Discover millions of ebooks, audiobooks, and so much more with a free trial

Only $11.99/month after trial. Cancel anytime.

ውበት አውሬው እና መጋቢው
ውበት አውሬው እና መጋቢው
ውበት አውሬው እና መጋቢው
Ebook331 pages2 hours

ውበት አውሬው እና መጋቢው

Rating: 0 out of 5 stars

()

Read preview

About this ebook

ለመጋቢዎች እና ለመጋቢዎች ሚስቶች የተለየው መጽሐፍ በመጨረሻ ይኸው መጣ! መጋቢዎች ወይም የመጋቢዎች ሚስቶች ካልሆናችሁ ይህ መጽሐፍ አይመለከታችሁመ! ይህን ምጽሐፍ ለማንበብ መስፈርቱን ካሟላችሁ እግዚአብሔር በዚህ ሃሳብን ከውስጥ በሚፈትሸው መጽሐፍ ወስጥ ይናገራችሁ። በየገጾቹ ሚስቶች በመጋቢዎች ህይወት ውስጥ የሚጫወጡት ሚስጥራዊ ሚና ይገለጣል። በየግጾቹ እየታነጻችሁ ወደ በረከታቸሁ ይምሩቿሁ።

Languageአማርኛ
Release dateJan 16, 2019
ISBN9781641357913
ውበት አውሬው እና መጋቢው
Author

Dag Heward-Mills

Bishop Dag Heward-Mills is a medical doctor by profession and the founder of the United Denominations Originating from the Lighthouse Group of Churches (UD-OLGC). The UD-OLGC comprises over three thousand churches pastored by seasoned ministers, groomed and trained in-house. Bishop Dag Heward-Mills oversees this charismatic group of denominations, which operates in over 90 different countries in Africa, Asia, Europe, the Caribbean, Australia, and North and South America. With a ministry spanning over thirty years, Dag Heward-Mills has authored several books with bestsellers including ‘The Art of Leadership’, ‘Loyalty and Disloyalty’, and ‘The Mega Church’. He is considered to be the largest publishing author in Africa, having had his books translated into over 52 languages with more than 40 million copies in print.

Related to ውበት አውሬው እና መጋቢው

Related ebooks

Reviews for ውበት አውሬው እና መጋቢው

Rating: 0 out of 5 stars
0 ratings

0 ratings0 reviews

What did you think?

Tap to rate

Review must be at least 10 words

    Book preview

    ውበት አውሬው እና መጋቢው - Dag Heward-Mills

    ክፍል 1

    ማስጠንቀቂያ

    ምዕራፍ 1

    ማስጠንቀቂያ፡ በአገልግሎት ያለ ትዳር ከተለመደው ትዳር የተለየ ነው

    በውኑ በይሁዳ ምድርና በኢየሩሳሌም አደባባይ ያደረጉትን የአባቶቻችሁን ክፋት፥ የይሁዳንም ነገሥታት ክፋት፥ የሚስቶቻቸውንም ክፋት፥ የእናንተንም ክፋት፥ የሚስቶቻችሁንም ክፋት ረስታችሁታልን?

    ኤርሚያስ 449

    አገልጋይ ከልሆንክ ይህን መጽሐፍ ላንተ አይደለም። አገልጋይ ካልሆንክ ይህን መጽሐፍ ማንበብ አትቀጥል። አገልጋይ ከልሆንክ እባክህ እዚህ ላይ አቁም። አገልጋይ ሳትሆን መንበብን ከቀጠልህ ያልተረዳህውን ነገር ትተቻለህ።

    አገልጋይ ካልሆን ስለጋብቻ የሚያስተምሩ ሌላ መጽሐፍ ፈልግ። ህይወትህን በታላቅ ሁኔታ የሚዱ ስለጋብቻ የተፃፉ ብዙ ጥሩ መጽሐፎች አሉ። ስለ ጋብቻ ጥሩ መጽሐፎች እንዴት ማግኘት እንደምትችል መረጃ ማግኘት ከፈለግህ እባክህ በቅርብ ያሉትን የመጽሐፍት መደብር ጠይቅ።

    መልካም ትዳር የለው መሆን በረከት ነው እንዲሁም ድንቅ በረከቶች የሆኑ መልካምና ጥሩ ትጋሮችን አውቃለሁ። የመልካም ጋብቻ በረከቶች በጥቂቱ ምንድን ናቸው ?

    1.   መልካም ጋብቻ በረከት ነው ምክንያቱም ሁለት ከአንድ ይሻላል። ከዚህ ሁኔታ ጋር የሚሄድ በርካታ ጥቅሶች አሉ።

    ድካማቸው መልካም ዋጋ አለውና አንድ ብቻ ከመሆን ሁለት መሆን ይሻላል።  ቢወድቁ አንዱ ሁለተኛውን ያነሣዋልና፤ አንዱ ብቻውን ሆኖ በወደቀ ጊዜ ግን የሚያነሣው ሁለተኛ የለውምና ወዮለት።  ሁለቱም በአንድነት ቢተኙ ይሞቃቸዋል፤ አንድ ብቻውን ግን እንዴት ይሞቀዋልአንዱም አንዱን ቢያሸንፍ ሁለቱ በፊቱ ይቆማሉ፤ በሦስትም የተገመደ ገመድ ፈጥኖ አይበጠስም።

    መክብብ 49-12

    2.  መልካም ጋብቻ በረከት ነው ምክንያቱም ጥንዶቹ አንድ ሰው ሊሰራው የሚችለውን በአስር እጥፍ መስራት ይችላሉ።

    እርሱ አምላካቸው ካልሸጣቸው፥ እግዚአብሔርም አሳልፎ ካልሰጣቸው፥ አንድ ሰው እንዴት ሺህን ያሳድድ ነበር? ሁለቱሳ እንዴት አሥሩን ሺህ ያሸሹ ነበር

    ዘዳግም 3230

    3. መልካም ጋብቻ በረከት ነው ምክንያቱም ባለትዳር በእግዚአብሔር ፊት ታላቅ ሞገስ አለው።

    ሚስት ያገኘ በረከትን አገኘ፥ ከእግዚአብሔርም ሞገስን ይቀበላል።

    ምሳሌ 1822

    ምንም እንኳን መልካም ጋብቻ በረከት ቢሆንም፣ የተለያዩ ትዳሮች አሉ። ጥንዶቹ በረከት የመሆንን አላማ በማሳካት ፍፃሜያቸውን የሚያጠናቅቁት ግን ሁሉም ጋብቻዎች አይደሉም።

    የሐሰት ጋብቻዎች የሚኖሩበት ምክንያት የእውነተኛና መልካም ጋብቻዎች መኖር ነው።

    ይህ መጽሐፍ ስለ አንዳንድ ለየት ስላሉ ጋብቻዎች የሚናገር ነው። ይህ መጽሐፍ ለአገልጋዮች እና ስለትዳራቸው እንጂ ለተራ ክርስቲያኖች ወይም ለማያምኑ ሰዎች አይደለም። መጋቢ ወይም የመጋቢ ሚስት ካልሆንሽ ይህ መጽሐፍ አይመለከታችሁም።

    በአብዛኛው የጋብቻ መጽሐፎች አገልጋዮችን ትክክለኛውን ሰው እንዳላገቡ እንዲሰማቸው የሚያደርጉ ናቸው ምክንያቱም ጋብቻው እንደጸሀፊው ያማረ አይደለም።

    በመቀጠልም የሰመረና መልካም ጋብቻ ያላቸውም አገልጋዮች እየተፋቱ መሆኑን ሲሰሙ ይደነግጣሉ።

    ይህ መጽሐፍ ስለተለመደው ዓይነት ጋብቻ አይደለም።  ይህ መጽሐፍ ሚዛናዊ የሆነ በሁለቱም አቅጣጫ ስለትጋር የሚያወራ አይደለም። ስለ ባል እና ስለሚስት መፃፍ እችል ነበር። ስለ ስኬታማ ጋብቻም መፃፍ እችል ነበር። እንዲያውም ጥንዶቹ በትዳራቸው ውስጥ ስለሚገጥማቸው ችግር እንዴት መወጣት እንዳለባቸው መፃፍ እችል ነበር። ያምሆቡ ግን በዚህ መጽሐፍ የማደርገው ያንን አይደለም። እኔ የመረጥኩት በአብዛኛው ሰዎች የማይነጋገሩበትን አርዕስት ነው።

    ይህ መጽሐፍ ስለሚስቶች ክፋት ነው። እኔ ይህንን መጽሐፍ የምጽፈው በብዙ ውብ ሚስቶች ውስጥ ስለተሸሸገው ክፋት ነው። ስለትዳር የሚያወራ መልካም መጽሐፍ ከፈለግህ፣ ይህ መጽሐፍ ያ ስላልሆነ እባክህ ሌላ ፈልግ። ይህ መጽሐፍ፣ ስለ ውበት፣ በአንዳንድ መጋቢዎች ሚስቶች ውስጥ ስላለ አውሬነት እና መጋቢው ከእነርሱ ጋር ስላለው ተግዳሮት ነው። ብዙ መጋቢዎች ቆንጆዎችን ያገባል ! ነገር ግን ብዙ ቆንጆዎች ደግሞ አውሬዎችም ናቸው !

    ብዙ ሰዎች ደግ እና መልካም መሳይ ሚስቶች ውስጥ ክፋት ይኖርባቸዋል ብለው ለመገምገም እንደማይደፍሩ አውቃለሁ። እንደተናገርኩትም ሚዛኑን የጠበቀ ሁለቱንም ወገን ያማከለ የትዳር ውይይት ላማድረግ አላማዬ አይደለም። እየፈለግህ ያለህው ሚዛኑን የጠበቀ ስለ ወንዶች መልካም እና መጥፎ ጎን ወይም ደግሞ ስለ ሴቶች መልካም እና መጥፎ ጎን ውይይት ከሆነ እባክህ ማንበብ አቁም። ይህ ስለ ሚስቶች ክፋት፣ በተለይም ስለ አንዳንድ የክርስቲያን ሚስቶችና ስለ አገልጋዮች ሚስቶች ክፋት ነው።

    ነብዩ ኤርምያስ ሚስቶች በይሁዳ እና በእየሩሳሌም ውስጥ ስፈጸሙት ክፋት አዝኗል። እነዚህ ሚስቶች የማያምኑ አልነበሩም ነገር ግን ከእስራኤል ቤት ወገኖች ነበሩ። ኤርምያስ ይናገር የነበረው እነዚህ ሚስቶች የነበረው ክፋት የጣዖት አምላኪነት እና በእግዚአብሔር ላይ አመጸኛ ስለመሆን ነበር። እየጻፍኩልህ ያለው ዓይነት ክፋት አንዳንድ የአገልጋይ ሚስቶች በእግዚአብሔር ላይ ስለሚፈፅሙት አመጽ ነው።

    በእርግጥም ይህ መጽሐፍ ለአገልጋዮች እና ለሚስቶቻቸው ነው። ይህ መጽሐፍ የተሰጡ ክርስቲያኖች እና የእግዚአብሔር ሰዎች ስለሚያልፉባቸው የትዳር ጎዳናዎች የሚገልጽ ነው። ይህ መጽሐፍ አገልጋች ሊያወሩት ስለማይችሉት ነገር ግን በትዳር ውስጥ እራሳቸውን ስለሚያገኙበት የጋብቻ ሁኔታዎች ነው።

    ብታገባ ግን ኃጢአት አትሠራም ድንግሊቱም ብታገባ ኃጢአት አትሠራም፤ ነገር ግን እንዲህ በሚያደርጉ በሥጋቸው ላይ መከራ ይሆንባቸዋል፥ እኔም እራራላችሁ ነበር።

    1ኛ ቆሮንቶስ 728   

    ጳውሎስ የሚያገቡ ሰዎች በስጋቸው ላይ መከራ እንደሚሆንባቸው ተብይዋል። ምናልባም ያላገባውም ለዚያ ይሆናል። በነገራችን ላይ ይህንን መጽሐፍ ስጽፍ ስለወንዶች ደካማ ጎን ምንም ሳላውቅ ቀርቼ አይደለም። አውቃለሁ ! እንደዲሁም ደግሞ ይህንን መጽሐፍ የምጽፈው ስለ ሴቶች ደካማ ጎን(ድክመትም) ለመፃፍ ፈልጌም አይደለም። የሴቶች ሚና በአገልግሎት ውስጥ እና የሾምኳቸውንና በአገልግሎት ውስጥ ወደ ላይ ከፍ ያደረኳቸውን ሴቶች፣ ቅባት እና ጥበብ አምንበታለሁ። ምንም እንኳን ሌሎች አገልጋዮች ቢኖሩም እንደኔ በአገልግሎት ውስጥ ብዙ ሴቶችን ለይቶ ለአገልግሎት የሾመን ሰው አላውቅም። ማንበብህን ስትቀጥል ለምን የሴትን መጥፎ ጎን ከወንድ መጥፎ ጎን ለምን ሚዛናዊ እንደማላደርግ ታስተውላለህ። ምክንያቱ ቀላል ነው፣ የመጽሐፉ አላማ ያ አይደለምና! በትዳር ውስጥ ያለውን የወንዶችን አስከፊ ኃጢአት ብጽፍ፣ እግዚአብሔር የሰጠኝን መልዕክት በሙሉ ላጠፋው እችላለሁ።ያንን አድርጌው ቢሆን ይህ መጽሐፍ ከዚህ ይበልጥ ነበር፤ እንዲሁም እንዳተ ዓይነት ብዙ የማያነቡ ሰዎች ለማንበብም አይሞክሩትም ነበር።

    ይህ መጽሐፍ ሴቶች በአገልጋዮች ህይወት ውስጥ የተጫወቱትን ምስጢራዊ ሚና ለመግለጽ ያለመ ነው። በትዳር እና በአገልግሎት ውስጥ ሴቶችን እናመሰግናለን እንዲሁም ስለሚጫወቱት ሚና አመስጋኞች ነን። ካለሴቶች እርዳታ በእግዚአብሔር ስራ ላይ ብዙ ውጤት አናመጣም። እኔ የማምነው ለቤተክርስቲያን እድገት አንደኛው ምስጢር ከሴቶች ጋር መስራት እና ለሴቶች እውቅና መስጠት ነው።

    ሴቶች ይመሰገናሉ ነገር ግን ስለ ተቃራኒው መንገዳቸው የተነገረው ጥቂት ነው ምክንያቱም ማንም መጥፎ ሆኖ መታየትን ስለማይገልግ ወይም በትዳራቸው ውስጥ ማንኛውም ችግር እንዳለ እንዳለ እንዳይታው ነው። ነገር ግን ላንተ የሚጠቅመውን ማንኛውንም ነገር ካንተ መሰወር አልፈልግም።

    …  ከሚጠቅማችሁ ነገር አንዳች ስንኳ አላስቀረሁባችሁም።

    የሐዋርያት ስራ 2020

    ቁንጅናው እውነት ነው ነገር ግን አውሬውም እውነት ነው ! አገልግሎትን ስለሚያጠፉ ሴቶች የተነገረው ትንሽ ነው። የኛ መጽሐፍ፣ መጽሐፍ ቅዱስ ሴቶች ይህንን ዓለም ለማጥፋት ስለሚጫወቱት ሚና ዝም አላለም። ከሔዋን የተነሳ የአዳም ህይወት እና አገልግሎት ወድሟል። ከሔዋን የተነሳ የሰው ዘር በሙሉ ወደ ጭለማ እና ችግር ውስጥ ተጥሏል።

    ብዙ መጋቢዎች በውበት ተስተካክለው ከተሰሩት ሚስቶቻቸው የተነሳ  ብዙ መጋቢዎች በጭንቀት፣በጭለማ እና በችግር ውስጥ ይገኛሉ።

    የዚህ መጽሐፍ ምክንያቱ አንዳንድ ሰዎች ያሉበትን እውነተኛ ገጽታ ለማሳየት ነው።

    ሌላኛው የዚህ መጽሐፍ ምክንያቱ ውበትን ለመመረጥ በዝግጅት ላይ ያሉትን ለመርዳት ነው። ውበታቸው በቀላሉ ወደ አውሬነት ሊቀየር እንደሚችል እነርሱን ማሳወቅ አስፈላጊ ስለሆነ ነው ! ይህ መጽሐፍ ሁሉም ውብ ሴቶች ወደ አውሬነት እንዳይቀየሩ ይረዳል ብዬ ተስፋ አደርጋለሁ ! 

    ጆን ዌስሊ ብቸኛ በነበረ ጊዜ፣ ታመመና በሃላ ሚስቱ ከሆነችው አንዲት ሴት ጋር ቆይቶ ነበር። እንዴት ቆንጆ፣ እንዴት ጨዋ እና እንዴት መልካም እንደሆነች ይናገር ነበር። የተናገረቻቸው የማይረሱ ነበሩ። ድምጽዋ ለስላሳ ነበር። ጆን ዌስሊ ሊቆጣጠረው ባልቻለው አጽናኙ ፍቅሯ ተስቧል ! እርሱም ሲናገር ሞሊ፣ የወደፊቱ ሚስቱ መቼም የሚያስፈልገውን ነገር እንደምትሰጠው ማረጋገጫ ሰጠችው። ስለእርሷም  ሊዘነጋው ስለማይችለው ስሜቷ ይናገር ነበር።የእንግሊዘኛው (inviolable) የሚለው ቃል እንዲያውም እኔ ልተረጉመው ከምችለው በላይ ነው። ኤይ!! ሊዘናጋ የማይችል ስሜት! ጆን ዌስሊ የእርሱን ቆንጆ እና ፍቀረኛ ሞሊን ከመጋባታቸው በፊት የተናገራት መጥቀስ እፈልጋለሁ።

    ጆን ዌስሊም እንዲህ አለ፣ አጅግ ብርቱ እና ሊዘነጋ ስለማይቻለው ስሜት ቃላት ሊሰጡ የሚችሉትን ማረጋገጫ ሁሉ ነበረኝ 

    ነገር ግን አንድ ቀን ከብዙ የትዳር ዓመታት በሃላ እርሷን ለመግለጽ የተጠቀመው የተለየ ቃላቶች ነበር። ቆንጆዋ አውሬ ሆነችበት። አንድ ቀን ሚስቱ ከቤት እየዋጣች ትጮህ ነበር። ብርቱ እና ሊዘነጋ የማይችል ፅኑ ስሜት አለት የተባለችው ሴት ነበረች። በሩን አልፋ ወጥታ ስትሄድ እንዲህ ብሏታል እንግዲህ ወዲህ ፈፅሞ ክፉ ፊትሽን አላየውም ብዬ ተስፋ አደርጋለህ 

    እንግዲህ ወዲህ ፈፅሞ ክፉ ፊትሽን አላየውም ብዬ ተስፋ አደርጋለህ የሚለው የጆን ዌስሊ ንግግር በእርሱ ቆንጆ ውስጥ አውሬነትን ካየ በሃላ ነበር ። ይህ አንድ መጋቢ ቆንጆን አግብቶ ወደ አወሬ የተለወጠችበት የተለመደ ምሳሌ ነው!

    በእርግጥም ይህ መጽሐፍ ሊቃና በማይችል በትዳር ሁኔታ ውስጥ ያሉ ሰዎችን እጅ እንዲያበረታታ ታስቦ የተዘጋጀ ነው። ይህ መጽሐፍ አገልጋዮች እያለፉበት ላለውን ሁኔታ መረዳትን በመስጠት ፍቺን ለመታገድ እንደሚረዳ ተስፋ አደርጋለሁ።

    በዚህ መጽሐፍ ውስጥ ብዙዎች ሊዛመዱት የሚችሉትን ነገሮች እንደሚያገኙ እርግጠኛ ነኝ። መልካሙን የእምነት ገድል ለመጋደል በዚህ መጽሐፍ ውስት የሚገኙትን እውቀት፣ መረዳት እና ጥበብ ተጠቀምበት። ትዳር አንዱ የምንጋፈጠው ፈተና ነው በስኬትም ልንወጣው ይገባል! ለአንዳንድ ሰዎች ትዳር ትልቁ ምቾታቸው ነው! ለአንዳንዶች ደግሞ ትዳር ትልቁ የሚሸከሙት መስቀላቸው ነው! አንዳንድ ሰዎች እጅግ መልካም ትዳር አላቸው። ነገር ግን መልካም ልምምድ የሚኖራቸው ሁሉም አገልጋዮች አይደሉም ወይም ስለትዳራቸው መልካም ታሪክ የሚተርኩት ሁሉም አይደሉም። በእርግጥም ትዳራቸው ውጊያ እንደሆነ የሚገልጹ ብዙ አገልጋዮች አሉ።

    ብዙ ትላልቅ የእግዚአብሔር ሰዎች እጅግ መልካም ስለሆነው ትዳራቸው ሲናገሩ ሌሎች ክርስቲያኖችን እና መጋቢዎችን በሚያሸማቅቅ እና ግራ በሚያጋባ መንገድ ነው። ሌሎች አገልጋዮች ስለ ጋብቻቸው ገለፃ ሲሰሙ ይሸማቀቃሉ። ለራሳቸውም ዋው! የእኔን ትዳር ከእነዚህ ከተባረኩት ጋር ለመዌየት መድፈርም የለብኝም ይላሉ። (ይህ የሚሆነውም መጋቢዎች የአገልጋዮች ኮስፈረንስ ላይ ሲካፈሉ እና በሺዎች የሚቀጠሩ አባላቶች ስላላቸው ትላልቅ ቤተክርስቲያኖች የሚያስደናቂ ታሪኮች በሚሰሙበት ጊዜ ነው።) ብዙ ተራ መጋቢዎች ይሸማቀቃሉ ምክንያቱም ወደ በቤተክርስቲያናቸው የሚመጡ በሺህ የሚቆጠሩ አባላት የላቸውም።

    መጋቢዎች ከዚህ ፍጸም-መስል ትዳሮች የሚያስደንቅ ንግግሮችን ይሰማሉ።

    ባለቤቴ ከዓለም አንደኛ ቆንጆ ሴት ናት

    ህይወቴን እና አገልግሎቴን ከሚስቴ የተነሳ ነው !

    ሚስቴ ባትኖር የት እሆን እንደነበር አላውቅም !

    ‘ካላንቺ’ ‘እኔ’ የሚባል ነገር አይኖርም ነበር !

    እንደ አንቺ አይነት የትም አይኖርም! አንቺ ልቤን እንደምትነኪኝ ማንም አይነካኝም!

     ካለ ሚስቴ የትም መሄድ አልችልም !

    ትልቋ ረዳቴ፣ ጓደኛዬ እና ደጋፊዬ ባለቤቴ ናት! 

    ከሚስቴ ጋር በጭራሽ ተጨቃጭቄ አላውቅም!

    ሚስቴን በቀን አስር ጊዜ ‘እወድሻለሁ’ እላታለሁ !

     ካለ ሚስቴ አንድ ቀን እንኳን መኖርን ላስበው አልችልም!

    እኔና ባለቤቴ ሁልጊዜ የምንተኛው ተቃቅፈን ነው !

    በዚህ ዓለም ቅርቤ የምላት ጓደኛዬ ሚስቴ ነች !

    ባለቤቴን ስትናፍቀኝ ፎቶዋን እሰማለሁ። ነገር ግን ሳገኛት እውነተኛዋን እስማታለሁ !

    ሚስቴ በዓለም ላይ ካሉ ሁሉ ሴቶች ወቧ ሴት እርሷ ነች፣የነፍሴ ቁራጭ፣ የህይወቴ አጋር፣ ጓደኛዬ፣ ደስታዬ፣ ወዳጄ እና የልቤ ማረፊያ !

    ስለ መልካም ትዳር ውጤት ስጡ ቢባል፣ እኔ 99 ከመቶ እሰጣለሁ !

    ዋው ! እነዚህ የሚገራርሙ አባባሎች ናቸው ! ከላይ የተጠቀሱትን ሁሉም ቢለው ምኞቴ ነው። በአገልግሎት ውጤታማ ለመሆን እንደነዚህ ዓይነት ትዳሮች ያስፈልጉን ነበር።

    ነገር ግን ሁሉም ያገቡ አገልጋዮች ያሏቸው ልምምዶች ይሄ አይደለም ! እንዴት አውቃለሁ ? የማውቀው በአገልግሎት ውስጥ ለብዙ ዓመታት ስለነበርኩ ነው እንዲሁም በሺህ የሚቆጠሩም መጋቢዎችን አውቃለሁ። በመጋቢዎች መካከል ያለውንም የፍቺ ቁጥርንም ስለማውቅ ከዚህ የተነሳም ደግሞ አውቃለሁ። መጨረሻው ፍቺ ሊያደርጉ እንደሆነ ሊናገሩ ብቻ ሲቀራቸው፣ ብዙ መጋቢዎች ከፍቅር ሁሉ ታላቁ አድርገው ትዳራቸውን በመሳል ከላይ ያሉትን አባባሎች ተናግረዋል።

    ለአንዳንድ ሰዎች እውነታው ምናልባትም የእነዚህ ንግግሮች ተቃራኒው ነው። እንደዚህ ብለው መናገርን የሚመርጡ አንዳንድ መጋቢዎች እነዚህ ናቸው፤

    ባለቤቴ ከዓለም ቆንጆዋ ሴት ናት ነገር ግን ከእርሷ ጋር መኖር ቀላል አይደለም !

    ከሚስቴ ነፃ መውጣት ምኞቴ ነው !

    የአገልግሎቴና የህይወቴ ትልቁ ተቃዋሚዋ ሚስቴ ናት !

    በህይወቴ በኃይለኛው የምትከሰኝ እና የምታቃጥለኝ ሚስቴ ናት !

    ለብዙ ወራት ወሲብ ፈጽመን አናውቅም !

    ካለፈው ወር ጀምሮ እኔና ሚስቴ አውርተን አናውቅም !

    መዋሸት ስለማልፈልግ ሚስቴን ‘እወድሻለሁ’ አልላትም !

    ሚስቴ የማትኖርበትን ቀን እናፍቃለሁ !

    እኔና ሚስቴ በየምሽቱ የምንተኛው በአልጋው ጫፍና ጥግ ነው ! 

    እኔና ሚስቴ እንደድሮው መቀራረብ የለንም !

    ሚስቴ አትናፍቀኝም። ፎቶዋን ሳይ በልቤ ውስጥ ካለው ሐዘን የተነሳ አነባለሁ !

    በህይቴ ውስጥ ካጠፋሁት ጥፋት ትልቁ ትዳሬ ነው !

    ሌላ ሚስት ብትኖረኝ ኖሮ፣ በአገልግሎቴ ብዙ ስኬት ይኖረኝ ነበር

    ጋብቻን በተመለከተ ብዙዎቻችን የምንመስለው አፍሪካዊ የባህል መድሃኒት አዋቂዎችን ነው። ለምን እምዲህ አልኩኝ? አፍሪካዊ መድሃኒት አዋቂ ምንም ዓይነት ችግር ይሁርህ ሁሉንም የሚፈውሰው በአንድ መድሃኒት ነው።  የዚህ የቅጠል በጣሽ መድሃኒት የሚፈውሳቸው ነስቶች፣ የአይን ህምም፣ የጥርስ፣ የደም ግፊት፣ ስኳር፣ ካንሰር፣ ሽፍታ፣ ስም፣ የወገብ ህመም፣ ስንፈተ ወሲብ፣ድካም እን የመሳሰሉትን ሁሉ ነው።ይህ የባህል ሐኪም የቀመመውን መድሃኒት ሲያስተዋውቅ እና የሚሰሙትን በታላቅ ቅናት ሲያስተዋውቅ ትሰሙታላችሁ። የማያው ሰዎች ብቻ ናቸው አንድ መድሃኒት ለሁሉም ፈውስ ነው የሚለውን እወጃ የሚያምኑት። ሁላችንም ያ አንዱ መድሃኒት የአይን ህመምን፣ የዳሌ ህመምን፣ ተቅማጥን፣ ሽፍታን፣ የደም ግፎትን እና ኪንታሮትን ማዳን እንደማይችል እናውቃለን።

    እንዲሁ፣ ወደ ጋብቻ ሲመጣ ለሁሉም ትዳር የሚጠቀሙት አንድ መድሃኒት ብቻ ነው። ሁሉም ትዳር አንድ ዓይነት ነው ብለው በማሰብ ለእያንዳንዱ ትዳር አንድ ዓይነት እርምጃ ይወስዳሉ። ይህ ስህተት ነው ምክንያቱም ያሉት ትዳሮች የተለያዩ ዓይነት ትዳሮች ናቸውና።

    በሌላው አቅጣጫ ደግሞ ባል ማድረግ የሚገባውን ሁሉ የሚያደርግ መልካም የተሰጠ ባል አለ። አንዳንድ ጊዜ የተሰጠው ባል በዚያው ልክ የተሰጠች ማድረግ የሚገባትን ሁሉ የምታደርግ ሚስት ሊኖረው ይችላል። በሌላው በኩል የተሰጠው ባል መጥፎ የተባለች ሴት ሚስት ሊኖረው ይችላል። የተሰጠች ሚስት ደግሞ ሚስት ሊኖረው የማይገባው ክፉ ባልም ሊያጋጥማት ይችላል።

    ብዙ ሁኔታዎች በጣም ከመለያየታቸው የተነሳ መልክ በመልኩ ልንረዳቸው ይገባል። መልካሙን እና ክፉውን በአንድ ቀን በአንድነት መስቀል ተገቢ አይደለም። (ኢየሱስ ክርስቶስ ከሌቦች ጋር የተሰቀለው በአንድ ቀን ነው ይህም ኢየሱስ ክርስቶስን እንደ ተራ ሌባ እንዲታይ አደረገው፣ ምክንያቱም የተሰተው ቦታ ለሌሎች ተራ ሌቦች እንደሚደረገው ስለሆነ ነው።)

    እያንዳንዱ ትዳር የተለያየ ልምዶችን ይዞ ይመጣል። አንዳንድ ሰዎች መከተል ያለባቸው ለመልካም ትዳር ሰባት እርምጃ የሚለውን ይሆናል እንዲሁም ትልቅ ደስታን ሊለማመዱ ይችላሉ። ሌሎች ደግሞ ለመልካም ትዳር ሰባት እርምጃን ሊከታተሉ ይችላለሁ፣ ነገር ግን ደስታ የሚባለውን ሊያገኙ አይችሉ ይሆናል።

    በእርግጥም ለትዳር የማይሆኑ ሰዎች አግኝቼ አውቃለሁ። ሊያገቡም አይችሉም እንዲያውም ፈጽሞም አያገቡ ይሆናል ምክንያቱም ለትዳር የሚመቹ አይደሉምና። በትዳር ስፍራ ጭራሽኑ ደስተኞች አይሆኑም። ያለመታደል ሆኖ ለትዳር የማትሆን ሴት ቆንጆ ከሆነች፣ ወደ ትዳር በቶሎ ትገባለች ከዚያም መጋቢው ሊቋቋመው የማይችለውን ሁኔታ ትፈጥርበታለች። ለ ለትዳር ለማይሆኑ ሰዎች የሚሰጠው ምክር ከሌሎች ተራ ሰዎች ምክር የተለየ መሆን አለበት ነው።

    ይህ መጽሐፍ የተፃፈው የሆነ ዓይነት ትዳር ላለቸው ሰዎች ምክር ለመስጠት ታስቦ ነው። መልካም በሚባለው የትዳር ዓይነት ውስጥ ያለህ እንደሆነ ጠንቀቅ በል ምክንያቱም የማትረዳውን የትዳር ዓይነት ስታይ ለመተቸት ትፈተን ይሆናል !

    በዚህ መጽሐፍ ውስጥ በሙሉ ሆን ብዬ በራሴ ትዳር ውስጥ የምደሰትባቸውን በረከቶች አላነሳም። በራሴው ትዳር ውስጥ ስላለውም ተግዳሮት አላነሳም። ለምንድን ነው? የራሴን የትዳር በረከቶች ባወራ የኔ ትዳር መልካም አይደለም ብለህ ልትሸማቀቅ ትችላለህ። በእርግጥም የራሴን ተግዳሮቶች ባወራ ምናልባትም ላትረዳው ትችል ይሆናል! ዝም ብለህ በዚህ መጽሐፍ ገፆች ውስጥ በተፃፉት ቃላቶች ለህይወትህ እና ለትዳርህ  በረከት እና ፈውስን ተቀበል።

    ምዕራፍ 2

    ማስጠንቀቂ፡ በአገልጋዮች ትዳር ውስጥ የሥልጣን ሚዛኑ ይቀየራል

    ሁሉ ተፈቅዶልኛል፥ ሁሉ ግን አይጠቅምም። ሁሉ ተፈቅዶልኛል፥ በእኔ ላይ ግን አንድ ነገር እንኳ አይሠለጥንብኝም።

    1ኛ ቆሮንቶስ 612

    በእንሰሳቶች መኸከል የሥልጣን ሚዛን ሲቀያየር ማየት የሚያስገርም ነው። የዝሆንን መንጋ እና የአንበሶችን የኮራ እንቅስቃሴ መመልከትየሥልጣን ሚዛን ከአንዱ ምድብ ወደ ሌላው ምድብ እንዴት እንደሚቀያየር ታላቅ መገለጥን ይሰጥሃል። በቀን ብርሃን ዝሆኖች በደንብ ማየት ስለሚችሉ ወደ እነርሱ የሚመጣውን ማንኛውንም አንበሳ መግደል ይችላሉ። ዝሆኖች በቀን ብርሃን የአንበሶች ጉራ ቦታም አይሰጡትም።

    ነገር ግን ሲመሽ እና ጨለማው ሲወድቅ፣ አንበሶች በደንብ ማየት ሲችሉ ዝሆኖች ደግሞ ማየት አይችሉም። አሁን የሥልጣን ሚዛኑ ዝሆኖቹን አጥቅተው በእርግጥም ወደሚገድሏቸው ወደ አንበሶቹ ይሆናል። የአንበሶች ምድብ ትልቅ ዝሆንን ሲበሉ ማየት የሚደንቅ ነው !

    ትዳርም እንደዚሁ ደግሞ የስልጣን ሚዛኑ ይቀያየራል። የሥልጣን ሚዛኑ የሚቀያየሩበት ሁለት መንገዶች አሉ።

    በጌታ ያልሆነን ሰው ማግባት (ወይም X5 ባል  A ምርጡ ባል ሲሆን X5 የመጨረሻው እንደማለት ነው።) የሥልጣኑ ሚዛን ወደ ባል ይሆናል። የማያምን ባል ወይም X5 ባል በእግዚአብሄር ቃል የታሰረ አይደለም። ለእግዚአብሔር ቃል የሚታዘዝ አይደለም። ደስ ያሰኘውን ነገር ያደርጋል። የተሰጠችው ክርስቲያን ሚስት እንዲቀየርላት በትህትና ልታስደስተው ትሞክራለች።  ዓለም ሚስቶቻቸውን በሚያሰቃዩ ባሎች የተሞላች ነች። ብዙ ህጎች በፍቺ ላይ ወደ ሴቷ ያደላሉ ምክንያቱም ሴቶች በማያምኑ ወንዶች ለዘመናት ይሰቃዩ ነበር።

    ይህ መጽሐፍ ስለእንደዚያ ዓይነት ትዳር አይደለም። ይህ መጽሐፍ ስል አገልጋዮች ነው።አገልጋይ ካልሆንክ ይህንን መጽሐፍ ማንበብ አልነበረብህም ምክንያቱም የተዘጋጀው ላንተ አይደለም። የማትረዳውን ነገር አትተች። ቤገልግሎት ውስጥ ያሉ ሰዎችም መጥፎ ትዳር ይኖራቸዋልም እያልኩ አይደለም። የማወራው የሥልጣኑ ሚዛን ይቀየራል ነው። ሴቷ አገልጋዩ ባሏን የመጉዳት ትልቅ እምቅ ችሎታ አላት።

    በዚህ ትዳር ውስጥ ለተሰጠው መጋቢው ባል (A1 ባል) የሥልጣን ሚዛን የሚያደላው ለሴቷ ነው። የተሰጠው የእግዚአብሔር ሰው ለእግዚአብሔር ቃል የታሰረ በው፣ እንዲሁም ሚስቱ ሳትፈታው የፈለገችውን ነገር ሁሉ ታደርጋለች። በውጤቱም የሥልጣኑ ሚዛን ወደ ሴቷ ተቀይሯል ማለት ነው እንዲሁም ብዙ ክፋቶችን ወደ የራሷ A1 ባል ላይ ታመጣለች። ይህ ሚስትን ባለስልጣን ያደርጋታል።

    የፈለገው ነገር ቢመጣ ሚስቱን እንደማይፈታ A1 ባል ቃል ገብቷል ! የሚያስገርመው የእርሱ ለትዳሩ መሰጠት ሚስቱ እንድትቀብጥ ጉልበት ይሰጣታል። መቼም ሊባርር የማይችል ሰራተኛም የሚሆነው እንደዚህ ነው። የፈለገውን ነገር ቢያደርግ ፈጽሞም ሊባረር አይችልም እንዲሁም በሥልጣኑ እና በዓመጸኛበቱ ያድጋል።

    በሚስት ታስረህ እንደ ሆንህ መፋታትን አትሻ፤ በሚስት አልታሰርህ እንደ ሆንህ ሚስትን አትሻ።

    1ኛ ቆሮንቶስ

    Enjoying the preview?
    Page 1 of 1