You are on page 1of 34

ለ አእምሮ መጽሔት፥ የነሐሴ/August እትም -ቅጽ I- ቁጥር – 05/08-7

ለ አእምሮ መጽሔት፥ አዲሱ እትም – I-05/08-7

*
ለ አእምሮ መጽሔት፥ አዲሱ እትም – I-05/08-7

ለ አእምሮ – Le’Aimero © መጽሔት
http://leaimero.com

ሰሞኑ ጽሁፎችና ሰነዶች/ Recent Articles

ለ አእምሮ መጽሔት፥ አዲሱ እትም – I-05/08-7
ፀጋ፥ብርሃን
ዘመነ፥ብርሃን / Enlightenment
ግ ብ ፅ / ምን ሊያስተምረን መጣ ?
ዘ ጋርዲያን / The Guardian
ዓለም እንዴት ሰነበተች?
“ራዕይ ራዕይ …. “ዶቸ ቬለ የጀርመን ራዲዮ፤ ውይይት
ውርሰ፥ቅርስ
የአምባሳደር ብርሃኑ ድንቄ ደብዳቤ ፣ ለንጉሠ፥ነገሥቱ (1965)
Ethiopia to Yemen – The Most Dangerous Journey on Earth (BBC)

ፀጋ፥ብርሃን
Posted on August 29, 2013 by ለ አእምሮ / Le'Aimero

ፀጋ፥ብርሃን
ሲያይዋት ትንሽ ናት።ጠጋ ብለው ሲተነትንዋት ይህ ነው የማይባል ትልቅ ነገር
ነች።
ሳይታሰብ ብቅ ትላለች።ቆይታም ሳትወድ ትጠፋለች። ወዳጆቹዋ በነፍስ ግቢና
በነፍስ ውጪ ሰዓት ብዙ ናቸው።የልባቸውን ያደርሱ ቀን ግን ተራ በተራ እነሱ
እሱዋን እነደማያውቁዋት ጨርሶ ይከዱዋታል።
ከመሣፍንቶች ጋር አንድ ጊዜ አብራ ትቆማለች። „አብዮተኞችም“በጣም
አድርገው ያስጠጉአታል።አክራሪዎቹም ያቅፉአታል። ፋሽሽቶቹም እነደ
ኮሚኒስቶቹ አላማቸውና ፕሮግራሞቻቸው ላይ ከፍ አድረገው
ያስቀምጡአታል።
ሥልጣን ላይ ሲወጡ ደግሞ ብዙዎቹ መልሰው እንደ የሚፋአጅ የፍም እሳት፣
እርግፍ አድረገው ሁሉም ይጥሉአታል። በእግራቸው ቢረግጥዋት ይረግጡዋትል- ደስተኛ ናቸው።
ለወረሪ ጠላት መቼም እንደ ሱዋ „አመቺ“ ነገር የለም። በእሱዋ ስም ይዘምታል።
በእሱዋም ስም ገንዘብ ይሰበሰባል። ሰውን ወደ ጦር ሜዳ መሰብሰብ ይቀላል።
ወጣቶች ልጆችም ዕውንት መስሎአቸው ሕይወታቸውን እሰከ መሰዋት ድረስ
ይሄዳሉ። ተንኮልኛ አታላዩም፣ ይህን ሰለሚያውቅ እሱዋን ያስቀድማል።

የዋሁም „ዕውነት“ ነው ብሎ ይህን የሚሉ ሰዎችን ሳይጠይቅና ሳይመራመር
ዓይኑን ጨፍኖ ይከተላቸዋል። ሳያውቅ የገባበትን ጣጣና መንጣጣ አደገኛ
መሆኑን የሚረዳው ግን ነገር ከእጁ ከአመለጠች በሁዋላ ላይ ነው።… ሲደርስበት
ደግሞ ብዙ ነገር አልፎአል።
ልቡን አንዴ የሰጣቸው ደግሞ፣ ቢያታልሉትም „አሜን“ ብሎ ተቀብሎ ምንተዕፍረቱን ሸፋፍኖ ውስጥ ውስጡን እየተቃጠለ፣ አንገቱን ደፍቶ ይከተላቸዋል።
የተቀረው ዓይኑን እሰከሚከፍት ድረስ በጭፍን መንገዱ አለጥያቄ አብሮ
ይጓዛል። የደረሰበት ቀን ግን ወደ ሁዋላ ማለትም እሱንም ይከብደዋል።
ይህን ቀስቃሾቹ በደንብ ያውቃሉ።ይህን ተንኮለኛ አደራጆቹ በደንብ
ይጠቀሙበታል።
ማናት ይህቺ፣ አንዳንዴ በሦስት አንዳንዴ በአራት ፊደል የምትጻፈው፣ ነገር ?
ከመሣፍንቱ እስከ ተራ አወናባጁ?… ከፋሽሽቱ እሰከ ኮሚኒስቱ ፣ ከአናርኪስቱ
እሰከ ሽፍታው፣…ከቅኝ ገዢው እስከ…ባሪያ ነጋዴው ድረስ የሚያነሱዋት ቃል?
ሊበርቲ ናት?… ወይስ አርነት?… ነጻነት ናት ወይስ ነጻ- ሰው?…ጥበብ? …ብርሃንና
ዕውቀት? ወይስ ጨለማ?…
ሞሰሊን ኢትዮጵያን ሲወር ያስቀደመው ቃል ቢኖር „…የሥልጣኔ ሚሺን፣…
ኢትዮጵያን ከባርንት ለማውጣት የታቀደ ዘመቻ… ሲቭላይዚንግ ሚሽን..“
የሚለውን ቃል:- ለማስታወስ ወርውሮ ነበር። የወረራ ዘመቻውንም ያ ፋሽሽት
የሰየመውም በዚሁ ግሩም ቃልና ጥሪው ነበር።
ሌኒንና ስታሊን፣ ማኦና ካስትሮ፣ ከእነሱ በሁዋላ የተነሱት ሥፍር ቁጥር
የሌላቸው „ነጻ-አውጪዎች፣ እስከ መገንጠል የሚለውን ትግላቸውን“ የቀየሱት፣
ያራመዱት፣ የልባቸውን ያደረሱት፣ በዚህች „አርነት“ በምትባለው ቃል ነበር።
በሌላ በኩል በአፍሪካና በደቡብ አሜሪካ በሕዝቡም ላይ ተነስተው የጨፈሩት
ወታደሮች ያራገቡት „ሥርዓትና ቃል…“ ሌላ ሳይሆን ይኸው፣„…አርንትን፣
..ነጻነትን፣ እኩልነትን፣ ሰበአዊ መብት፣ …ዲሞክራሲን “ነበር። የወታደሩ
መንግሥት፣ ደርግም ብሎታል።„እናመጣላችሁዋለን…“ በሚለው ውሸት ዙሪያ
እስከ አሁን ድረስ ብዙዎች ቆመዋል።
የ20ኛው ክፍለ ዘመን የውሸት ፖለቲካም በብዙ አካባቢ የተመሰረተው ፣በዚሁ
አታላይ ቃል ላይ ነው። እላይ ከተጠቀሱት ቡድኖችም ውስጥ አንዳቸውም
የገቡበትን ቃላቸውን እስከ አሁን ድረስ አላከበሩም።

እንግዲህ ነገሩ ያላው እነሱ ጋ ሳይሆን እኛው ጋ ነው።

„ነጻነትን፣…በሌላው አካባቢ እንደሚባለው፣ ሊበርቲን፣…ጥብብን፣ ብርሃንና
ዕውቀትን…“ እባካችሁ ስጡን፣ እባካችሁን አምጡልን ብለን፣ ማንንም
የምንጠይቀው ነገር ሳይሆን ፣ እኛው ነጥቀን የምንወስደው ነገር ነው።
መሬት ላይ የወደቀውን ነገር ብድግ አድርጎ የእራሳችን ማድረጉ ደግሞ ወንጀል
አይደለም። ለዚህ ደግሞ ዕውነቱን ለመናገር፣ „ግብ ግብም፣ጦርነትም”
የሚባለው ነገር ውስጥ መሄድ አያስፈልግም ።
ማመዛዘናና ነገሮችን መመልከት፣… ማሰብና ያሰቡትን ነገር መናገር፣… መጻፍና
መወያየት፣ መከራከርና መተቸት፣ እኛ የሰው ልጆች ከእግዚአብሔር ወይም
አቴኢስቶች እንደሚሉት „ከተፈጥሮ“ ያገኘነው ፀጋና ስጦታ ነው። ለምን
አምባገነኖች ይህቺን መብት ይፈሩአታል?
አንድ አምባገነን ሥልጣኑን መከታ አድርጎ ብዙ ነገሮችን „አታድረጉ ብሎ አንድን
ሕዝብ ሊከለክል“ ይችላል። ማሰብን ግን እሱ ጨርሶ መከልከል ይችላል?
በምንም ዓይነት፣ ማሰብን መከልከል አይችልም። በምን አቅሙ ነው፣ የአንድ
ሰው ጭንቅላት ውስጥ ገብቶ ሊከለክል የሚችለው? ይህማ አስቸጋሪ ነው።
አእምሮ ያሰበውን፣ የታሰበውንስ ቀና ሐሳብ ከሌላው ጋር ለመነጋገር (ምንም
ዓይነት ሥልጣን ቢኖረው) ማንም ሰው ማንንም ሊያግደው አይችልም ።
እንግዲህ አሁን ያለነው፣ በዚህ „ፀጋ-ብርሃን“/ዘመነ፥ብርሃን በሚለው ጽሑፋችን
እሱን አንስቶ መመልከቱ ላይ ነው። አምባገነኖች የእያንዳንዱን ግለሰብ ነጻነት፣
ለምን እንደጦር እንደሚፈሩ በየጊዜው አንስተን እንመለከተዋለን።

እንግዲህ ይህ አንደኛው አርዕስት ነው።
ሁለተኛው ስለ ጋርዲያን ጋዜጣ ነው።የምዕራቡ ዓለም ስለ ሚኮራበት ስለ ፕሬስ
ነጻነት፣ ስለዚያም አታሚዎች ፍተሻ ፣ስለ ጋርዲያን ጋዜጣ ነው። ቻይና በዚህ
ጉዳይ ላይ ምን እንዳለች አስተያየቱዋን ፈልገን ለማውጣት አስበን ነበር።
አልተሳካልንም። ግን አገላብጣችሁ እንደምታዩት የሌሎቹም አስተያየት ቀላል
አይደለም።

ሦስተኛው አርዕስት„ ….እኛ ጥቁሮች እራሳችንን በእራሳችን፣ ተመካክረንና
ተቻችለን ተፈራርቀን መግዛት ስለ አልቻልን፣ የዱሮ ጌቶቻችን ነጮች መጥተው
ይግዙን…“ በሚለው አዲስ ጥሪ ላይ ያተኩራል።
ይህ ደግሞ ምን እንበላው „…ያሳዝናልም። ያስቃልም። ያቃጥላልም።
ይኮረኩራልም። ….“ ወቸ ጉድም ያሰኛልም።
በተጨማሪም አወዛጋቢ ሰለሆነው የግብፅ ጉዳይ ያለንን አስተያየትና፣ እንዲሁም
ስለ ውርሰ፥ቅርስ ለመነሻ ያህል የደረሰንን ሰነደንና የሰዓሊው የእስክንድር
ቦጎስያን ማስታወሻችንንም ተመልከቱት።
ዋና አዘጋጁ
ይልማ ኃይለ ሚካኤል
——————–
© ለ አእምሮ 2005 / © Le’Aimero Copyright 2013

ሕግ፥ነክ ማስታወሻዎች / Disclaimer & Legal Statements
Le’Aimero’s Disclaimer

ዘመነ፥ብርሃን / Enlightenment
Posted on August 29, 2013 by ለ አእምሮ / Le'Aimero

ማንም ሊያግደው የማይችለውየተፈጥሮ ጸጋ! የተፈጥሮ መብት!
በትክክል ስለ ነጻ ሰውና ስለነጻነት፣ስለ ማሰብና ስለ አለ ፍረሃት መነጋገር፣ ስለ
እነሱም መጻፍና መመራመር የተጀመረው:- እንደገና በትክክል ነገሩን
ለማስቀመጥ “ ስለ ባሪያ ሳይሆን ስለ ነጻ ሰውና ስለነጻነት“ (ይህ መነገር ያለበት
አስፈላጊ ቦታ ነው) ስለዚህ ጉዳይ ማሰብና መነጋገር የተጀመረው በጥቂት ሰዎች
የጥናት ክበብና የጽሕፈት ቢሮ ውስጥ ነው።
የደረሱበት ውጤትና ተመክሮዎች፣ ታትሞና ተባዝቶ፣ለሰዎች መበትን በአውሮፓ
የተጀመረው በመካከለኛው ክፍለ ዘመን ነው።
የዚህ ጥናት ውጤት የዩኒቨርስቲ አስተማሪዎች እጅ ይገባል።ቆየት ብሎ
ተማሪዎቻቸው ቀበል አድርገውት በየአለበት፣በመጀመሪያ በዘመዶቻቸውና
በጓደኞቻቸው መካከል አሰራጭተውታል።
እንደሚባለውና ብዙዎቹ እንደሚገምቱት የጀርመኑ ፈላስፋ ኢማኑኤል ካንት
አይደለም „ስለ ዘመነ- ብርሃን፣ስለ ጸጋና ስለ ጧፍ ልጆች፣… ስለ ጨለማው
ዓለም „ የመጀመሪያውን የአካዳሚ ጽሑፍ የጻፈው።ያስተማረው። የተነተነው።
ለካንት አስተማሪዎቹና የቅርብ ጓደኞቹ ናቸው፣ አርዕስቱንም፣ሁኔታውንም ለእሱ
የእንግሊዘኛ ቋንቋ በደንብ ለማያውቀው ፈላስፋ በሁዋላ ያስተዋወቁት።
ካንት ግን አለጥርጥር ትላልቅ ጽሑፎች አውጥቶ የዘመኑን ሰዎችና ከዚያ በሁዋላ
የተወለዱትን ትውልዶች፣ ስለ ሞራልና ስለ ኤትክ፣ስለ የሰው ልጆች አብሮ
የመኖር ዘይቤ፣ ስለ የዓለም ሰላም፣ ስለፍትህና ፍርድ ብዙ ነገሮች
አስተምሮአል።

እንግዲህ የኢንላይትሜንት :- የዘመነ- ብርሃን ትምህርት ፣ ዋና አባት ካንት
ሳይሆን የእንግሊዙ ፈላስፋው ጆን ሎክ ነው።
ሎክ ይህን ዕውቀት የሰበሰበው፣ከቡዙ ጊዜ ጥናት በሁዋላና እሱ እራሱ ከአየውና
ከአገኘው ተመክሮ ተነስቶ ነው። ግሩም ጥያቄዎችን ለእራሱና ለሌሎቹም
በማቅረቡና ለእሱም ጊዜ ወስዶ ከፍተኛ አተኩሮስ ሰጥቶ፣ በመልስ ፍለጋውም
ላይ በመጠንከሩም ነው።
ከጓደኞቹ ጋር አብሮ እየተገናኘ በአደረገው የረጅም አመታት የጥናት ጊዜ በሁዋላ
እሱ እንደሚለው „…የተሳሳተ አቅጣጫ ይዘው ሁሉም ብዙ ተንከራተው“ እንደ
ነበር በተወልን ማስታወሻው ላይ ያስታውሳል።
በእርግጥም ጆን ሎክ ከጓደኞቹ ጋር በየጊዜው እየተገናኘ በጋራ በሚያካሄደው
የጥናትና የምርምር ድካም ፣ እሱ እንደሚለው፣ የተሳሳተ መንገድና የተሳሳተ
ፍንጭና ዱካ ተከትለው የማይሆን ቦታ ደርሰው ነበር።
ግን አስተዋዩ ሎክ፣እሱ እራሱ እንደሚለው፣ ያን ጎዳና ጥሎ በ1689
ዓ.ም(እ.አ.አ) „አንዳንድ አመለካከቶች፣ በፖለቲካና በሃይማኖት፣እንዲሁም
በአስሰተዳደር ላይ…“በሚለው አርዕስት ሥር የራሱን አመለካከቶች ጽፎ
አደባባይ ላይ ሳያወጣው ለተወሰኑ አመታት ሐሳቦቹን አስቀምጦታል።
ሎክ እሱን በሚያበረታተውና መልሶም በሚጠይቀው በፖለቲከኛው በሁዋላ
የመኳንንት ማዕርግ አግኝቶ ግራዝማች የተባለው አንቶኒ ኤሽሌ ኩፐር፣በእሱ
ምክንያት የአመለካከት አቅጣጫውን ሊቀይር ችሎአል።
ግራዝማቹ የኤርል ኦፍ ሻፍትስበሪ”.. እስቲ ደግሞ በዚህ ጉዳይ ላይ አሰበህ
ጻፍልኝ..“ ብሎ ይጠይቀው እንደነበር ይጠቀሳል። ትውውቃቸው በሰኔ/ሐምሌ
1666 አካባቢ ነው።
የእሱና የአብዛኛው የጧፍና የብርሃን ልጆች የትግል አቅጣጫም „ …የሰውን
ልጆች፣ በሙሉ በዚያውም የእንግሊዝን ኑዋሪዎች“ እነሱ እንደሚሉት“…
ከሮማው ሊቃነጳጳስ የባርነት ዘመን ነጻ -ለማውጣት ምን እናድርግ ?“ የሚለው
„ጥያቄና የትግል ብልሃት“ የጉዞአቸውን አቅጣጫ እነደወሰነውና እንደቀየረው
እነሱም፣አረጋግጠው ተናግረውታል ።
በአጭሩ ሎክ የሮማውን ቤተ ክርስቲያን ሊቃነ ጳጳስ የበላይነት፣ እንደሌሎቹ
እንግሊዞችና የሰሜን አውሮፓ ተወላጆች እሱ የማይቀበል ሰው ነበር።
እንዲያውም „በቫቲካን ሥር ሁኖ የካቶሊክን ሃይማኖት ተከትሎ መኖርን
እንደባርነት“ የሚያይ ሰው ነበር። በዚህ አመለካከቱም ብቻውን አልነበረም።

ዘግየት ብለን እነደምናየው የሎክ ትምህርቶችና አመለካከቶች በፈረንሣይ እና
በአሜሪካን አብዮት፣ከዚያም በሁዋላ እነሱ እራሳቸው ወደው በነደፉትና
በተቀበሉት ሕገ- መንግሥት ላይ እንዲሰፍር ተደርጎአል።
በጀርመኑ በ1848 እና እንደገና ከዘውድ አገዛዝ በሁዋላ ተነድፎ በወጣው በ1918
የጀርመኑ የቫይመር ሕገ-መንግሥት ላይ የጆን ሎክ መሰረታዊ አስተሳሰቦች
አብሮ ተጠቃሎ እንዲቀመጥም ተደርጎአል።
የዓለም ሕዝብ በፋሺዚምና በኮሚኒዚም ተዋክቦና በሚሊዮን የሚቄጠሩ ሰዎች
በዚያ ጦስ ተጨፍጭፈው ከአለቁ ወዲህም፣ ከዚያ በተገኘው ተመክሮም
“አረመኔዎች ተመልሰው እንዳይመጡ በተነደፈው የጋራ ሐሳብም ላይ” የጆን
ሎክ መሰረታዊ ሐሳቦች መነሻ ሁነው „ዓለም አቀፋዊው የሰባአዊ መብት አዋጅ“
ሊታወጅም ችሎአል። ንቁ የሕግ አዋቂ የኢትዮጵያ ልጆችም አብረው የጥቁሩን
ሕዝብ ወክለው የ1948ቱን አዋጅ ነድፈዋል። እንደሚባለው “የነጮች አዋጅ”
ሳይሆን አብረው እንደአባልነታቸው አጽድቀዋል። “የአረመኔዎች አገዛዝ ተመልሶ
እንዳይመጣ” -ይህ ነው የዓለም አቀፉ አዋጅ- ይህ ነው የጀርመኖች ከሒትለር
በሁዋላ የወጣው አዲሱ ሕገ-መንግሥት ይዘት “…የሰው ልጆች ሁሉ
በተፈጥሮአቸውና በሕግ ፊት እኩል ናቸው የሚለውን መሰረተ ሐሳብ
ተንተርሶ፣… ማንም
ሰው
የሌላውን
ሰው
መብትና
ሰበአዊ ክብሩን ሊደፍረውም ሊረግጠውም
አይችልም …”ብሎ ያግደዋል።
ከዚያም ስለ መብቱ፣ከግል ሀብት እስከ የግል እምነቱ፣ ስለ መናገርና
መጻፍ ነጻነቱ፣…ፍርድና ፍትህ፣ ስለ ተቃውሞ መብቱ… ይዘረዝራል።
ሎክ በምርምር ዘመኑ „ ብዙ የተለያዩ አስተሳሰቦችና እምነቶች በአሉበት በአንድ
ሕብረተሰብ ውስጥ እንዴት ተቻችሎና ተከባብሮ መኖር ይቻላል?“ የሚለውን
ጥሩ መጣጥፉን (በ1667እ.አ.አ) ጽፎ መሰረታዊ የሆኑ ነገሮችን፣ አብሮ ለመኖር
አስፈላጊ የሆኑ ነጥቦችን አስፍሮልናል።
ሰውዬው ” ባለ ግርማው አብዮት Glorious Revolution” የሚባለው
የእንግሊዞች አብዮት ከመፈንዳቱ በፊት የስደት ዓለምን በነጻው ሆላንድ
ቀምሶአል።
በጽሑፉም የአንድ መንግሥት ወይም የአንድ አስተዳደር ዋና „ዓላማና ኃላፊነቱ፣
ጸጥታና ሰላም በዜጎቹ መካካል ማረጋገጥ፣ ሰው የፈለገውን ሃይማኖት
እንዲከተል መልቀቅ እንጂ ከዚያ አልፎ ያ አስተዳደር በመንፈሳዊ ዓለም ውስጥ
ገብቶ ሰዎች እንዴት መኖር እንዳለባቸው፣ማንን ማምለክ እንዳለባቸው፣… በማን
ሃይማኖታዊ አባት ሥር መተዳደር እንዳለባቸው መወሰን ቀርቶ፣ እዚያ ውስጥ
አልፎ ተርፎ ገብቶ ማብኳት አንድ መንግሥት የለበትም „ ይላል።

በእሱ እምነት „መንግሥት በዚህ ጉዳይ አያገባውም“ባይ ነው። ከዚሁ ጋር
ፈላስፋው ሎክ አንድ ሰው፣አንድ ሕዝብ የፈለገውን የተለያዩ ሃይማኖቶች፣እራሱ
መርጦ ሊከተል ይችላል።”
ይህን ማድረግ በእሱ እምነት „ሀገር እንዳይበታተን ይጠቅማል“ ባይ ነው።
ንጉሡ ግን የእንግሊካን እንጅ የካቶሊክ ሃማኖት ተከታይ ፍጹም መሆን
የለበትም ይላል። ቅራኔ ይታይበታል? አይደለም።
የጆን ሎክ ጉዞ በዚህ አቅጣጫ ጀርመኖችም ከሮማው የቫቲካን ካቶሊክ
ቤተክርስቲያን ለመላቀቅ ከአደረጉት ከማርቲን ሉተር የፕሮቴስታን እንቅስቃሴም
ጋር በጥብቅ ይመሳሰላል ።
ግን ደግሞ የፈላስፋው አመለካከቶች፣ከዚያም አልፎ ይሄዳል። “መለኮታዊ ነኝ”
የሚለውን የአንድ ንጉሥ ፈላጭ ቆራጭ አገዛዝን እንደ ሮማው ካቶሊክ
ቤተክርስቲያን እሱንም ያቃወማል።
ብረሃን ልጆች፣ የንጉሰ ነገሥቱን ዙፋንና ዘውድን ሳይተቹና ሳይነኩ በዚያ ላይ
ያቆማሉ ብሎ መገመት ስህተት ነው። በ1680 „…መለኮታዊው የንጉሡ
ሥልጣን…“በሚለው ጽሑፉ ሎክ ስለ የሥልጣን ገደብ በንጉስ ላይ አንስቶ
ከዚሁ ጋር ራመድ ብሎ ስለ ነጻነትና ስለ እኩልነት፣ ስለፍትህና ዳኝነት፣ ስለ
የፓርላማ መብትና ገደብ በአንድ ሕብረተሰብ ውስጥ፣ ምን መምሰል አለበት?
ብሎ ወደ መዘርዘሩ ይራመዳል።
እንግዲህ ይህ ሰው ቆየት ብሎ በቀጥታ እኛን የሰው ልጆችን(የትም እንሁን የት፣
እስላም እንሁን ክርስቲያን፣ አሕዛብ እንሁን፣ኮሚኒስት ወይም ሶሻሊስት…)
በቀጥታ ሁላችንም ሰለሚያሳስበውና ስለሚያስጨንቀው በሥራም ላይ ውሎ
ሌላ ቦታ ማየት ስለ ምንፈልገው “ …ስለ በነጻ-የመኖር መብት፣…ስለ ነጻ-ሰው
መብት፣ ስለ የግል ሀብት፣ በእሱም የሰው ልጅ ስለ አለው መብት…“ ፈላስፋው
ጆን ሎክ አንስቶ መልስ ይሰጣል።
ንጉሠ ነገሥቱ ሕግ ከጣሰ? ብሎ ይጠይቃል። ሕዝቡም መብቱን በመንግሥት፣
በገዢ መደብ ከተገፈፈ? ምን እናድርግ ይላል። ፈላጭ ቆራጩ ጉልበተኛ ገዢ
አልሰማም ከአለ? ….ያኔ ሕዝቡ፣ ሰበአዊ መብቱ ተገፎ ተገዢ ባሪያ እንዳይሆን፣
ፈላስፋው „…እግዚአብሔር ለሰው ልጆች በተፈጥሮ የሰጠውን መብቱን
ለማስከበር፣ላለማስነጠቅ መነሳት“ አለበት ብሎም ያስተምራል።
ካንት በአስተማሪዎቹና በአብሮ አደግ ጓደኞቹ የጆን ሎክን ከእንግሊዘኛ ወደ
ጀርመንኛ የተተረጎመውን ጽሑፍ አገላብጦ እላይ እንዳልነው ወፋፍራም
መጽሓፍትን በሁዋላ ጽፎልናል።

የአሜሪካንንና የፈረንሣይ አብዮት አባትና አዋላጆች በሕገ-መንግሥታቸው ላይ
„ስለ ምርጫ፣ ….“ የሎክን ሓሳቦች መሰረት አድርገው ወደ ዲሞክራቲክ ሥርዓት
ከአንድ መቶ አገር የበለጡ መንግሥታት ተሸጋግረዋል። እንደተባለው ከ1948 ቱ
የተባበሩት መንግሥታት አዋጅ ወዲህ “ለሰበአዊ መብት መታገል፣ ለነጻ-ፕሬስ
መሟገት፣ ለግል ሀብት መቆም፣መምረጥና መመረጥ፣መተቸት፣ፊልም መቅረጽና
መጸሕፍቶች ማተም …” እንደ ወንጀል አይቆጠርም። የሎክ ትምህርት ውጤት
ይህ ነው።
ይህን ሐሳብ ግን :- ይህ ነጥብ ሲነሳ የሚቆጡ ደግሞ የሚበሳጩ አይጠፉም- እነ
ሌኒንና እነ ስታሊን፣ ማኦና ሖዲጃ፣ ፖልፖትና ካስትሮ፣ ኢሳያስና መንግሥቱ
ኃይለ ማሪያም…ቆጥረን አንጨርሰውም፣ ተነስተው ….ይህን ሐሳብ ውድቅ
አድረገው „አምባገነን ሥርዓታቸውን“ (መውደቃቸው ላይቀር) በገዛ
ወገኖቻቸው ላይ መስርተዋል።
እዚሁ “የቶታሊቴሪያንና የአምባገነኖች የአስተሳሰብ” ማጥ ውስጥ ገብቶ አልወጣ
ያለው ሰው ቁጥር ሌላ ቦታ እየቀነሰ ሲመጣ እኛ ጋ ተበራክቶአል። ይህ ዕውነት
ነው?
ጆን ሎክ ፈላስፋው „ስለ አእምሮ ነጻነት አመጣጥ „ ጽፎአል። ወዳጄ!
በአንዴ ሁሉን ነገር ዘርግፎ ማስቀመጥ አይቻልም። በቂ ጊዜ ወደፊት ስለ አለን
ቀስ ብለን እንመለስበታለን። ቀስ ብለን እንደርስበታለን።
አንድ ጥያቄ ግን አንስተን ጉዳዩን እዚህ ላይ ለጊዜው እናሳድራለን። ለምንድነው
የኢትዮጵያ ምሁር እንደዚህ ዓይነቱ፣ እነደ ሎክ ያሉ ፈላስፋዎች ላይ
አተኩሮአቸውን ሳይጥሉ እንዲያው „…በላብ አደሩ አምባገነን ሥርዓት፣በዚያ
ፍልስፍና ተማርከው….“ ” …በሌኒን እና በስታሊን ፣… በማርክስና በማኦ
ትምህርት” ላይ ዓይናቸውን ጥለው እሰከ አሁን ድረስ እዚያው ላይ ብዙዎች
የቀሩት? ለመሆኑ እነሱስ ዛሬ ስንት ናቸው?
…የሰው ልጆች:-ሁለተኛው ጥያቄ- ዕድሜ ልካቸውን ሊገዛቸው የሚፈልገውን
“አንድ አምባገነን ሥርዓት” ምን ያህል ጊዜ ዝም ብለው ይቀበሉታል?…
ይሸከሙታል?
በሌላ በኩል „ በተፈጥሮ ያገኘነውን የነጻነት መብት“ እሱን ማን ሊያግደው
ይችላል? ለምን ድነው “ስለሃይማኖት ነጻነት፣… ስለየተለያዩ ሃይማኖቶች
በኢትዮጵያ ተቻችለው መኖር” በየጊዜው እያስታወሱ መናገር የሚያዘወትሩ
ሰዎች፣ ለምን ስለ የተለያዩ ፖለቲካ ድርጅቶች እንደዚሁ ተቻችሎ መኖር
የማይናገሩት?

ለምንድነው ስለ
“ብሔር/ብሔረሰቦች እኩልነት በኢትዮጵያ አለ” ብለው
የሚናገሩ ሰዎች፣ ስለ “ሰበአዊ መበት፣ ስለ ግለሰብ ነጻነት፣ ስለ ነጻ-ፕሬስ
አስፈላጊነት ግልጽ በሆነ ቋንቋ የማይናገሩት?
መልሱንም እንግዲህ ቢቻል ወደፊት በጋራ መልስ ብለን እንመለከተዋለን።
ይልማ ኃይለ ሚካኤል

ግ ብ ፅ / ምን ሊያስተምረን መጣ ?
Posted on August 29, 2013 by ለ አእምሮ / Le'Aimero

„ጠላት“? አንድ ግራ የሚያጋባ ቃል!

„አብዮት“፣- ፈረንሣይ አገር አንዴ እንዳደረገቸው- በኢትዮጵያ ልጆቹዋን ቅርጥፍ
አድርጋ በልታለች። ግብጽ ላይ ደግሞ -አንዱ የጀርመን ጋዜጣ እንደ ጻፈውይህቺ ጨካኝ አብዮት ብቅ ብላ „ወንድሞቹዋን“ ከእህቶቹዋ ጋር ጠብሳ፣ ዋጥ
አደርጋችዋለች።“
ነገ ደግሞ – ይህን ዛሬ ማን ያውቃል- አንዱን ቀቅላ እንደ ልማዱዋ ትበላለች።
ምናልባት -ይህን ማሰቡ ያስፈራል- እናትና አባትዋን አሳዳ…ትጨርስም ይሆናል።
ወሬው እንደተሰማ፣ ዜናው ከካይሮ እንደተስፋፋ(-የአገሬን ልጆች መቼም
በዚህቺ ድፍረታቸው እወደቸዋለሁ፣ በዚህችም ችሎታቸው አደንቃቸዋለሁ -)
ቶሎ ብለው፣ “… ሙርሲ ይህን ቢያደርግ፣ የእስላም ወንድማማቾች ያን
ቢያደርጉ፣ ወታደሩ ለአገሩና ለሕዝቡ ቢያስብ፣ አንድ ላይ ተቀምጠው ቢነጋገሩ
ኑሮ፣….ሁለቱም ሦስቱም፣አራቱም ወገኖች የጋራ መንገድ ቢፈልጉ፣እረ ቢያንስ

በትንሹ ቢከባበሩ፣… አስታራቂ ሽማጋሌዎች እንኳን መኻላቸው ቢገቡ…ይህ ሁሉ
እነሱ እነደሚሉት ትርምስና ደም መፍሰስ፣ሞትም ላይ በአልደረሱም ነበር…“፣
ይላሉ።
እንደዚህ ዓይነቱን ቀና ሐሳብ ከሚሰነዝሩት ሰዎች መካከል፣መገመት
እንደሚቻለው ኢህአዴግን የሚደግፉ ሰዎችም (ወደ ኢትዮጵያ ስንመጣ ግን
ሌላ ነገር ያነሳሉ) እንደ ተደመጠው፣ እነሱም ይገኙበታል።
አዲስ የተፈጠረው የግብጹ ውስጣዊ የፓለቲካ ሁኔታ ግልጽ አድርጎ የሚያሳየን
አንድ ነገር ቢኖር (ምን ግብጽ ብቻ!… ጠቅላላው መካከለኛው ምሥራቅ)፣
እንዴት አድርጎ፣ አለመደማመጥ፣ በጠላት አይን ከመሬት ተነስቶ መተያየት፣
…የሁዋላ ሁዋላ፣ ቀስ እያለ፣ ከባድ ችግር ውስጥ አንድን ሀገርና አንድን ሕዝብ
እንደሚከት ቁልጭ አድረጎ፣ያስተምረናል።ያሳየናል።
እንዴት አድርጎም ስለ „ሀገር አስሰዳደር ብልሃትና ዘዴ፣ ምንም ነገር አለማወቅ“፣
ምን ያህል መመለሻ የሌለው እሳት ውስጥ አንድን ሕዝብና እንድን ሀገር፣
በጥቂት ሰዓታት፣በትንሽ ጊዜ፣ በቅጽበት፣ እነሱንጨምሮ እንደሚበታትን
ማስተዋል የሚችል ሰው ቢኖር፣ የግብጽ ሁኔታ፣ ቁልጭ አድርጎ ያሳያል።
ያስተምራል።
ስለ የተለያዩ የሰው ልጆች በህሪና ተፈጥሮ ቅንጣት ያህል እነኳን ደክሞ
ለመረዳት አለመቻል፣ አለመሞከርም ገፍትሮ መጨረሻ ወደ ሌለው የማይታወቅ
ሁኔታም ውስጥ እነደሚከት፣ የግብጽ ግርግር ያስተምራል።ተጠንቀቁም ብሎ
ይመክራል።

ግብጽ አብዮቱን በአካሄደች በአንድ አመት ጊዜ ውስጥ እንደዚህ ትሆናለች ብሎ
የገመተ ሰው የለም።
ግብጽ የገባችበት ሁኔታና ችግር ደግሞ ማንኛውም አገር -የአስተዳደር ብልሃትን
ከአላወቀበት፣ ምክንያቱ እላይ ተገልጸአል- ዓይኑ እያየ፣ ነገ ሰተት ብሎ፣ ያ!
ሀገርና ሕዝብ ሊገባ ይችላል።
ሌላም ትምህርት የግብጹ ሁኔታ ጥሎልን ሄዶአል።
እሱም „ወታደሩ“ በግብፅ ሀገር (በሌላው ዓለም እንደምናውቀው)፣ „ በፖለቲካ
ስር የሚተዳደር የሀገር መከላከያ ተቋም „ ሳይሆን፣ ይህ የጦር ሠራዊቱ እራሱን
የቻለ(እስከ ዛሬ የምናውቀው አራት ተቋሞችን ብቻ ነው፣እሱም…የሕግ
ማውጫ፣የሕግ መወሰኛ፣ ነጻ-ፍርድ ቤትና ነጻ- ጋዜጣን/ሜድያ…) „አምስተኛው፣

የሕብረተሰቡ በዚያውም ፖለቲከኞቹንና የፖለቲካ አቅጣጫን የሚቆጣጣሪ
ኃያል ኃይል“ ሁኖ ዘንድሮ ብቅ ብሎአል።
እንደሚባለው የግብጽ የጦር ኃይል፣ ዱሮንም ቢሆን „በአገሪቱ ውስጥ፣
በመንግሥት ስር የራሱ የሆነ “ልዩ መንግሥት“ ገና ዱሮ እንደ አቋቋመ፣
የአደባባይ ምሥጢር ሁኖ ይነገርለታል።
የእራሱም የሆነ የተለያዩ እንዱስትሪ፣ምርት የሚያመርቱ የግል ፋብሪካዎች፣
የንግድ ድርጅቶች፣የሕንጻ ተቋራጮች፣ የጉዞ ወኪሎችና የቱርስት ድርጅቶች፣
ከእነሱ ጋር በየቀኑገንዘብ„የሚያትምበት“ ሆቴሎች፣ባንኮች፣ሠራዊቱ አሉት።
„ሲሶ መንግሥት ነው“ ማለት፣አንድ ተመልካች እንዳለው፣ ይቻላል። ይህ
በግብጽ እንደሆነም እርግጠኛ ሁነው ብዙዎቹ ይናገራሉ።
እንደዚህ ዓይነቱ የአሰራር ዘይቤምና ሐሳቡም ተስፋፍቶ ወደ ሌሎች የአፍሪካ
ግዛቶችም እንደዘለቀና፣ አንዳንዶቹ የአፍሪካ የጦር ኃይሎች፣ ባንክ ቤቶች
ለመክፍት፣ ፋብሪካ ለመመስረት፣ የሕንፃ ተቋራጭ ለመሆን ዝግጅት ላይ
እንደሆኑ የአውሮፓ ጋዜጣዎችም ይጽፋሉ።
ምን ይታወቃል፣ በዚህ በያዝነው በ21ኛው ክፍለ-ዘመን የግብጽ ጉዞ ተከታይ
አግኝቶ፣ እኛም ከሌሎች የአፍሪካ ሀገርና መንግሥታት ጋር ወደዚያው(ደርግ
እንዳልገዛን ሁሉ) እንደገና ተመልሰን እናመራ ይሆናል።
በርካሽ የወር ደመወዝ የጦር ፋብሪካውን፣ሆቴሉን … በጉልበት ሥራ
የሚያንቀሳቅሱለት፣ነገሩ ከተነሳ ላይቀር „…ወጣት ወታደር እና ሰላይ ሁነው
የሚቀጠሩት ልጆች“ እንደሆኑም ይጠቀሳል።
ሐሳቡ ከየት መጣ? ማነው የዚህ ዓይነቱ አሰራር አባቱ?
እሱን እነተውና „አብዮት ልጆቹን የምትበላው ለምንድነው?“ ብለን እንጠይቅ።

ቡዳ ስለሆነች አይደለም። ወይም የአብዮት „ዓይኑዋ „ ከሩቁ ስለሚወጋም
አይደለም። ወይም ደግሞ አብዮት „…ደም ማሽተት፣ደም ማፍሰስ“
ስለምትወድም አይደለም።
አብዮት ልጆቹዋን ትበላለች የሚባለው በአንድ ነገር ነው።
እሱም በአንድ ሀገር የሚኖሩ፣ ነገር ግን የተለያዩ አመለካከቶችና አቋሞች
የሚያራምዱ፣ኃይሎች፣… እንበል ጥቂት ቡድኖች፣የፖለቲካ ድርጅቶች:-

አቋማቸው ሊጻረርም ይችላል- „ በጠላትነት በደመኛ ጠላትነት መተያየት „
የጀመሩ
ሰዓት“

ያኔ!
ነገር
ተበላሸቶ፣”አብዮት ልጆቹዋን
ለመብላት” ቢላዋን ትስላለች፣ድስቱዋን
ትጥዳለች፣
ጠበንጃዋን
ትወለውላለች፣ ማለት ነው።
ቀደም ሲል „ሰውን ለመሰብሰብ ሆን ተብሎ የተወረወረ አይዲኦሎጂ የሚዋገው
ጠላት“ ያስፈልገዋል ብለናል።
አለበለዚያ ያ ድርጅት እንደ ምትሃት፣ ለአፍዝ አደንግዝ፣ ተከታዮቹን
ለመሰብሰብ የቀነጠሰው ቅጠል፣ ያን ቢል ይህን ቢያደርግ የመከተለው “ጀሌ”
መሰብሰብ ሰለማይችል፣ድካሙ ሁሉ ከንቱ ሁኖ አይሰራለትም።
ግን የተመኘው ከሰራለት ያኔ ! እነዚህ „በጠላትነት የሚተያዩና የሚፈላለጉ“
ቡድኖች ፊት ለፊት፣ የተገናኙ ቀን ደግሞ „…ደመኛ ጠላቶች“ ስለሆኑ
የሚገላግላቸው ነገር (ይህ የታወቀ ነው) አንድ እርምጃ ብቻ ነው። እሱም አንዱ
ሌላውን ቀድሞ (ሻለቃ መንግሥቱ ብሎት ጨርሶታል - ለምሳ ያሰቡንን ቁርስ
አደረግናቸው…እንዳለው) መግደልና መገዳደል ብቻ ነው።
ይህ ብዙ ቦታ ተደጋግሞ ታይቶአል።
እራሱ የቅርቡ የኢትዮጵያ ታሪክም ምስክር ነው።… ለመድገም:- ደረግና የደርግ
አባሎች እርስ በራሳቸው፣ ደርግና መሣፍንቱ፣ ኢህአፓና መኢሶን፣ ወያኔና
ሻቢያ፣ሻቢያና ጀበሃ፣ ደርግና ወያኔ፣ደርግና ሻቢያ፣ ኦነግና ወያኔ….ወያኔና
አባሎቹ…ወዘተ፣እነዚህ ሁሉ እንደ ዕውር ተያይዘው ተናንቆዋል። ይህም ማየት
ለሚፈልግ ሰው ቋሚ ምስክሮች ናቸው።
ችግሮቻቸውን፣ በአንድ ዓረፍተ-ነገር ለመናገር ለመፍታት የሞከሩት በኃይል፣
ያውም በጥይት ነው።
ለምንድነው በአውሮፓ ወይም በሰሜን አሜሪካ እንደዚህ ዓይነቱ“ጥላቻና የደም
ማፍሰስ ጭካኔ፣ በጠላትነት የመተያየት መንፈስና ሓሰቦች“ በዚያ አካባቢ፣
በመካከላቸው ዛሬ የማይታየው?
ለምንድነው የምሥራቅ አውሮፓው፣ ጸረ-ኮሚኒስትና ጸረ-አምባገነኖች የሕዝብ
እንቅስቃሴ – ከአለ የሩሜኒያው ቻውቼስኮ የሞት ፍርድ በስተቀር – አንዲት
ጥይት ሳትተኮስ በሰላም ያለቀው?ለምንድነው ለሁለት ተከፍለው ከአርባ አመት
በላይ ይኖሩ የነበሩ የጀርመን ወታደሮች ጠበንጃቸውን ጥለው በውህደቱ
ቀን የተቃቀፉት?

ከ500 ሺህ በላይ የሆኑ በደንብ የታጠቁ የራሺያ ወታደሮች ጓናቸውን
አንዲት ጥይት ሳይተኩሱ ጠቅልለው የጀርመንን መሬት የለቀቁት?
ይህን መረዳት የምንችለው“ጠላት“ የሚለውን ቃል አውሮፓያኖቹና አረቦቹ፣
ኢትዮጵያና አሜሪካኞቹ፣ ቻይናና ሕንዱ፣ እሥራኤልና ኢራኩ፣… እነዚህ ሁሉ
አገሮች የሚያዩበትን ዓይንና ግምት፣ ጠጋ ብሎ መመልከት አስፈላጊ ነው።
የሚያዩበት ዓይናቸው የተለያዩ ናቸው። ፍጹም ሌላ በመሆኑም ችግራቸውን
የሚፈቱት በተለያዩ መንገድ ነው።
በአውሮፓና በአሜሪካን የፖለቲካ ፍልስፍና „ጠላት“ ተብሎ የሚታየው፣እነደ

ጠላትም የሚቆጠረው „ ሀገር አቋርጦ፣ድንበር ሰብሮ፣ ጦር መዞ፣ ወታደር
አሰልፎ የሁሉም እናት ሀገር የሆነቺውን መሬት ይዞ ባሪያ ለማድረግ የተነሳውን፣
የሚነሳውን ወራሪ ኃይል ብቻ ነው።
ሌላውስ ? ለየት ያለ የፖለቲካ አቋም የሚያራምደውስ? ሥልጣን ላይ
ለመውጣት ተቀናቃኝ ሁኖ የፖለቲካው መድረክ ላይ ብቅ የሚለውስ ቡድን?…
ድረጅት?…ተቺውስ?ጸሓፊ ጋዜጠኛውስ?… እነሱ በአውሮፓና በአሜሪካ „ጠላት“
አይደሉም። በጠላት ዓይንም፣ እርስ በእራሳቸው አይተያዩም።
ሥልጣን ላይ ያለውን፣በሌላ በኩል እንበል አንድ የገዢን መደብ፣ ሕዝቡ በምን
ዓይን እነሱን ያያቸዋል?

እሱም ቢሆን፣ ይህኛው ገዢው ክፍል በምንም ዓይነት፣ በምዕራብ አውሮፓ ሆነ
በአሜሪካ „ተቃዋሚ“ እንጂ „ጠላት፣ ደመኛ ጠላት“ አይደለም።
ይህን የመሰለ የፖለቲካ ጥበብና ዕውቀት አውሮፓውያኖች ፈልገው ያገኙት
ደግሞ ወደ ታሪክ መለስ እንበል፣ ከጥንታዊ ግሪክ፣ ከአቴንስ ፍልስፍና እን
ከእነሱም ሥልጣኔ ነው።
ሁለተኛው „ጠላትህን እንደ እራስህ አድርገህ ውደደው“ ከሚለው ከክርስትና
ትምህርትም ነው። ሶስተኛው በተጨማሪ ከሮማ ሕግ ነው።
አቴናውያን በነበራቸውና በአገኙት የምርምር ነጻነት „..ዓይን ለዓይን፣ጥርስ
ለጥርስ „ የሚለውን የሓሙራቢን ሕግ (እስከ አጼ ምኒልክ ድረስ እኛ አገር ይህ
ሕግ፣አልፎ አልፎ በአንዳንድ ቦታዎች ይታይ ነበር) ከጥቅሙ ለአንድ
ሕብረተሰብ፣ ጉዳቱ ስለሚያመዝን እሱን ጥለውት ለመሄድ፣ ለየት ያለ መንገድ
እነሱ ፈልገው ፣ መርጠው ወስደዋል።

ከእሱም ጋር „…በሰው ልጆች ዘንድ ቂም በቀልን ለማስቀረት ፣… ለፈሰሰው
የአባት ወይም የወንድም ደም ፤… ልጅ የአባቱን ደም መበቀል አለበት“
የሚለውን ልማድ ( የጣሊያን ማፊያ አሁንም ድረስ ያደርገዋል) እነሱ ገና ዱሮ፣
እንደዚህ ዓይነቱን ልማድ አስቀርተዋል። ለምን? ምን ታይቶአቸው ነው ይህን
ያደረጉት?
ይህ አካሄድ “ አንዱ አድፍጦ አንዱን መበቀል…ዞሮ ዞሮ መጨረሻ ወደሌለው
የበቀል ኣዙሪት“ ትውልዱን እንደ ሚከት እንደከተተም መለስ ብለው ስለ
ተገነዘቡት ነው። ይከታል። ደግሞም ከቶአቸዋል።
ስለሚከትም ከዚያ „ባህልና ልማድ፣እንዲሁም ከጥንታዊ ሕግጋት“ ለመላቀቅ
የወሰዱት እርምጃ ወሳኝ እና በጣም የሚደነቅ መንገድ ነው።
ከክርስቶስ ልደት በፊት እነዚህ ግሪኮች የደነገጉት ሕግ „የሁለት ጠበኞችን ጉዳይ
በግዲያም ሊሆን ይችላል… ይህን ውዝግብ ችሎት ተቀምጦ፣ የሚመለከተው፣
የተበዳዩ ቤተሰብ ሳይሆን፣…. ዳኛና ፍርድ ቤት ነው ብለው ደንግገዋል።
“ …ያ እሱ በእኔ ዘመድ ላይ ስለአደረገው ወንጄል፣ እኔ አጻፋውን በተመሳሳይ
መልኩ፣ በልኩ እሱ እንዳደረገው፣ እኔም በዚያው መልክ መልሼ ልገደለው
እችላለሁ“ ብሎ መነሳት እንደማይችል -ይህ ነው እንግዲህ የአቴኖች ችሎታበሕግ፣እሱ ይህን ማድረግ እንደማይችል እነሱ ከልክለዋል። „ቂም በቀል
እርምጃውንም“ ማንም ከመሬት ተነስቶ እንዳይወስድ አግደውታል።
እንዴት አድርገው ነው ሕዝቡ እንደዚህ ዓይነቱን አዲስ አሰራር፣…የዱሮውን
ባህሉንና ልማዱን ጥሎ፣ በቀላሉ፣ ያኔ ጋዜጣና ራዲዮ፣ ቴሌቭዠንም በሌለበት
ዘመን እንዲቀበለው ያደረጉት?
በቲያትር ጫዋታ ነው። መድረኩ ላይ በሚታየው ድራማ ነው። „….ትረጀዲአሳዛኝ ጨዋታዎችን“ በመጫወትና እሱንም ሰው አይቶ እንዲነጋገርበት፣
እንዲከራከርበት በማድረግም ነው። ቀስ እያሉ ሕዝቡን በዚህ ዘዴ ማስተማር
ችለዋል።
በየአደባባዩ ቀንም ሆነ ማታ ማታ መድረክ ላይ በሚጫወቱት
የቲያትር ትራጀዲ ”ሚስቱን ስለገደለ፣ አንድ የልጆች አባት” ይተረካል። ይነሳል።
ሚስት ባሉዋን… ወንድም በወንድሙ ላይ ያካሄደውን የግዲያ ሙከራ፣
በመድረኩ ላይ ተመልካቹ ፍርዱን በሁዋላ እንዲሰጥ ይደረጋል። የወንድሙዋ
ገዳይ ፍቅረኛዋ ሆኖም ይገኛል።

እንግዲህ ቤተሰብ እንዳይበትን፣ ሰው በቂም በቀል ተናንቆ እንዳያልቅ፣ ጉዳዩን
የሚከታተሉ ዳኞች ተቀምጠው፣ ችሎት፣ ጉዳዩን የሚመለከት፣ መድረኩ ላይ፣
በትራጀዲ ጨዋታው ላይ ይጠራል።
አማልክቶቹ በፍርድ አሰጣጡ ላይ እንዲሳተፉበት ይደረጋል። ጎረቤቶች
አስተያየታቸውን እንዲሰነዝሩበት ይጠየቃል።…
የግድያው መነሻ ምክንያት ምንድነው? ተብሎ እዚያው መድረኩ ላይ
ይመረመራል። ሲወድቅ ነው የሞተው ወይስ በተሰነዘረበት ጩቤ፣ ተብሎ
ይጠየቃል። ባሉዋን የገደለቺው ሴትዮ እሱዋ ብትገደል (ልጁዋ ነው የአባቱን
ደም መበቀል ያለበት) ሌሎቹን ማን ያሳድጋል ተብሎ ጉዳዩ ይታያል። ልጁስ
ውድ እናቱን ለመግደል ፈቃደኛ ነው ወይ? ተብሎም ይጠየቃል።

ይህንንና ይህን የመሳሰሉ ኃይለኛ የትራጀዲ ድራማዎች „ ፍርድ መስጠት“ የነጻ
ፍርድ ቤት ኃላፊነት እንጂ፣ ማንም ከመሬት ተነስቶ በሰው ልጆች ሕይወት ላይ
መፍረድ እንደማይችል፣ አቴኖች አስተምረውበታል።
ይህም ታሪካዊ የሆነ -በሁዋላ ዓለም አቀፋዊ እርምጃ – በሕግ በደንብ ተደንግጎ
እንዲወጣም ተደርጎአል።
እንግዲህ በአውሮፓ ወይም በአሜሪካ በፖለቲካ ጥያቄ ሆነ፣ በምርጫ
“ማጭበርበር”…ሌላም ነገር ለሆን ይችላል- ሁለት ወይም ከዚያ በላይ የሆኑ
የፖለቲካ ድርጅቶች ሸንጎ ውስጥ ሆነ ከሸንጎ ውጭ ከአልተግባቡ ፣ „ጉዳያቸውን
ጠቅላይ ፍርድ ቤት አቅርበው ዳኞች እንዲያዩትና ፍርዳቸውን እንዲሰጡ –
እዚህ ይደረጋል።“
በግብጽና በኢትዮጵያ፣ወይም ሌላ ቦታ… በፖለቲካ ድርጅቶች መካከል ውዝግብ
ሲነሳ፣ በተለይ አንድ መሪ ሕገ-መንግሥቱን ጥሶ፣ ሰውን ሁሉ ከሥራው አባሮ
በእራሱ ሰዎች ሲተካ (ፕሬዚዳንት ሙርሲ ይህን አደረገዋል ኢትዮጵያም ውስጥ
ተካሂዶአል) ያኔ እንደዚህ ዓይነቱን፣ ሰው ከሥራው ሲባረር፣ ይህን እርምጃ፣
በሠለጠነው ዓለም፣ይህን እርምጃ የሚያግደው „ችሎት የተቀመጠው ነጻ- ፍርድ
ቤት“ ነው እንጅ ወታደሩ፣ፖሊሱና የአየር ኃይሉ ባለደረቦች አይደሉም።
በግብጽ እንዳየነው ወታደሩ መሳሪያውን ይዞ አደባባይ ወጥቶ የእራሱን ፍርድ
ሰጥቶ፣ሰልፈኞች ላይ ተኩሶአል። ፕሬዚዳንቱንም አስሮአል። ሌሎቹን አርፋችሁ
ተቀመጡ ብሎአል።

እንግዲህ ከዚህ አንጻር ነው የግብጽን ውስጣዊ ፖለቲካ፣ በዚያውም የሌሎቹን
አፍሪካ ሀገሮች፣ የኢትዮጵያንም ውስጣዊ ውዝግቦችና ችግሮች ማየት
የሚቻለው።
„የጠላትን፣… የደመኛ ጠላትን ትርጉም በአንድ ሕብረተሰብ፣ “በደንብ
አለመረዳት ያንን ሀገር፣…አንድን ሕዝብ፣ ሳይታሰብ መጨረሻ ወደ ሌለው
እልቂት እንዴት እንደሚወስደው፣ የግብጽም፣ የኢትዮጵያም፣ የኮንጎም፣
የሱማሌም የናይጄሪያም፣ ውስጣዊ ሁኔታዎች ሕያው ምስክሮች ናቸው።
በሌላ በኩል የኔልሰን ማንዴላ የፖለቲካ እርምጃ „ዘረኛ የነበሩ ነጮቹን
ማንከባከብና ማቀፍ“ እራሱን የቻለ ትልቅ (በጠላት ትርጉም ላይ)ትምህርት
ይሰጣል።

„ጠላት“ ማለት እንድገመው፣ ባሪያ አድርጎ ለመግዛት ከውጭ የሚመጣ ወራሪ
ኃይል ብቻ ነው። የፖለቲካ ተቃዋሚና ተቀናቃኝ ድርጅቶች „ጠላት „ ሳይሆኑ
የሀገር ልጆች ናቸው። ሕገ -መንግሥቱም በትክክል በሥራ ቢውል የመቃወም
መብታቸውን ያረጋግጥላቸዋል።
ከጠላት ጋር የሚደረገው ፍሊሚያ ጦር ሜዳ ይለይለታል። ለየት ያለ የፖለቲካ
አቋምና የፖለቲካ ፕሮግራም ከሚያራምደው ጋር ያለውን ልዩነት የሚፈታው
ደግሞ፣ እኛ እዚህ እንደምናውቀው፣ ሕዝብ ፊት ቀርቦ በሚካሄደው፣ በክርክር፣
በውይይት፣ በመጨረሻም፣በምርጫ ሂደት፣ በወረቀት ነው። ወይም ደግሞ
ውዝግብ ሲነሳ በጠቅላይ ፍርድ ቤት ነው።
„ገዢው መደብ፣ አልሰማም ብሎ እምቢ ከአለ ደግሞ፣ (በጦርነት ሳይሆን)
በሕዝብ አመጽ በተቃውሞ ሰልፍ፣ ከቦታው እንዲነሳ የደረጋል። ወጣ ወረደ

ወሳኙ ሰበአዊ መብቶች ፣ በሁሉም ወገኖች ዘንድ ይከበራሉ ወይስ አይከበሩም
ነው። የግለሰብ ሰበአዊ መብቶችን አምባገነኖች ለምን እንደማይቀበሉት
(ሌላውን ነገር ሁሉ ፣ የብሔር እኩልነትና የሃይማኖትን እኩልነት እንቀበላለን
ይላሉ) የሚያጠያይቅ ነገረ ነው።
ታቦታችን ላይ የሙሴ ጽላት ላይ “አትግደል” ይላል።
ከግብጽ የምንማረውም እሱኑ ነው። ከሣቴ ብረሃን ሣልሳዊ
© ለ አእምሮ 2005 / © Le’Aimero Copyright 2013

ሕግ፥ነክ ማስታወሻዎች / Disclaimer & Legal Statements
Le’Aimero’s Disclaimer

ዘ ጋርዲያን / The Guardian
Posted on August 29, 2013 by ለ አእምሮ / Le'Aimero

ዘ ጋርዲያን / The Guardian

[1] የዛሬ 5000 ዓመታት ይህችን የነፃነት መልክት የነደፏት አስተዋዮች ምንኛ በደነቃቸው!
***

ብዙ ሐተታ አቅራቢ ጸሓፊዎች የኤድዋርድ ስኖውድንን መረጃ ሰነዶች እንቀማለን ብለው የ ጋረዲያንን
መዝገብ ቤት አለማዘዣ ስለፈተሹት የጸጥታ ፖሊሶች እዚህ አውሮፓ ጽፈዋል።

እራሱ ዘ ጋርዲያን የደረሰበትን ችግር ከመካከለኛው ክፍለ-ዘመን ከኢንኩዜሽን
ፍርድና ምርመራ ጋር አያይዞት የሚከተለውን አረፍተ ነገር ለአንባቢዎቹ
እንደዚህ አድረጎ አስፍሮአል።
„…እሰከ ዛሬ ድረስ ቀልዳችሁብናል። አሁን ግን ይበቃችሁዋል። የመጣነውም
ሰነዱን ለመውሰድ ነው።´
በነዚህ ቃላቶች ነበር የብሪታኒያ መንግሥት በኢንተርኔት ክፍለ-ዘመን አስገራሚ
የሆነውን የሳንሱር ቁጥጥር በእኛ ላይ ለመክፈት የቃጣው። በዝግጅት
ክፍላችንም ጋዜጣችን የሰበሰበውን መረጃዎች የጸጥታ ፖሊሶቹ ልክ እንደ
የቀድሞው የስፓንያን መጽሐፍ አቃጣዮች፣ በደስታ ዓይን ነበር፣ እነሱም
ተዝናንተው ሰነዶቻችን ሲወድሙ ይመለከቱት የነበረው።
የስኖውድን መረጃዎች በዓለም ዙሪያ እንደተበተኑ ብንነግራቸውም እንኳን፣
ከደስታቸው የተነሳ ይህን እርምጃችንን ሰምተው ከቁም ነገርም አልቆጠሩትም።
የፈለጉት በመጥፎ መናፍስት ተያዙ የተባሉትን ሰዎች በእሳት ሲቃጠሉ ማየቱን
ብቻ ነው። ሌላ እነሱ የፈለጉት እኛ ይህን የቃጠሎ ድርጊታቸውን እንድናከሽፍ
ነበር።…እኛ ግን አውቀን ደስ እንዲላቸው ለቀቅንላቸው …“ ዘ-ጋርዲያን ይላል።
ቀደም ሲል ይኸው ጋዜጣ ” እነሱን የጎበኙ ነጭ ለባሽ ፖሊሶች፣ የጄምስ ቦንድ
ፊልምን እንኳን በደንብ ያዩ ይመስላሉ” ብለው ቀልደውባቸዋል።

የጀርመኑ ጋዜጣ „ሱድ ዶቸ ሳይቱንግ“ ለምን ያለ ፍርድ ቤት ማዘዣ በሩን
ለፖሊሶቹ ከፈታችሁላቸው ብሎ ጋዜጠኞን ሲወቅሳቸው፣ የራሻው ፕራቭዳ
(ይህ ይገርማል) ከዚህ ቀጥሎ ያለውን ዓረፍተ-ነገር አምዱ ላይ አስፍሮአል።
„ የጋዜጣው አዘጋጆቹ ያላቸው ምርጫ ውስን ነው። ወይ ሰነዱን አውጥቶ
እነዳለ ሁሉንም ማተም ነው። ወይም እነሱ እራሳቸው መረጃዎቹን ማውደም።
ወይም ደግሞ ጉዳዩን ፍርድ ቤት አድርሶ ከመንግሥት ጋር ጠበቃ ይዞ መሟገት
ነው።
በሦስተኛው አማራጭ ላይ የፍርድ ቤት ዳኞቹም ሰነዱን ማጥናት ስለ አለባቸው
መረጃዎቹ ምን ምን፣ ነገሮችን እነደ አዘለም ማወቅ ይችላሉ። ወጣ ወረደ ይህ
ከሆነ ዘ ጋርዲያን ከቅጣት አያመልጥም ነበር። ስለዚህ ቀላሉ እና በገንዘብ ደረጃ
ርካሹ መንገድ፣ የጸጥታ ፖሊሶቹ እያዩ፣ ሰነዱን ማውደም ትክክልኛ ውሳኔ ነው።
እንደዚህ ዓይነቱ ድርጊት ደግሞ በጋርዲያን ታሪክ ፍጹም አስገራሚ ነበር።“
„አሁን የኮሚፒውተር ቀፎና ሆድቃውን ማቃጠልና መጨፍለቅ“ ኖይ ዙሪሸ
ዛይቱንግ የተባለው የስውሲ ጋዜጣ እንደ አለው“… ምን ያደርጋል። በቀላሉ እኮ
ጠቅ አድሮ ሥፍር ቁጥር የሌላቸውን ኮፒዎችና ግልባጮቹን ማንም ሊደርስበት
የማይችለበት አገሮችና መንደሮች ወይም አህጉሮች አሸጋግሮ ማስቀመጥ
ይቻላል። ዋና አዘጋጁ አንድ ጥሩ ነገር ብሎአል። አስፈላጊ ከሆነ የተጠለፉትን
ንግግሮችና ሰነዶች ሁሉ ወደ አሜሪካን አገር አሸጋግሮ ከዚያ ሁኖ (በአሜሪካን
የፕሬስ በጣም ነጻና ሊበራል ነው) ማተም ይቀላል ነው፣ ብሎአል።“
የኖርዌዩ ዳግስአቪሰን በተራው፣ የብርትሺን ጸጥታ ፖሊሶች እርምጃ
አውግዞአል።
„….እንዲያው ጉልበት ለማሳየት የተወሰደ እርምጃ ነው እንጂ ምንም ፋይዳ
የሌለው ነገር ነው። ኃይልን ለማሳየት የብርቲሽ መንግሥት አውቆ ሕግን
ተንተርሶ፣ አሳዛኝ የስልክ ጠለፋውን ድርጊት በዚህ ዘዴ አግዳለሁ ብሎ
መድከሙ ከንቱ ነው።… ሕገ-ወጥ ሥራቸው ከተንኮል ሥራ የማይርቁትን፣
ከእሱም የማይመለሱትን፣ … ጨካኝ፣ አረመኔ ገዢዎችን አለጥርጥር፣ በደንብ
ያስታውሰናል። የጋርዲያን፣ ዋና አዘጋጁ የተናገረው ቃል ዕውነት አለው።
የእንግሊዝ መንግሥት ህገ ወጥ ሥራ፣ አንድ የሚያሳየው ነገር ቢኖር፣ ስኖውዲን
የሰበሰባቸው መረጃዎች ምን ያህል ትልቅና ከባድ ቁም ነገሮች እንዳዘሉ ያሳያል።

ጉዳዩ ለስርቦቹ ጋዜጣ “ፖለቲካ“ ለሚባለው ቅጠል ” በጣም አሳፋሪ ድርጊት
ነው” ይላል።

„…የብሪታኒያ ጋዜጠኞች የምዕራቡ ዓለም እሰከ ዛሬ የሚኮሩበትን የፕሬስ
ነጸነት፣ ሳይፈሩ ከፍ አድርገው በማውለብለባቸው ጥሩ ሥራ እነሱ ሰርተዋል።
የየናይትድ እስቴት ኦፍ አሜሪካና ታላቁዋ ብርታኒያ በዚህ የሽብረ ፈጠራ
ሥራቸው የዲሞክራሲ መሰረት የሆነውን የፕሬስ ነጻነትን ስም አጉድፈዋል።
ጋዜጠኞቻቸው ሳይሆኑ እነሱ እራሳቸው በቀጠሩአቸው ሰላዮቻቸው
መንግሥታቸውንና ሥርዓታቸውን፣ እነዚህ ሰዎች እንደሚያዳክሙባቸው
አይገባቸው ይሆን?
…ስለዲሞክራሲ ምንም የማያውቁ፣ ጭላንጭሉም እንኳን ቢሆን ምኑም
በማይታይበት አገር፣ የሚሰሩና የሚንቀሳቀሱ ጋዜጠኞች ከእንግዲህ ለእነሱ
ወዮላቸው ማለት ይሻላል። በታላቁዋ ብርታኒያና በሌሎች የምዕራብ አገሮች
የሚታየው የሳንሱር ቁጥጥር እነሱን፣ ዲሞክራሲ የሚረግጡትን መንግሥታት ፣
ይህ እርምጃቸው አደፋፍሮ ጋዜጠኞቻቸውን እንዲያዋክቡ የልብ ልብ ተመልከቱ፣ እነሱንም፤ እያሉ- የፈለጉትን ለማድረግ ዕድል ይሰጣቸዋል።
ያበረታታቸዋል።“
የቻይናን ጋዜጣዎች በዚህ ጉዳይ ላይ ምን እንደጻፉ ለመመልከት ሞክረን
ሳይሳካልን ቀርቶአል።

[1] የነጻነት

ሲምቦል (ca. 2350 B.C) /

http://sumerianshakespeare.com/21101.html

——————–
© ለ አእምሮ 2005 / © Le’Aimero Copyright 2013

ሕግ፥ነክ ማስታወሻዎች / Disclaimer & Legal Statements
Le’Aimero’s Disclaimer

ዓለም እንዴት ሰነበተች?
Posted on August 29, 2013 by ለ አእምሮ / Le'Aimero

ዓለም፣ የለም! አፍሪካ እንዴት ሰነበተች!
ሕልም ወይስ ቅዠት? አንድ አፍሪካ ውስጥ እየታተመ የሚወጣ መጽሔት
ነጮች መጥተው ይግዙን ብሎ ይለምናል!(1

ዝነኛውን „…ምኞትና ሕልም“ ተብሎ በታሪክ ላይ የተመዘገበውን የቀሲስ
ማርቲን ሉተር ኪነግ የዋሽንግተኑ ንግግር ዘንድሮ ሃምሳኛው አመት
በሚያከብርበት ወራት በአፍሪካ ጥሩ ስምና ዝና ያላቸው የአህጉሪቱ ምሁሮች
የተገላቢጦሹን ጉዞ ይዘው„…ነጮች ተመልሰው በመዳፋቸው ሥር አሰገብተው
በቅኝ ገዢነት ያስተዳድሩን“ የሚለውን ጥሪአቸውን እነሱ ለቀዋል።
ይህን የመሰለ „ልመናም“ ለመጀመሪያ ጊዜ የተሰማውና የተነበበው፣ „ቺሙሬንጋ
CHIMURENGA Chronic“ በተባለው በየአራት ወሩ እየታተመ
የሚወጣው አንድ የአፍሪካ መጽሔት ላይ ነው።
CHIMURENGA የባንቱ ቃል ነው። በዚምባቡዌም የመገበያያ ቋንቋ ይህ
ቃል፣ ትረጉሙ፣ እዚህ ለእኛ የተረጎመው „ዲ ቬልት“ የተባለው ዕለታዊ ጋዜጣ
እንደሚለው „ አብዮታዊ ትግላችን“ ማለት ነው።
በአጭሩ ይላል ጸሐፊው ይህ ቃል „…ለሰበአዊ መብቶች መከበር፣…ለፖለቲካ
እኩልነት፣…ለፍርድና ለፍትህ፣…ለማህበራዊ ኑሮ መሻሻል“ (ማመን ከተቻለ)
የቆመ ነው ይለናል።

„ቺሙሬንጋ“ በሁለት ክፍለ-ዘመን እንደተከፈለ አስታውሶ፤ (አንደኛው
በ19ተነኛው ክፍለ-ዘመን መጨረሻ ላይ ከእንግሊዝ ቅኝ ግዛት ከብሪታኒያን
መዳፍ ለመውጣት የተካሄደው የአመጽ ጊዜ ነው።
ሁለተኛው በ1960 እና 70 ዓ.ም እአአ. የካሄደውን የነጻነት ትግል ዘመን ነው )
እሱን ጋዜጠኛው አስታውሶ፣ የአሁኑን የቺሙሬንጋ „ተግባርና ሚና“ ወደ
ማስረዳቱ ይሸጋገራል።
ይህ መጽሔት በየአራት ወሩ ታትሞ በደቡብ እፈሪካና በኬንያ እንዲሁም
በናይጄሪያ ይበተናል። በኢንተርኔት ኦንላይንም ማንበብ ይቻላል።
http://www.chimurengachronic.co.za/?s=Jean-Pierre+Bekolo
ከመጽሔቱ ጀርባ በገንዘብ ዕርዳታ „ዲ ቬልት“ እንደሚለው „የጀርመኑ የባህል
ማዕከል የጉተ ኢንስቲቲውት፣ የሓይንሪሽ ቦል የበጎ አድራጎት ድርጅትና የጀርመኑ
የባህል ሽልማት ድርጅት…“ ሦስት ተቋሞች ይገኙበታል።
በሚቀጥለውም አመት፣እነደተባለው፣ በጀርመንኛ ቋንቋም ይኸው መጽሔት
ታትሞ ገበያ ላይ ይቀርባል።
„አብዮታዊ ትግላችን“ የሚለው ቃል የቀድሞ ቅኝ ገዢዎች የክሱ አግዳሚ ወንበር
ላይ አስቀምጦ በአንባቢው ፊት „ይከሳቸዋል፣ያጋልጣቸዋል፣ይተቻቸዋል…“
ብሎ የሚገምት ሰው ከአሁኑ ከአለ ትንሽ ቆየት ብሎ ወረድ ብሎ ጽሑፉን
ሲያገላብጠው ደንግጦ አፉን ይይዛል።
ከዚህ በፊት በተደጋጋሚ፣እንደ የሥነ-ጽሑፍ ኖቤል ሽልማት አሸናፊው እንደ
ወሌ ሶይንካ ያሉ ሰዎች፣እንደ የሰላም ኖቤል አሸናፊዋ እንደ የኬንያዋ ተወላጅ
ወይዘሮ ዋንጋሪ ማታይ፣እነዚህ ሁሉ “…አሁን በየአለበት ፈልቶ የሚታየው
የአፍሪካ ችግርና ችግሮች ሁሉ በአንደኛ ደረጃ ዋና ተጠያቂ የቀድሞው የአውሮፓ
የቅኝ ገዢዎች ሳይሆኑ እራሳቸው የአፍሪካ መሪዎች ናቸው…“ ስለዚህ መታረም
አለባቸው ብለው ነገሩን ጨርሰውታል። የዚህ መጽሔት አዘጋጆችም አቋም
በመጀመሪያ ላይ ላዩን ሲያዩት ይህንኑ ዓይነት መልዕክት ያዘለም ይመስላል።
ግን የፊልም ዳይሬከተሩ የካሜሩን ተወላጁ፣በ1966 የተወለደው ጎልማሣው ጃን
ፒዬር ቢኮሎ ለመጽሔቱ በሰጠው ቃል-ምልልስና ቀስ ብሎ በወረወረው
አስተያየቱ የሚገርምም የሚደንቅም ነገር አንስቶአል።

„ቅኝ ገዢዎቹ ተመልሰው መጥተው አፍሪካን ያስተካክሉአት“ ይላል። „እኛ
እራሳችን ችግራችንን ለመፍታት አልቻልንም „ ብሎም የዕርዳታ ጥሪውን ወደ
አውሮፓ ይለቃል።
„…በግልጽ እንናገር፣እኛ ብቻችን አልቻለነውም፣ስለዚህ እነሱ ብቻ ናቸው
ሚያውቁበት፣…ተመልሰው ይምጡ„ ብሎም ቅኝ ገዢዎቹን እንዲመጡለት
ይለምናል።
ጠያቂው:- „..ለመሆኑ ካሜሩን እንደገና የቅኝ ግዛት መዳፍ ውስጥ ተመልሳ
እንድትገባ ይሻሉ?..ይህንስ ይመኛሉ?“
ቢኮሎ:- „…ከሃምሳ ሁለት አመት የነጻነት አመት በሁዋላ መቀበል ያለብን አንድ
ነገር ቢኖር የእራስን ዕድል በራስ መወሰን የሚባለው ነገርና የነጻነት አይዶሎጂ፣
ብሔራዊ አመጽ…እነዚህ ሁሉ ምንምአላመጡልንም።
የዓለም አቀፉንም ሁኔታ፣… ግሎባላይዜሽንም ስንመለከተው፣
እኛን አሁን ወደፊትም ወደ ሁዋላም ለመሄድ የማንችልበት ደረጃ ላይ
አድርሶናል።
ዓላማችንና ግባችንን እንዳልመታን ግልጽ ነው። ይህን ብቻችን የማንወጣው ነገር
ነው። ሁሉ ነገር ደግሞ አሁን ከአቅማችን በላይ ነው።“
ሌላ ተጨማሪ ጥያቄ:- „..በትክክል ተረድቼዎታለሁ፣…ነጮች ተመልሰው
መጥተው (አፍሪካን) እንዲያሰተካክሉሎት ይፈልጋሉ?“
ቢኮሎ:- „ የቅኝ ገዢዎች ዓላማና ፕሮጄክት ግሩም ነበር።ብዙ ነገሮች ላይ
ደርሰናል።…ቀኝ ገዢ መሆን ተቀባይነት በአጣበት ዘመን፣ያኔ አይሮፕላኑን
የሚያከንፈው ፓይለት ቀስ ብሎ ሽው ብሎ ጃንጥላውን ይዞ በመስኮት ፈትለክ
አለ።
ሌላው እችልበታለሁ ብሎ መሪውን ጨበጠ።ግን ምኑንም አያውቅበትም።
ከነአካቴው (አይሮፕላኑን ይዞ) ወዴት እንደሚከንፍም ፕላን ስለሌው እሱ እረሱ
አያውቅም። ይመስለዋል“ ፤ ቀጥሎ እንደአለው „ …እራሱን ሲያታልል
የሚያደርገውን ሁሉ የሚያውቅ ይመስለዋል።…አንድ የሚያውቀውና የሚችለው
ነገር ቢኖር፣ የሕዝብ ንብረትን ዘርፎ የእራሱን የግል ጥማት ብቻ ማርካት ነው።
…የሐሰተኞችና የዋሾዎችም ቤት ነው።“

እንደዚህ አድርጎ ጎልማሳው ጃን ፒዬር ቢኮሎ የአፍሪካን መሪዎች በጅምላ በንቀት
ዓይኑ እየገረፈ ሙልጭ አደርጎ እነሱን እየተቸ ሲጓዝ፣ዞር ብሎ የነጮቹን የግዛት
ዘመን ያደንቃል።
„…ለባህላችንና ለጥንታዊ ቅርሳ ቅርስ ታሪካችን መጠበቅ እንኳን ገንዘብና
ሕንጻ“፣ እሱ እንደሚለው „ሰርተው የሚሰጡን እነሱ ነጮቹ ናቸው፣ …በዚህ
የጃክ ሺራክን ሙዚየም በካሜሩን አመስግነን መቀበል ይኖርብናል። ቢያንስ በዚህ
የበጎ አድራጎት ሥራ ውረሰ ቅርሳችን እዚያ ሳይጠፉ ለትውልድ ተጠብቆ
እንዲቆይ ተደርጎአል።…ግፋ ቢል የአፍሪካ ገዢዎች፣የእስክስታ ጭፈራ
ቡድኖችን አይሮፕላን ጣቢያ ድረስ እየጠሩ እነሱን ማስጨፈር ይችሉበታል።
እሱም ቢሆን የነጮች ሥራ ነው።“ብሎ አሽሟጦ ወደ ሌላ አርዕስት፣ቢኮሎ
ይሸጋገራል።
ጠያቂው እንደገና :- „ አፍሪካውያኖች እራሳቸውን ማስተዳደር አይችሉም ነው
የሚሉት?“
መልስ:- „… እቅጩን እንናገር ከተባለ ምንም ነገር ለመሥራት አልተቻለም።
ምኑም ነገር አይሰራም።…ሞከርን፣ ደከምን፣…ከአቅም በላይ ስለሆነ፣ ምኑንም
አልቻልንበትም።…እራስን በራስ መቻልና ማስተዳደር፣ እኛን ለመግዛት
የተወረወረ የውሸታሞች የፖለቲካ ጨዋታ ነው።…የአለነው በትክክል ለመናገር
የፖለቲካ እስር ቤት ውስጥ ነው፤ …ታዲያ ዝምታ እሰከ መቼ…!“
የቢኮሎ ትንተና እና ግንዛቤ „ሰምና ወርቅ“ መልዕክት ያዘለ ነው ብለው
የሚገምቱ ሰዎች አይጠፉም።በሌላ በኩል ይህንኑ የእሱን መደምደሚያ ተከትለው
„ጊዜው ደረሰ ብለው፣ ስንቃቸውን የሚያዘጋጁ ቅኝ ገዢዎችም ትንሽ አይደሉም።

„ቀልድ ነው።” እንዳይባል ልጁ አይቀልድም።”ዞሮበታል” እንዳይባል ጤነኛ
ነው።ታዲያ ነገሩ ምንድ ነው። መልእክቱስ?
ጥያቄዎች ይነሱ መልሶችም ይደርደሩ፣ ቢኮሎ እና ከእሱ ጋር ይህን የሚያስቡ
ሰዎች ፈልገው ያገኙት መፍትሔዎች ለእኛ ለኢትዮጵያውያኖች “ትክክል ነው”
ማለት አይቻልም።… ያሳፍራል። ይህ ከሆነ አባቶቻችን ለአገራችን፣
ለባንዲራችን፣ለሃይማኖታችን… ለኢትዮጵያ ነጻነት ሲሉ የሞቱላት ሞት ከንቱ
ነው ማለት ነው።

ሰበአዊ መብት፣ዲሞክራሲ፣ብልጽግና፣ ዳቦና ሥራ፣ፍትህና ፍርድ፣ሰላማዊ ኑሮ ፣
…ይህን እኛው እራሳችን በአገራችን ላይ ከተደማመጥን፣ከተስማምን እኛው፣
እንደሌሎቹ የምናመጣው ሥርዓት ነው። ደግሞ ይቻላል። ማምጣትም
እንችላለን።
ቢኮሎ (ምናልባት ሁሉም ነገር ፊልም ስለሚመስለው) ከግምቱ ውስጥ
ያላስገባቸው ብዙ ነገሮች አሉ።
„ነጮቹ ተመልሰው ቢመጡልን“ አፍሪካ „ምድራዊ ገነት“ ትሆንልናለች
የሚለው ቢኮሎ፣በምን ላይ ተማምኖ እንደሆን አናውቅም። አንድ ግን ከዓለም
ታሪክና ሥልጣኔ ተነስተን ለማለት የምንችለው ነገር ቢኖር፣ „ ቁጥጥር
የማይደረግበት ገዢ“…በህግና በፕሬስ ሥር „ቁጥጥር የማይደረግበት“ አንድ
ቡድን፣ሞራል የሌለው ኃይል፣… ጥቁር ይሁን ነጭ፣…አረብ ይሁን ቢጫው
ቻይና፣ሕንድና ጃፓን፣ እነዚህ ሁሉ አፍሪካን እንደገና ተቀራምተው ቢይዙ፣
ቢኮሎና ቢጤዎቹ እንደሚሉትና ወጣቱን አፍሪካዊ ለማሳመን እንደሚሞክሩት ያ
የተባለው „የዲሞክራሲና የሰላም፣ የብርሃን ዘመን“ ምንም ጊዜ ቢሆን
አይመጣም።
ትርፉ፣ምን አለፋን፣ትርፉ ባርነት ነው። ይልቅስ ከእግዚአብሔር በተፈጥሮ
የተሰጠንን፣ የሰው ልጆች ሁሉ እኩልናቸው፣የሚለውን፣… የመናገር የመተቸት፣
የመጻፍ የመደራጀት መብታችንን፣( ለዚህ ደግሞ ከማንም ፈቃድ ማግኘት
አያስፈልግም፣ በእጃችን በደጃችን ነው) እንጠቀምበት።
የቢኮሎ ግምትን ሁለት ጊዜ አገላብጦ ማየት አስፈላጊ ይመስለናል።
እራሳቸውን ዛሬ ሥልጣን ላይ የተቀመጡትን የአፍሪካ ገዢዎች፣እነሱን ማን በርቱ
ብሎ መርቆ እደሸኛቸው ለመሆኑ ቢኮሎ ያውቅ ይሆን?
ተፈሪ መኮንን
——————(1 -Afrika-Debatte _ Die Weißen sollen bitte draußen bleiben – Nachrichten Kultur – DIE
WELT
© ለ አእምሮ 2005 / © Le’Aimero Copyright 2013

ሕግ፥ነክ ማስታወሻዎች / Disclaimer & Legal Statements
Le’Aimero’s Disclaimer

“ራዕይ ራዕይ …. “ዶቸ ቬለ የጀርመን ራዲዮ፤ ውይይት
Posted on August 29, 2013 by ለ አእምሮ / Le'Aimero

“….ራዕይ ራዕይ…” ስንል አንዱም ሳይያዝ፣ በመሃከል ያንድ ሰው እድሜ አለፈ።
ኢትየጵያም አሁን ጥናቶች እነደሚመሰክሩት ” ከድንቁርናና ከድህነት ፈጽሞ
አልተላቀቀችም።” በጣት የሚቆጠሩ ጥቂት ሰዎች በሀገራችን በኢትዮጵያ ከልክ በላይ
ስላለፈላቸውና ጠግበው ስላደሩ፣ ህዝቡ ጠግቦ ያደረና የተመቸው የሚመስላቸው አሉ።
ዛሬ ሁሉንም ዜጋና ወገን እንደ ማንኛውም የዓለም ሕዝብ በአገሩ የፖለቲካና የኢኮኖሚ
መድረክ ሚያሳተፍበት ግልጽ የሆነ የነጻነትና የልማት የዕድገት ፕሮግራም የለም። የግል
ሀብት፣የመሬት ባለቤትንት መብት ክልክል ነው። ሕገ መንግሥቱ ላይ የሰፈሩት ሰበአዊ
መብቶች በሥራ በትክክል አልተተረጎሙም።
የፕሬስ ነጻነት የለም። የግለ ሰቦች መብቶች -አንድ ሰው የፈለገውን ለመከተል፣ለመተቸት፣
ለመቃወምና
ለመደገፍ፣ለመሰብሰብና
ለመደራጀት-ይህ ሕገ-መንግሥቱ ላይ
የሰፈረው መብቱ አይከበርም ። የነጻ-ፍርድ ቤትና የነጻ-ዳኛ ጉዳይ አለ።አንድ ሰው
ጠበቃ ይዞ በሥነ-ሥርዓቱ ሳይከራከርና በጥፋቱ ሳይፈረድበት ይወነጀላል።…
ግን ምንነቱ የማይታወቅ፣ ብዙዎቹ እንደሚሉት፣እሰከ አሁን ድረስ ምንም በቂ ማብራሪያ
ያልተሰጠው „ …ራዕይ አለ እሱን ተከተሉ” እንባላለን።
ይህ ” የአቶ መለሰ ራዕይ…የተባለው ሰነድ ” አንድም ቦታ ተጠርዞ ሲበተን አላየንም። ምን
ዓይንት መልዕክቶችን እንደያዘም እኛ በዝርዝር የምናውቀው ነገር የለም።
ይህን ጉዳይ አስመልክቶ “ዶቸ ቬለ-የጀርመን ራዲዮ ጣቢያ ” ስለ ጊዜያዊው የኢትዮጵያ
ሁኔታ አዘጋጅቶት የነበረውን አጠር ያለ ውይይት፣ እንድታደምጡት፤ መጽሔቱ „ለአእምሮ
“ ይጋብዛችሁዋል።
—————————————————https://soundcloud.com/ethiopia-leaimero/dw-discussion-ethio-poli

——————–
© ለ አእምሮ 2005 / © Le’Aimero Copyright 2013

ሕግ፥ነክ ማስታወሻዎች / Disclaimer & Legal Statements
Le’Aimero’s Disclaimer

ውርሰ፥ቅርስ
Posted on August 29, 2013 by ለ አእምሮ / Le'Aimero

ውርሰ፥ቅርስ
በየቤቱ ብዙ ሰነዶች እንደአሉ መገመት ከባድ አይደለም። የተማረው ክፍል
በሕብረተሰቡ ውስጥ ብዙሃኑን አይያዝ እንጂ፣የጽሑፍ ፊደል ከጥንት ጀምሮ
በሚታወቀውና በሚገለገልበት በኢትዮጵያ ምድር፣ ወረቀት ላይ ሳይሰፍሩ
ተረስተው የቀሩ ነገሮች አሉ ብሎ መገመት በጣም ይከብዳል። ቢያንስ
በእያንዳንዱ ቤተሰብ ውስጥ ፣ የገበሬ ቤትም ቢሆን አንድ ልጅ ለቤተ-ክርስቲያን
አገልጋይነት ይሰጣል። በዚያውም ያ ልጅ (ቁጥሩን በደንብ አናውቅም እንጂ)…
ድቁናና ቅስና ባይቀበልም ፊደል ቢያንስ እንዲቆጥር ይደረጋል።
በጥንታዊ ገዳሞቻችን እና በየቤተክርስቲያኑ አድባራት፣ ረዥም ዕድሜ ያላቸው
ጥንታዊ ጽሑፎች፣እንደ ጥንታዊው ዛፎች፣ ተደርድረው እንደሚገኙ
እናውቃለን።
ዘራቸው ሌላ ቦታ የማይገኝ፣ በቅጥር ግቢው ውስጥ የቆሙትን ጥንታዊ
የአገራችንን ዛፎች፣ እንኳን ከቅርቡ ከሩቁም አፋፍ ላይ ስለሆኑ በደንብ
እናያቸዋለን። በሌላ በኩል መጻሕፍት፣ በየአለበት አሉ ይባላል እንጂ እነዚህ
መጻሕፍት ምን እንደአዘሉ፣ ምን እንደተሸከሙ ምን ዓይነት ሚሥጥራዊ
መልዕክቶች ለትውልዱ እንደያዙ ምንም የምናውቀው ነገር የለም።…
አናውቅም።
እንደዚሁ የአገራችን ሥዕሎች፣ ድርሰቶች፣ግጥሞች፣ እራሱ የምግብ ዝግጅትና
አሰራር፣ ስንት እንደሆኑ? የት እንዳሉ? በማን እጅ እንደሚገኙ- የተመዘገበ፣
የተጻፈ ነገር ስለ ሌለ፣ ምንም የምናውቀው ነገር የለም። እንዲያው ብቻ
„…የባላበት፣የፊውዳል፣የአቆርቋዥ…ባህል…“ ጥራዝ ነጠቆች እያሉ ሁሉን
ነገር አጥላልተውት ዞር ብሎ የአገሩን ቅርስ የት ደረሰ? ምን ሆነ ብሎ የሚጠይቅ
ሰው
ጠፍቶአል።
በ19ኛውና በ20ኛው ክፍለ-ዘመን ብዙ ተማሪዎች ለትምህርት ወደ አውሮፓና
ወደ መካከለኛው ምሥራቅ ፣ወደ ሰሜን አሜሪካም እንደሄዱ እናውቃለን።
እነዚህ ሰዎች በወጣትነት ዘመናቸው ምን እንደጻፉ፣ ምን እንዳጠኑ፣ለየትኛው
የጥበብና የዕውቀት ክፍል ልባቸውንና አእምሮአቸውን ሰጥተው በዚያ እንደተሳቡ

–አንዳንዶቹ በእርግጥ ጽፈዋል- ስለሌሎቹ ብዙም የምናውቀው፣ምንም ነገር
የለም።
ጳውሎስ ኞኞ- ነፍሱን ይማረውና- አንዴ በርሊን መጥቶ ሲያጫውተን፣ ትልቁ
ቤተ-መንግሥት ውስጥ፣ ስለ አጼ ምኒልክ ታሪክ ለመጻፍ ሰነዶች ለመሰብሰብ
በደርግ ዘመን በተፈቀደለት ጊዜ ፣በቤተ-መንግሥቱ ምድር ቤቱ ውስጥ ያየውን
ነገር እንደዚህ አድርጎ ተርኮልን ነበር። መዝገቦቹ ሁሉ ተበትነዋል። በእጅ የተጻፉ
ወረቀቶች ጣውላው ላይ ወድቀዋል። ከውጭ ክረምት ስለሆነ የዝናብ ወሃ
ይገባል። አንዳንድ ብጣሽ ወረቀቶች ወሃ ላይ ይንሳፈፋሉ።አንዲት ወረቀት ብድግ
አድርጌ ስለመለከት፣የሚንስትሮች ስብሰባ ቃለ-ጉባዔ ይዘት የያዘች የንጉሡ
(የቀ.ኃ.ሥ.) ማስታወሻ ነበረች። „…እምሩ ጥሩ ብሎአል።…አበበ ተሳስቶአል።
…“
ደርግ ከወደቀ በሁዋላም አንዱ ያዳመጠውን እንደዚህ አድርጎ ሁኔታውን
አስቀምጦታል።
ሥልጣኑን በምርጫ ሳይሆን ያኔ በጠበንጃ ለሦስት የተረከቡት ድርጅቶች ( …
ሻብያም ፣ኦነግም፣ከሕዝባዊ ወያኔ ጋር አብረው አዲስ አበባ ገብተዋል) የእነሱ
ወታደሮች በዚያን ጊዜ ትልቁን ቤተ-መንግሥት የሚጠብቁት ዘበኞች፣ያለ
የሌለውን ጥንታዊ ሰነዶች፣ ለሻይ ጀበናቸው የከሰል ማቀጣጠያ እንዳደረጉት
በርከት ያሉ ሰዎች አይተዋል።
ምክንያቱ ግልጽ ነው። አለማወቅ ብቻ ሳይሆን ያው „የአደሃሪ፣
የፊውዳል…የበዝባዣ…ታሪክ ከሚለው ጥላቻ ተነስተው ነው።“ እነዚያ የከሰል
ማቀጣጠያ የሆኑ ሰነዶች ስለ ኢትዮጵያና አሜሪካ ግንኙነቶች ሊሆን ይችላል።
ወይም ስለ ሌላ ጉዳይ። ግን ዛሬ ብንፈልጋቸው የማናገኛቸው ሰነዶች ናቸው።
አንድ ስለ ኢትዮጵያ ጥንታዊ ታሪክና ባህል ለረጅም አመታት ጥናት የሚያደርጉ
አዛውንት፣ ፕሮፌሰር ሆህናዚ የሚባሉ ምሁር „ገንዘብ ከአለህ ኢትዮጵያ
ስትወርድ ያገኘኸውን ቅርሳ ቅርስ ዝም ብለህ ግዛ፣ ወደፊት በቀላሉ የማታገኙት
የአገሪቱ ንብረታችሁ እየተዘረፈ ነው“ ብለው መክረውኝ ነበር። ይህን ለማድረግ
(ሮከፌለር ወይም ቢል ጌት መሆን ያስፈልጋል) የአንድ ሰው ሥራ አይደለም።
ይህን ማድረግ የሚችለው መንግሥት ወይም ብዙ ሰዎች ሰብሰብ ብለው
የሚያቋቁሙት „ትሪስፓረንት“ ግልጽ የሆነ አባሎቹ በየጊዜው የሚቆጣጠሩት
የበጎ አድራጎት፣የሽልማትም ድርጅት ሲመሰረት ነው። ለዚህ ደግሞ በወር አንድ
ዶለርም በነፍስ ወከፍ ማዋጣቱ በቂ ነው።

ለምንድነው ይህን ጉዳይ የምናነሳው? ለትውልድ የሚተላለፉ ጽሑፎች የት
እንዳሉ አናውቅም ብለናል። የሚታወቁትም ምን እንዳዘሉ እነደዚሁ ስ እነሱ
የምናውቀው ነገር የለም ብለናል። የአገራችን ሰዓሊዎች የሳሉት ሥዕሎች
ተሸጠው በዓለም ዙሪያ ተበትነዋል። አንደ ቤተ መንግሥቱም ሰነዶች እነሱም
አልተመዘገቡም ብለናል።
የትምህርትና ሥነ-ጥበብ ሚኒስትር ተመራቂ ተማሪዎች ብዙ ናቸው። ሥራቸው
የት ገባ? የትይገኛል?… ቢያንስ በምዝገባ ሥራ አንዳንድ ነገሮችን መጀመር
ይቻላል።
እንዳው ለመነሻ ያህል፣

አምባሳደር ብርሃኑ ድንቄ፣ እአአ 1965፣ ለንጉሠ፥ነገሥቱ
የጻፉትን አቤቱታ እዚህ እትም ውስጥ አካተነዋል።
*

የአምባሳደር ብርሃኑ ድንቄ ደብዳቤ ፣ ለንጉሠ፥ነገሥቱ (1965)
Posted on August 29, 2013 by ለ አእምሮ / Le'Aimero

አምባሳደር ብርሃኑ ድንቄ
ኢትዮጵያን ያገለገሉ ናቸው።

ለረዥም

ዘመናት

በአምባሳደርነት

አገራቸውን

ገና ጥዋት፣ በኢትዮጵያ ሀገራችን ዛሬ የምንመለከታቸው የህዝብና የአእምሮ ትርምስ
ከመድረሱ በፊት፣ ለኢትዮጵያ መልካም አስተዳደር በመመኘት ለንጉሠ፥ነገሥቱ የጻፉትን
ደብዳቤ ለመዝገብና ለማገናዘብ ይሆን ዘንድ፣ ያላችሁት እንድትመለከቱት በእጅ
የተጻፈውን ሰነድ አስቀምጠነዋል።
በተመሳሳይ ጉዳይ ላይ እነ ጄኔራል አብይ አበበ፣ እነ አቶ ሓዲስ ዓለማየሁ፣ እነ ልዑል
አሥራተ ካሣ፣ እንደ ደጃች … ተክለ ሐዋሪያት የሰነዘሩአቸው ሐሳቦችም አሉ።

የአምባሳደር ብርሃኑ ድንቄ ደብዳቤ
——————–
© ለ አእምሮ 2005 / © Le’Aimero Copyright 2013

ሕግ፥ነክ ማስታወሻዎች / Disclaimer & Legal Statements
Le’Aimero’s Disclaimer

Ethiopia to Yemen – The Most Dangerous Journey on
Earth (BBC)
http://www.youtube.com/watch?v=ihQ4oL4Iwf4

Posted on August 29, 2013 by ለ አእምሮ / Le'Aimero

——————–
© ለ አእምሮ 2005 / © Le’Aimero Copyright 2013

ሕግ፥ነክ ማስታወሻዎች / Disclaimer & Legal Statements
Le’Aimero’s Disclaimer

እስክንድር / Tribute to Skunder Boghossian
Posted on August 28, 2013 | Leave a comment

http://www.africa.upenn.edu/Smithsonian_GIFS/Boghossian.gif

እስክንድር፣
በኪነ ጥበብ ፀጋው፣ ማዕከሉ ላይ ያለችውን ሰላም ለማግኘት፣
በዘመናችን ያለውን አምባ ጓሮ፣
ከንቱ ዕልቂትና ውዳሴ ሲያስመዝግበን ይሆን ?

አዎ ሰሚ አእምሮ ካገኘ!
____
Boghossian was born on July 22, 1937 in Addis Ababa, at the time the capital of the Italian
colony Italian East Africa, one and half years after the Second Italo-Abyssinian War.[1] His
mother, Weizero Tsedale Wolde Tekle, was Ethiopian.[1] His father, Kosrof Gorgorios
Boghossian, was a colonel in the Kebur Zabagna (Imperial Bodyguard) and of Armenian
descent.[1] Kosrof’s father, Gregorios Boghassian, an Armenian trader, had established a
friendship with Emperor Menelik II and worked as a traveling ambassador in Europe on
behalf of the Emperor.[4]
Boghossian’s father was active in the resistance against the Italian occupation and was
imprisoned for several years when Boghossian was a young child.[1] His mother had set up a
new life apart her children and although both he and his sister Aster (Esther) visited their
mother frequently, they were raised in the home of their father’s brother Kathig Boghassian.[4]
Kathig, who was serving as the Assistant Minister of Agriculture, together with other uncles
and aunts brought them up during their father’s imprisonment.[4]

He attended a traditional Kes Timhert Betoch kindergarten where he was taught the Ge’ez
script.[1] In primary and secondary school, he was taught by both Ethiopian and foreign tutors
and become fluent in Amharic, English, Armenian and French.[1] He studied art informally at
the Teferi Mekonnen School.[5] He also studied under Stanislas Chojnacki, a historian of
Ethiopian art and watercolor painter.[5]
READ MORE
https://www.google.de/search?q=Skunder+Boghossian-and-more
SKUNDER
Celebration of Art & Culture
——————–
© ለ አእምሮ 2005 / © Le’Aimero Copyright 2013

ሕግ፥ነክ ማስታወሻዎች / Disclaimer & Legal Statements
Le’Aimero’s Disclaimer

TRIBUTE