጥ መሆን ማለት ነው። አንድን ነገር እርግማን የሚያሰኘዉ ተደጋጋሚ፣ ቀጣይነት ያለው እና የማያቋርጥ ሃዘን ማሰከተሉ ነው። አዳም በቀሪው የሕይወት ዘመኑ ሁሉ ለሀዘን ተዳርጎ ነበር። የሰው ልጆች የማያቋርጥ ሐዘን ምክንያቱም ይህ ነው። በመላው ዓለም ላይ የሚታይው የማያቋርጥ ሀዘን፣ የመንፈስ ጭንቀት እና ጨለማ የእርግማንን መኖሩ ማረጋገጫ ነው። ከመንፈስ ቅዱስ የሚመጣውን ደስታ ተቀበል አና ከዚህ እርግማን በላይ ከፍ በል!

    አዳምንም አለው። የሚስትህን ቃል ሰምተሃልና፣ ከእርሱ እንዳትበላ ካዘዝሁህ ዛፍም በልተሃልና ምድር ከአንተ የተነሣ የተረገመች ትሁን፤ በሕይወት ዘመንህም ሁሉ በድካም ከእርስዋ ትበላለህ፤

    ዘፍጥረት 3:17

    5. መረገም ማለት ሁልጊዜ ሁሉም ነገሮች አንተን ባለማቋረጥ ሲቃወሙህ ነው። መረገም መልካምነትን፣ መልካም እድልን እና ህይወትን መቀበል ሲገባህ በፋንታው ክፉ፣ ጠማማ እድል እና ሞት ሲያጋጥምህ ነው።

    እሾህንና አሜከላን ታበቅልብሃለች፤ የምድርንም ቡቃያ ትበላለህ።

    ዘፍጥረት 3:18

    6. መረገም ማለት በከንቱ ላብ ማንጠፍጠፍ፣ ትግል ማድረግ፣ መጨናነቅ፣ መከራን መቀበል ማለት ነው። በዓለም ውስጥ ያለው ውጊያው፣ ትግል እና ክንቱ ልፋት የእርግማን መኖር ማስረጃዎች ናቸው። ምድር ላይ ካሉ ውጥረት፣ ድካም እና ከንቱነቱ በላይ ከፍ ለማለት ፀጋን ተቀበል።

    አዳምንም አለው። የሚስትህን ቃል ሰምተሃልና፣ ከእርሱ እንዳትበላ ካዘዝሁህ ዛፍም በልተሃልና ምድር ከአንተ የተነሣ የተረገመች ትሁን፤ በሕይወት ዘመንህም ሁሉ በድካም ከእርስዋ ትበላለህ፤

    እሾህንና አሜከላን ታበቅልብሃለች፤ የምድርንም ቡቃያ ትበላለህ። ወደ ወጣህበት መሬት እስክትመለስ ድረስ በፊትህ ወዝ እንጀራን ትበላለህ፤ አፈር ነህና፣ ወደ አፈርም ትመለሳለህና።

    ዘፍጥረት 3:17-19

    7. የተረገመ መሆን ሁልጊዜ ተስፋ መቁረጥ፣ ደስተኛ አለመሆን እና ለሰራህው ስራ የሚገባውን ተቃራኒ መቀበል ነው። ቃየን የተረገመ ነበር ይህም የዚህ እርግማን መተግበር ነበር። ባዶነት፣ ከንቱነት፣ ተስፋ መቁረጥ፣ የተሻሉ ነገሮችን ለመያዝ መጣር የእርግማን መኖር ዋነኛው ምልክት ነው። የሰዉ ልጅ ትምህርት ቤት ቢሄድ እና ቢሰራም ቢለፋም ባዶነት እና ከንቱነት የሰውን ዘር ተቆጣጥረውታል።

    እግዚአብሔርም ቃየንን አለው። ወንድምህ አቤል ወዴት ነው? እርሱም አለ። አላውቅም፤ የወንድሜ ጠባቂው እኔ ነኝን? አለውም። ምን አደረግህ? የወንድምህ የደሙ ድምፅ ከምድር ወደ እኔ ይጮኻል።

    አሁንም የወንድምህን ደም ከእጅህ ለመቀበል አፍዋን በከፈተች በምድር ላይ አንተ የተረገምህ ነህ። ምድርንም ባረስህ ጊዜ እንግዲህ ኃይልዋን አትሰጥህም፤ በምድርም ላይ ኰብላይና ተቅበዝባዥ ትሆናለህ።

    ዘፍጥረት 4:9-12

    8. የተረገመ መሆን አለመጽናት፣ ከንቱ መሆን፣ ሁልጊዜ መሮጥ፣ ሁልጊዜ መለመን፣ ስርዓት አልባ መሆን፣ ወሮ በላ መሆን እና የማይጠቅም ሰው መሆን ነው። ወሮ በላ መሆን በእርግማን ስር መሆን ማለት ነው። እግዚአብሔር ወሮ በላ ከሚመስል ሁኔታ ዉስጥ እያወጣህ ነው!

    እግዚአብሔርም ቃየንን አለው። ወንድምህ አቤል ወዴት ነው? እርሱም አለ። አላውቅም፤ የወንድሜ ጠባቂው እኔ ነኝን? አለውም። ምን አደረግህ? የወንድምህ የደሙ ድምፅ ከምድር ወደ እኔ ይጮኻል።

    አሁንም የወንድምህን ደም ከእጅህ ለመቀበል አፍዋን በከፈተች በምድር ላይ አንተ የተረገምህ ነህ። ምድርንም ባረስህ ጊዜ እንግዲህ ኃይልዋን አትሰጥህም፤ በምድርም ላይ ኰብላይና ተቅበዝባዥ ትሆናለህ።

    ዘፍጥረት 4:9-12

    9. የተረገመ መሆን የባሪያዎች ባሪያ መሆን ነው። የባሪያዎች ባሪያ በቋሚነት ከእድገት እና ብልጽግና መከልከል፣ ሁልጊዜ ግራ መጋባትና የተደናቀፈ መሆን ነው። የባሪያዎች ባሪያ በተደጋጋሚ ከፍ አለማለት፣ ደስታን ማጣትና እና ብቸኛ መሆን ነው። ከማንኛውም ለማምለጥ ከማይቻል ባርነት ነፃ ወጥተሃል! 

    እንዲህም አለ። ከነዓን ርጉም ይሁን፤ ለወንድሞቹም የባሪያዎች ባሪያ ይሁን።

    ዘፍጥረት 9:25

    10. የተረገመ መሆን በሚያሳዝን የህይወት ፍጻሜ መከበብ፣ መጠቃት፣ ያለማቋረጥ መጨነቅ፣ ማምለጥ አለመቻል ነው። ስትገባም ስትወጣም ወደ ተመሳሳይ ድምዳሜና ግራ መጋባት ትመጣለህ። እግዚአብሔር በዙሪያህ ከከበቡህ ጠላቶችህ የምትድንበትን የጥበብ ቁልፍ እየሰጠህ ነው! 

    አንተ በመግባትህ ርጉም ትሆናለህ፣ በመውጣትህም ርጉም ትሆናለህ።

    ዘዳግም 28:19

    እነዚህ የእርግማን ትርጓሜዎች የሚያመለክቱት የተረገመ ሰዉ የተከበበ መሆኑን ነው። የተረገመ መሆን የተከበበ መሆን ነው። የተከበብክ ስትሆን ምንም ነገር አይሰራልህም። የእርግማን ሁሉ ትርጓሜዎች ወደዚህ ድምዳሜ ይወስደናል። የተከበብክ ነህ! 

    ንብ ማርን እንዲከብብ ከበቡኝ

    መዝሙር 118:12

    መከበብ ሲባል ምን ማለት እንደሆነ ለመረዳት እንሞክር። በሞት የተከበባችሁ ከሆነ፣ በምትሄዱበት አቅጣጫ ሁሉ ያገኛችኋል። ስለዚህ ለመሞት የተረገምክ ከሆነ የትኛውን አቅጣጫ ብትዞር ሞት ያገኝሃል። ሻይ እየጠጣህ ልትሞት ትችላለህ። ረጅም ጉዞ እያደረክ ልትሞት ትችላለህ። እርግማንን አንድ ሰው በችሎታው ማምለጥ አይችልም። ማምለጥ የሚቻልበት መንገድ ስለሌለ እርግማን ይፈጸማል። ስለሆነም ክርስቲያኖች ለእርግማንና ለበረከት ትክክለኛው መረዳት ሊኖራቸው ይገባል።

    መረገም በዙሪያህ የታጠርህ መሆን ማለት ነው። በዙሪያህ ታጥረሃል ማለት ተከብበህ ሁሉም የአቅርቦት መስመሮች እና የማገገሚያ መንገዶች ሙሉ በሙሉ ሲዘጉ ማለት ነው። በዚህ ህይወት ውስጥ ብዙ ነገሮች ትርጉም እንደማይሰጡ ተገነዘባለህ። ብዙ ነገሮች እንደዚያ ለምን እንደሆኑ እንኳን ለማወቅ ያስቸግራል። ብዙ ነገሮች ከጠበቅከው ፍጹም ተቃራኒ ይሆናሉ።

    እርግማን ለመረዳት የማይቻል እና የማይታወቅ ስዕል ይፈጥራል። ያ ምስል በየትኛውም ጊዜ እንዴትም ቢሆን የትም ቢሆን በእርግማን ውስጥ ያሉትን ሰዎች ተመሳሳይ ታሪክ ያመላክታል ! የአፍሪካን ታሪክ ተመልከቱ! የአፍሪካ ሀገሮች ቅኝ አገዛዝ ወይም አፓርታይድ ውስጥ ነበሩ፣ በቀኝ ባይገዙም አብዮታዊ ለዉጦች፣ ዴሞክራሲ፣ እራሳቻውን ቢችሉም እንኳን በአፍሪካ ውስጥ ያላቸው ተመሳሳይ ምስል ነዉ።

    ድህነት ለሚነዳው የአፍሪካ አህጉር ማብራሪያዉ ምንድነው? ወደ ማንኛውም የአፍሪካ አገር በምትሄዱበት ጊዜ የምታዩት ነገር ተመሳሳይ ነው። የተከበብን እና የተወረርን ነን? የትኛውም ቦታ ብትሄዱ ወይም ምንም ነገር ብትሰሩ ከዚህ መውጣት አትችሉም።

    ለምሳሌ በቤተሰብ ላይ እርግማን ሲኖር አንድም ሴት ልጅ ልታገባ አትችልም። ቁመት ያላቸው፣ አጫጭር፣ መካከለኛ ወይም ጠቆር ያለ፣ ቆንጆ ወይም አስቀያሚ ቢሆኑም ውጤቱ አንድ ነው። ምንም ጋብቻ የለም! 

    የሰው ልጆች በላያቸው የሚያንዣብብ የሞት እርግማን አለባቸው። ሀብታም፣ ድሃ፣ ታዋቂ፣ አስፈላጊ ያልሆነ፣ አውሮፓዊ፣ አሜሪካ፣ አፍሪካዊ፣ ጥቁር ወይም ነጭ ብትሆን ሞት የሚጠብቅህ ጠላትህ ነው። ምንም ብትሆን ከዚህ ጠላት ማምለጥ አትችልም።

    እርግማንን ልታሸንፈው ከፈለግህ በዚህ መንገድ መረዳቱ አስፈላጊ ነው። ስንከበብ እንዴት መውጣት እንዳለብን የሚነግረን መጽሐፍ ቅዱስ ብቻ ነው። ትንሽ ከተማ በጦር ሠራዊት በተሞላ አንድ ኃያል ንጉሥ በተከበበ ጊዜ፣ ሞትና መደምሰስ የማይቀር ይመስላል። ማምለጫ የለም እና ከከተማ መዉጫ ምንም መንገድ የለም። ምንም ብታደርጉ፣ ውጤቱ አንድ ዓይነት ነው - ሞት!

    ተረግመሃል? ተከበሃል?

    በህይወትህ ውስጥ ምንም ዓይነት መዉጫ ያሳጣህ ሁኔታ ውስጥ እንዳለህ ይሰማሃል? የምትሰራው ነገር ሁሉ ወደ ውድቀትና ተስፋ መቁረጥ እየመራህ ነው? ምናልባት እርግማን እየሰራብህ ይሆናል። በጣም ብዙ ክርስቲያኖች ከአያታቸው ወይም ከቅድመ አያቶቻቸው እርግማን መኖሩን ለማወቅ ብዙ ጊዜአቸውን ያጠፋሉ። ይህ አስፈላጊ አይደለም። ቅድመ አያትህ በቤተሰብ ውስጥ እርግማን አምጥቶ እንደ ሆነ ለማወቅ ለምን ትጨነቃለህ? መጽሐፍ ቅዱስ በምድር ላይ እርግማን እንዳለ ይነግረናል። እርግማን በእርግጥ እውን ነው፤ በየቦታውም ይገኛል! የቱንም ያህል እምነት ቢኖርህም፣ በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ከተጻፈው በላይ አልፈህ አትሄድም። በቤተሰብህ ውስጥ እርግማን እንዳለ ለማወቅ ለመሞከር ጊዜህን ከማባከን ይልቅ አንድ እርግማን ሊኖር እንደሚችል እመን። ማድረግ ያለብህ ነገር ከተከበብክበት ሁኔታ ውስጥ እንዴት መዉጣት እንዳለብህ ማወቅ ነው። በምድር ላይ እንዳሉት አብዛኞቹ ሰዎች ምናልባት በዙሪያህ የተከበብክ ልትሆን ትችላለህ። መከበብ ምን ማለት እንደሆነ ከተረዳህ ከዚያ ለመውጣት ያስችልሃል።

    አሕዛብ ሁሉ ከበቡኝ፣ በእግዚአብሔርም ስም አሸነፍኋቸው፤

    መክበቡንስ ከበቡኝ፣ በእግዚአብሔርም ስም አሸነፍኋቸው፤ ንብ ማርን እንዲከብብ ከበቡኝ፣

    እሳትም በእሾህ ውስጥ እንዲነድድ ነደዱ፣ በእግዚአብሔርም ስም አሸነፍኋቸው።

    መዝሙር 118:10-12

    ቤተሰቦችህ በምድር ላይ እንዳሉት ሌሎች ክፉ ቤተሰቦች በተመሳሳይ ክፉዎች እንደሆኑ ላረጋግጥላችሁ እችላላችሁ። በአንተ ቤተሰብ ዉስጥ እንደ ማንኛውም ሌላ ቤተሰብ መጥፎ ሰዎች፣ ኃጢአተኞች፣ ጠንቋዮች እና አስማተኞች በእኩል ደረጃ እንዳሉ እርግጠኛ ነኝ። በአንድ ሰው ቤተሰብ ውስጥ ጠንቋዮች እና አስማተኞች አሉ ብለህ እንደምታስብ እንደዚያዉ ሌሎችም በአንተ ቤትም ጠንቋይና አስማተኛ እንዳለ ያስባሉ። የመርገሞችን እና የጥንቆል መገኛ ምንጮችን ፍለጋ ጊዜህን ማባከን ማቆም አለብህ። የሆነ ቦታ ላይ እርግማን እየሰራ እንደሆነ እንድታውቅ መመከር አይጠበቅብኝም።

    ከፀሐይ በታች እርግማን መኖሩን መጽሐፍ ቅዱስ በግልፅ ይነግረናል። በጋና፣ ናይጄሪያ፣ ሮማኒያ፣ አሜሪካ፣ እንግሊዝ፣ ጀርመን ወይም ማሌዥያ ብትኖርም ከመብላትህ በፊት በላብህ መልፋት ይኖራል። ተመሳሳይ ሞት እና ከንቱ ፍርሀት በሁሉም ቦታ መገኘቱን ትገነዘባለህ። ከዚህ ዓለም መሸጋገራችሁን ከሚያሳዩ ታላላቅ ምልክቶች አንዱ እርግማን እና የእርግማን ዉጤት አለመኖር ይሆናል። በመንግስተ ሰማያት ይህ በጣም ዝነኛ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅስ …ከእንግዲህም ወዲህ መርገም ከቶ አይሆንም። (ራዕይ 22፡3) የሚለው ሙሉ በሙሉ ይፈጸማል። ስለ እርግማን ስታስብ ብዙ ርቀህ አትሂድ። እርግማን በሁሉም ቦታ ይገኛል። በምድር ላይ በምናደርገው ማንኛውም ነገር ሁሉ ታላቅ ተስፋ መቁረጥ እና የባዶነት ስሜት ይፈጥራል። ጠቢቡ ሰሎሞን በምድር ላይ ታላቅ እርግማን እንደነበረ አውቋል። እንደ እውነቱ ከሆነ፣ እርግማን አንድ ቦታ ላይ እየሰራ መሆኑን ለመለየት ጥበብ ያስፈልጋል።

    ሰሎሞን በዚህ ምድር ላይ ያለን እርግማን ገልጿል።

    ሰሎሞን ሁሉ ከንቱ ነው ሲል ምን ማለቱ ይመስልሃል? እሱ ያደረጋቸው ነገሮች ሁሉ ተመሳሳይ ፍፃሜ ነበራቸው፤ ከንቱ፣ ዋጋ የለሽነት፣ ባዶነት፣ ቅጣትና ብስጭት እና ግራ መጋባት! በምድር ላይ ህይወት የተስፋ መቁረጥ፣ ከንቱነት እና ባዶነት እርግማን አላት። አዳም የተቀጣዉ ቅጣትም እጅግ የከፋ ነበር። ሰሎሞን ብዙ የተለያዩ ነገሮችን በማድረግ እርግማንን ለማምለጥ ሞክሮ ነበር። ሰሎሞን ምንም ቢያደርግ ውጤቱ አንድ ነበር - ከንቱነት! ሰሎሞን የፈተናቸውን የተለያዩ ነገሮች እንመልከት።

    ሰሎሞን እንዲህ አለ፣ ኑ፣ እንደሰት። በህይወት ያሉ 'መልካም ነገሮች' እንፈልግ። ነገር ግን ይሄም ቢሆን ትርጉም የማይሰጥ እንደ ሆነ አወቀ። እሱም እነሆ ሳቅን እብድ ነህ አለ። ደስታን ለመፈለግ የሚደረገው ሩጫ ምን ይጠቅማል? "ብዙ ካሰበ በኋላ፣ በወይን ጠጅ ለመደሰት ወሰነ። አሁንም ጥበብን እየፈለገ፣ ሞኝነትን ያዘ። በዚህ መንገድ፣ በዚህ አጭር የህይወት ጊዜ ውስጥ ሰዎች የሚያገኙትን ብቸኛ ደስታ ለማግኘት ሞክሯል።

    ሰሎሞን ለራሱ ግዙፍ ቤቶችን በመስራት እና ቆንጆ የወይን ተክሎችን በመትከል የህይወትን ትርጉም ለማግኘት ጥረት አድርጓል። የተለያዩ የፍራፍሬ ዛፎችን በመትከል አትክልቶችንና መናፈሻዎችን አዘጋጀ። እርሱ ብዙ የተንሰራፉትን ዛፎች ለማጠጣት የውሃ ማጠራቀሚያዎችን ገነባ። ወንድና ሴትን ባሪያዎች ገዛ እና ሌሎችም በቤቱ ውስጥ ተወለዱ። ደግሞም ከእሱ በፊት በኢየሩሳሌም ከነበሩት ነገሥታት ሁሉ ይልቅ ታላቅ የሆነ የፍየሎችና የከብቶች መንጋ ነበረው።

    ሰለሞን ከፍተኛ መጠን ያለው ብርና ወርቅ እንዲሁም ብዙ ነገሥታትና ግዛቶች ወደ ራሱ ሰብስቧል። እርሱ ወንዶችም ሆነ ሴቶችን በጣም ጥሩ የሆኑ ዘፋኞችን ቀጠረ፣ ብዙ ውብ ሚስቶችና ቁባቶች ነበሩት። አንድ ሰው የሚፈልገው ነገር ሁሉ ነበረው! 

    ስለዚህም እርሱ ከእርሱ በፊት በኢየሩሳሌም ይኖሩ ከነበሩት ሁሉ ይልቅ ታላቅ ነበረ፤ ጥበቡም አልጣለዉም ነበር። የሚፈልገውን ነገር ሁሉ ይወስዳል። እርሱ ምንም ዓይነት ደስታ አላጣም! 

    ሰለሞን ጠንክሮ በመሥራት ከፍተኛ ደስታ አግኝቷል። ነገር ግን ለማከናወን እጅግ በጣም ከፍተኛ ጥረት ያደረገውን ሁሉ ሲመለከት፣ ነፋስን እንደማሳደድ ሁሉ ዋጋ ቢስ ነው። በየትኛውም ቦታ ምንም ፋይዳ ያለዉ ነገር የለም። እርሱ ያንን በትክክል ገልጾታል፤ ሁሉም ባዶ እና ከንቱነት ነው።

    ከፀሐይ በታች በደከመበት ድካም ሁሉና በልቡ አሳብ የሰው ጥቅም ምንድር ነው? ዘመኑ ሁሉ ኀዘን፣ ጥረትም ትካዜ ነው፤ ልቡም በሌሊት አይተኛም፤ ይህም ደግሞ ከንቱ ነው።

    መክብብ 2:22-23

    እርግማን እየሰራ እንደሆነ ስታውቅ ጥሩ ነገር ነው። ይህ ለምንድ ነው? ስለ እርግማን ስታውቁ፣ እንዳይሰራባችሁ ተጽዕኖውን ለመከላከል ጥበብ ለማግኘት መጸለይ ትችላላችሁ። በዚህ መጽሐፍ ውስጥ ስለ ብዙ መርገሞች እና ምን እንደሚመስሉ ትማራላችሁ። የእግዚአብሔር ጥበብ በዚህ ህይወት ውስጥ እርግማንን እንድትቋቋሙና እንድታሸንፉ ሊያደርግ ይችላል።

     ምዕራፍ 3 

    ዓለም አቀፋዊ መርገሞች

    ከእንግዲህም ወዲህ መርገም ከቶ አይሆንም። የእግዚአብሔርና የበጉም ዙፋን በእርስዋ ውስጥ ይሆናል፣ ባሪያዎቹም ያመልኩታል፣ ፊቱንም ያያሉ፣

    ራእይ 22:3

    በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ በግልጽ የተቀመጡ ሦስት የመርገም ዓይነቶች አሉ።

    1. ዓለም አቀፋዊ መርገሞች

    2. የመጽሐፍ ቅዱስ መርገሞች

    3. ለአንድ ሰው የተለዩ መርገሞች

    ዓለም አቀፋዊ መርገሞች ከመጀመሪያው ጀምሮ በምድር ላይ የመጡ እና ያለማቋረጥ እና ቀጣይነት ባለው ሁኔታ በመላው ዓለም ላይ ተጽዕኖ ያሳደሩ መርገሞች ናቸው።

    የመጽሐፍ ቅዱስ መርገሞች በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የተረገመ ተብሎ የተጠራው ሁላችንም የምናውቃቸው የተለመዱ ነገሮች ናቸው። የተወሰኑ መስመሮችን የሚያልፍ ማንኛውም እንቅስቃሴ ወይም ድርጊት እነዚህን የመጽሐፍ ቅዱስ መርገሞች ያስከትላል። በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ በሙሉ፣ እነዚህ የመጽሐፍ ቅዱስ መርገሞች ሲሰሩ ምሳሌዎችን ታገኛለህ።

    ለአንድ ሰው የተለዩ መርገሞች በግለሰቦች ላይ በተደረገ ክፉ ስራ ምክንያት በሌሎች ግለሰቦች የሚነገሩ መርገሞች ናቸው። ምክንያት የሌለው እርግማን አይመጣም፤ ነገር ግን ምክንያት ያለቸው መርገሞች ግን ኃይል ይኖራቸዋል!

    እንደሚተላለፍ ድንቢጥ ወዲያና ወዲህም እንደሚበርር ጨረባ፣ እንዲሁ ከንቱ እርግማን በማንም ላይ አይደርስም።

    ምሳሌ 26:2

    በዚህ እና በቀጣዮቹ ሁለት ምዕራፎች ውስጥ፣ ዓለም አቀፋዊ መርገሞችን፣ የመጽሐፍ ቅዱስ መርገሞችን እና ለአንድ ሰው የተለዩ መርገሞችን እንመለከታለን።

    ዓለም አቀፋዊ መርገሞችን

    1. የወንዶች እርግማን

    አዳምንም አለው። የሚስትህን ቃል ሰምተሃልና፣ ከእርሱ እንዳትበላ ካዘዝሁህ ዛፍም በልተሃልና ምድር ከአንተ የተነሣ የተረገመች ትሁን፤ በሕይወት ዘመንህም ሁሉ በድካም ከእርስዋ ትበላለህ፤ እሾህንና አሜከላን ታበቅልብሃለች፤ የምድርንም ቡቃያ ትበላለህ። ወደ ወጣህበት መሬት እስክትመለስ ድረስ በፊትህ ወዝ እንጀራን ትበላለህ፤ አፈር ነህና፣ ወደ አፈርም ትመለሳለህና።

    ዘፍጥረት 3:17-19

    2. የሴቶች እርግማን

    ለሴቲቱም አለ። በፀነስሽ ጊዜ ጭንቅሽን እጅግ አበዛለሁ፤ በጭንቅ ትወልጃለሽ፤ ፈቃድሽም

    Enjoying the preview?
    Page 1 of 1