Sie sind auf Seite 1von 44

1

የተመረጡ አጫጭር ፅሁፎች ስብስብ

እትም-14 ነሐሴ| 2012


2

አዘጋጆቹ
የኔማ ጌታ የሰጠኝ ስንዴ
ገና ሳልበላዉ አበጠ ክንዴ
ወይ የኔ ጌታ የሰጠኝ ሙክት
እግንባሩ ላይ አለዉ ምልክት
መስከረም ጠባ እሱን ሳነክት

ፌስ ማስክ ያረጉ ቡሄ ጨፋሪዎችና ምናልባት በ100 አመት አንዴ ያየነው የ12/12/12


ግጥምጥሞሽ የነበረበትን የወርሃ ሐምሌ አጋማሽ የአጤሪራ 14ኛ ዲጂታል መፅሔትን
ወደእናንተ ስናደርስ እንደተለመደው ለተሳትፏችሁ እያመሰገን ይህንን ኮቪዳም አትክን
አመትና አልቃሻ ክረምት የቡሄው ችቦ ወደመጪው ብርሀናማ አመት መሻገሪያ ብርሀን
ይሁናችሁ ብለን እንመርቃለን፡፡ በሙሉሙሉ ፋንታም አጤሪራ ቅፅ 14ን እነሆ ብለናል።

*ይህ በእንዲህ እንዳለበዚህ እትም ፅሁፋችሁ ያልተካተተ ወዳጆቻችንን በጣም ተንዛዝቶ አንባቢ እንዳያሰለች
ለሚቀጥለው እትም አቆይተነው እንጂ ችላ ብለን አይደለም እያልን ይቅርታችሁን እንለምናለን *
መልካም ንባብ
ተካኢ ሃይሌ
ኪሩቤል አጥናፉ

Telegram | https://t.me/aterira
Facebook | https://www.facebook.com/aterira
Call | +251 925 749 956
እትም-14 ነሐሴ| 2012
3

እትም-14 ነሐሴ| 2012


4

FIGHT OR FLIGHT
SELMAN HUSSEIN

I’m one of those people who “discovered” Tweeter during this Pandemic. I
don’t really have much interaction but, even as a “follower”, it’s a fascinat-
ing place. A place where accounts are verified, ideas go viral much more
easily and words count. And if you are a football fan, it’s all more interest-
ing. But enough beating around the bush and let’s cut to the chase.

I recently noticed a trend of this sort in this la la land:

I was 11 and it was my cousin


12 and it was a family friend
14 and it was my teacher
17, a stranger
...
and the list goes on.

Reading these threads, I couldn’t help but dwell between two sensations.
One, of course, was a mix of melancholy and empathy. I imagined the hor-
rors a young girl had to endure making her way in this brutal world. There
really is no room for justification. This is truly depressing. And savage. It
must STOP. Enough is enough!

A bit deep in my consciousness, however, I felt something was wrong


about this whole “movement”. A suppressed voice in the back of my head
labeled this trend as a yet another manifestation of our mob mentality as a
society. After all, what good is celebrating this horror show as if you could
stop it by complaining about it? You were fortunate, educated and articu-
late enough to voice your protest, but what of those silenced women who
can’t afford even that? What good will your trendy movement do them ex-
cept, perhaps, triggering their oppressors into being more cautious “next
time”? Is it not better to tune down the rhetoric’s and focus on practical
solutions such as strict legislations and empowering women, both literally
and figuratively?

እትም-14 ነሐሴ| 2012


5

I couldn’t stick to either sensation for long. As with most extreme argu-
ments, I thought there could be a benign middle where these opposing
lines of thought converge, somehow. I needed to borrow some skills from
Sherlock Holmes to reach that sweet spot. Or so it appeared.

My first impression could be driven by a desire to identify with the new


politically correct idea; a fear from being left out the social progress; a syn-
thetic empathy or call it what you may. After all, what are most of the ideas
we fight for such as fairness, freedom and the law if not social constructs?
imagined orders?

Perhaps, that naughty voice at the back of my head was just guilty con-
science trying to avoid pointing fingers. I may have sexually harassed a girl
at some point in time or another, even in the mildest sense of the term,
and this is me avoiding confrontation. After all, what kind of a monster
blames a rape victim? Would I still argue if the assaulted was someone
close to me?

It might be the case that, perhaps, eliminating the contradiction in this


issue is not in anyone’s best interest. Both extremes could check and bal-
ance the other while pragmatic solutions are sought. The romantic left
could sit opposite to the bold right and monitor the actions of leaders, in
the middle, to alleviate oppression and bring about a hospitable society
for every member.

Therefore...

Ladies, I’m sorry you have to go through all this horror. I’m sorry for the
part I play in it. Say No to sexual harassment, and rightfully so. But don’t
just stop there. Focus on practical solutions. Don’t wait for empathy from
someone who will harass you the next day. This is a broken world. Learn to
defend yourself. Teach your daughters as well. Sue the bastard! Or call him
out. And, of course, the law should be strict enough to provide protection.

And boys, whenever you wine about a girl leaving you without a warn-
ing, try to imagine the kind of shit she lives through; the catcalling on the
streets, those predatory looks in every corner and the unsettling status
quo that conditioned her into a constant fight or flight mode. Perhaps the
እትም-14 ነሐሴ| 2012
6
part you had to play in your sudden break up was insignificant compared
to the baggage she is carrying. Perhaps it’s not entirely your fault. Perhaps
you were just a trigger.

Let that be a solace to you both. And an alarm.

እትም-14 ነሐሴ| 2012


7

አበሻ እንደሆነ ፥ ሴክሥ አይወድ


• HABESHA WAY OF SEXUALITY.
ልዑል ፡ ዘወልደ
የወሲብ መፅሔት መጀመሪያ ያየሁት ስምንተኛ ክፍል ሳለሁ ነው ። አማርኛ አስተማሪ
ቀርቶ ይመስለኛል ፥ ክፍሉ ገበያ ሆኗል ። እሙ የምትባል የመጨረሻው ረድፍ ተማሪ
በጇ የተጠቀለለ መፅሔት ይዛ ወደኛ መጣች ። በግዜው የምናውቀው ዘመናይ መፅሔት
የአየር መንገዱን “ሰላምታ” ነው ። ለፈተና ምናምን ይዞ መምጣት መጨረሪያም ሆና
ነበር ። ዝም ብዬ እኮ ነው የምማረው ባቋርጥ ራሱ እጣዬ እንደአባ ውቅያኖስ ለውቂያኖስ
ማቋረጥ ነው ፥ ምናምን እንደማያ ።

በዴክሳችን ሁለት ወንድና አንድ ወንድም ሴት እንቀመጣለን ። በቀኝ ጥግ ግድግዳው


ያዋስነናል ። መሀል መግባት ምቾት ስላልሰጠኝ እሙን አሳልፌ በመውጫው ዳር
ተቀመጥኩ ። አቻ-ለአቻ ለአራት ተሰግስገን ተቀመጥን ።

-የሆነ ነገር ላሳያቹ ነው

-ምን

-ተረጋጋ እስኪ ፥ ጉዳዩን በፎቶ ላስከልማችሁ

- ኧ...ረ ?

ከዛ በፊት አንድ ሁለቴ የዴክ ካሴት አልቆ ሳጠነጥን ጉዳዩን (ተውኔተ ወሲብ ) አይቻለሁ
። መጀመሪያ አንደመደንገጥ አርጎኝ ነበር ፥ ምን ጉድ ነው ? አይነት ። ድንጋጤው ሲበርድ
ተደብቆ የጉዱን ጉድ ማየት ጀመርኩ ። የተደበቀን የመሻት ጉጉት ይሁን ተፈጥሯዊ
የጉርምስና ሽፍደት እርግጠኛ አልነበርኩም ።

በፊልሙ ላይ አንዲት የመረብ ታይት ያደረገች የቢሮ ፀሐፊ ለአለቃዋ የነበራትን ፍቅር
በየአቅጣጫው በመተተጣጠፍ ስትገልፅለት ያሳያል ። ከዛን ግዜ አንስቶ አለቆችና ፀሐፊ
የተለየ ግኑኝነት ሊኖራቸውም እንደሚችል መገመት ጀመርኩ ። አሁን እንዲህ የተባ
እውቀት ከወዴት ይገኛል ?

( *ስለVHS ፊልሙ እመለሳለሁ የክፍሉን ዛንታ ልጨርስ)

ክፍሉ ውስጥ የነበረው ጫጫታና ወከባ ምቾት ሰጥቶናል ። እሙ መሀል ገብታ አንድ
በአንድ እየገለጠች አስኮመኮመችን ። ለአራት እንዳቀቀረቅረን አረ በስማምዬ! እያልን
ጉዳዩን አየን ።

እትም-14 ነሐሴ| 2012


8

ከየትአባቷ እንዳመጣችው እንጃ የፎቶ ጥራቱ ውል ያለ ነው ። የፎቶ አነሳሳቸው ግን ግራ


አጋቢ ነበር ። መጀመሪያ ለመለየት ተቸግሬ መፅሔቱን በየአንግሉ እያዟዟርኩ አየሁ ።
በፎቶው የሚታዩት እንደ ሒንዱ ጣኦቶች ብዙ እግርና እጅ ያላቸው መስሎኝ ሁላ ነበር
። ልብ ስል ለካ አንድ ሰው ከብዙ እየባለገ ነው ። የጦሳ ያለህ ፥ ተንቀልቅለው ያወቁትን
መደምሰስ አይቻል ነገር እስከመጨረሻው እየገለጥን ብዙ ጉድ ገበየን ።

ልክ እንዳለቀ በረጅሙ ተሳሳቅን ። ሳቁ እሙ ጀምራው ያጀብናት እንጂ ፈልገን ያመጣነው


አልነበረም ። ውስጣችን የተለኮሰ የማናውቃት ስሜት መሸንገያ ነው ፥ ተሳካልን ነገር ።
ፈገግታችን ፊታችን ላይ ሳይሻግት የሶስተኛው ፔሬድ (*ክፍለ ግዜ ማለት አልወድም ፥
ደስ የማይል ስነ-ስርዓት አለው) ደውል ተደወለ ። እሙ ወደቦታዋ አልፋ የግድ መሄድ
ነበረባት ። እኔ ሆዬ ደግሞ ከፈቃዴ ውጪ የከናዳሁት ነገር ነበር ። እግዜር ይስጣት ፥ እንደ
የባርቴንደር በር አወዛውዛው አለፈች ።

(ስለፊልሙ ደሞ እንቀደድ)

ከአጋጣሚው ወዲህ ፊልም ሁሉ ወሲብ ተደምስሶ የሚቀዳበት መስሎኝ ነበር ። የካስት


መውጣት ማሳረጊያ ሳይሆን የመሻት (curiosity) መቅድም ሆነ ። የዴኩ አልማዝ ቃ
ብሎ እስኪያቆም አጠነጥናለው ። ቀስ እያልኩ ልፋት ለመቀነስ ከመጨረሻ ወደኋላ ማየት
ጀመርኩ - ሃሃ ።

የዛን አይነቱ አጋጣሚ በቀላሉ የሚገኝ አልነበረም። ያለኝ ምርጫ ያየሁትን እራሱን ደግሞ
መከራየት ነበር ። ለጓደኞቼ ሁሉ እየጠራሁ በምስጢር አሳየኋቸው ፥ ከአንዱ ጓደኛችን
በቀር *የባለጌ ነገሩን የጠላ አልነበረም ። እንደውም ብዙ ምርቃት አተረፍኩ ።

ጥሩው ነገር ከዛን ኋላ በግልፅ ማውራት ተለማመድን ። አንድ ግዜ አንድ ጓደኛችን


ግለወሲብ በየቀኑ እንደሚያደርግና አይኑ እንዳይጠፋበት መስጋቱን አወራን ። ድርጊቱን
ከማብዛቱ የተነሳ እግሩ መሀል ህማመ ላሽ ሁሉ በልቶታል ። ልጁ የሰንበት ቤት ተማሪ
ሲሆን ከሁላችን በላይ ተከርክሞ ተገስፆ ያደገ ነው ። መኝታ ቤቱ በቅዱሳን ስዕል
በመሞላቱ ጉዱን ያላየ ቅዱስ አልነበረም ። ይሄ ይሄ ነው መሰለኝ ሲያወራን የሐጣን
ስሜት ይጫነዋል ።

ድርጊቱን የሚፈፅመው ሁሉ በዓይነ ኀሊናው ነው ። ልቡ የፈለጋትን ሴት በምናቡ


ይስላል ፥ ከዛ በወዛ እጁ ይዳራታል ። የገረመን ወላ በህሊናውም ቢሆን ከዛች ሴት ውጪ
አይወሰልትም ። በጣም የገረመን ደሞ ሴቲቱን የምናውቃት ፣ ምንፈራትና ትልቅ መሆኗ
ነው ።
.
.
.
እትም-14 ነሐሴ| 2012
9

ምክትል ዳይሬክተራችን - ሃሃ

ከቅርብ ግዜ ወዲህ ኤፍኤሞች በግብራሰናያት ፈንድ ስለወሲብ በግልፅ ማውራትና


ማስተማር ጀምረዋል ። በጉረምስናችን ወቅት ስለ*Sexuality ( በአማርኛ ቃል ላገኘ ወሮታ
ከፋይ ነኝ ) የተማርነው ራሳችንን በማጤን ወይ ደሞ በደመነብሳዊ አጋጣሚ ነው ። እጅግ
ብዙ ነገሮችቻችን ድብቅ ናቸው ። ሴቷ ስለወር ፅጌዋ አይነገራትም ። ወንዱ ልሙጡን
አንሶላ በህልመሌት ኮኮብ ስሎበት ያድራል ፥ ያው ፖለቲካ ነው ነግቶ አያወራውም ።

ክቡሩ የወሲብ እውቀት ዋጋ እንደሌለው ነው ። ስለወሲብ ትምህርት ሳስብ የማስታውሰው


ሰው አለ ። የፀረ ኤች አይቪ ክበብ አባል ሳለሁ የገጠመኝ ነበር ። የዛሬን አያርገውና
ወጣቶችን ስለኮንዶም አጠቃቀም ከእጨት በተሰራ ቆለጥ አስተምሪያለው -ሃሃ

ታዲያ አንድ ሰውዬ ይመጣና ሚስቱ በሁለት አመት ሶስት ልጅ ወልዳበት ግራ እንደገባው
ያማክረኛል ። የቤተሰብ ምጣኔ ቢሮውን ጠቁሜው ተለየሁት ። ከአመታት በኋላ ስታዲየም
ሰልፍ ላይ ተገናኝተን ጠየኩት ። ሰውየው ፥ አመስግኖኝ አላቧራ አለ ። ሰልፉ ስላሰለቸኝ
ወሬ አሰፋሁ ...

-የሚቀበር መዳኒት ጀመራቹ ወይስ መርፌ ?

-ኧረ የለም ፥ ምንም ነገር አልወሰድንም ።

- እንዴት ? ያን ቀን ሀኪም አላየህም እንዴ ?

- ኧረ በጭራሽ ። በሩ ላይ የተለጠፈውን አንብቤ ነው የሰመረልኝ ።

በወቅቱ የቤተሰብ ምጣኔ ምክር አገልግሎት በር ላይ የተለጠፈውን ለማስታወስ ሞከርኩ


። ከተለያየን ከሰዓታት በኋላ ቆይቶ መጣልኝ ።

“ እባክዎ በሚቀጥለው መግቢያ ይጠቀሙ ! “

እ...ግ...ዚ...ኦ !

እኛ አገር እንዲህ ነው ። ወሲብ የሌለ ይመስል ትምህርቱ ነውር ሆኖ ቆይቷል ። ጥቃቅን


ኤሮቲክ አርቶች ራሱ ነውር እንደሆኑ ነው ። በበይነ መረብ ሞዴሎች ፎቶ ሲለቁ ከስር
የሚሰጠውን አስተያየት ማንበቡ ይበቃል ። በድፍረት ኑድ ሆና የተወሰነች አንድ
የማስታውሳት ተዋናይ ጭራ ቀረሽን ነው (*ርዕሱ በጠፋኝ የአውሮጳ ፊልም)

ኢህአዲግ በገባ በሰማንያዎቹ መጨረሻም ኤሮቲክ አርት ተፋፍሞ ነበር ይባላል ። ጋዜጦች
ቢኪኒ ያረጉ አክትረሶችን በፊት ገፃቸው ያወጡ ነበር ። የነስብሃትና ሌሎች ላፓሪዚያን

እትም-14 ነሐሴ| 2012


10
አብዮት እንደሆነ እገምታለሁ ። ብቻ በነሱ ትግል በሌሊን ዲስኩር የደነዘዘው ህዝቤ
የሽፍደት ረሃቡን አስታግሷል ።

ህቡዕነት ለጭዋነታችን በጎ ነው ወይስ ወሲባዊ ጥቃቶች ደጅ እንዳይወጡ መደረዣ


ምክንያት ነው ? በሚል አንከራከርም ። የዛሬ ሀሳቤ Sexuality ብቻ ነው ፥ ይደርልን ።

ወደ ቀደመው ወሬ ስንመለስ ፥ ያንኑ መከረኛ ፊልም ደጋግሞ መከራየቱም ሆነ አከራዩን


እንዴት ያለ ልብ የሚነካ ፊልም መሰለህ እያሉ መሸንገል ያሳፍረኝ ገባ ። መፍትሔ ሆኖ
የታየኝ ካሴቱን አስቀርቶ ከአከራዩ ጋር መጣላት ነው ። አደረኩት ። በዛ ቪድዮ ቤት
ማለፉም ቀረ -ሃሃ

ታድያ አንድ ግዜ አጠንጥኜ ያስቀመጥኩትን ቪ.ኤች.ኤስ ሰራተኛችን የሰርግ ቪድዮ


ማህደር ውስጥ ትከተዋለች ። የአጋጣሚ አሽከርነት ከገጠር ዘመዶቻችን መጥተው አባቴ
አውጥቶ ይከፍተዋል ።

( እስክመጣ ምን እንዳሉ አልፃፍኩትም ፥ ጠንቋይ አይደለሁ በምን አውቃለሁ)

አይመሽ የለን መሸና አገር ሰላም ብዬ እያፏጨሁ ስገባ ዘመድ አዝማድ አይኑ እኔ ላይ ነው
። እንዳየኋቸው ከአደነጋገጣቸው የሆነው ሁሉ ገባኝ ። የመጨረሻ ቃሌን አወጣሁ ።

- እሺ የመጥፊያ ብር ስጡኝ ... ሃሃሃ

እትም-14 ነሐሴ| 2012


11

KALKIDAN GENET

God created man in his likeness


In Divine curiosity
He placed the tree of knowledge in the center of Eden
And waited
For man to ask
But nothing

Then God created a woman


He placed ambition within her heart And
she didn’t fail him
The man and his woman left heaven
To fulfill the word
So God would step a foot on earth

Ever since
God sins through Man carrying the ancestral sin
Fulfilling his interest without having to be a man himself
And the man goes to Sunday churches to confess his questions
Of being a first time human
“Forgive me father for I have sinned” he’d say
When in fact he did nothing but lived

That wasn’t enough


Man had to question beyond creation
To question his name
His place
His skin
His vision
His creator
እትም-14 ነሐሴ| 2012
12

God put an ultimatum


Between heaven or hell
Threatened that the questions would trace back to him

God put prayer in man’s heart


So he keeps track of his intentions
But man had long forgiven himself
And the woman had become too liberated

Man prayed in tongues instead


Worshiped In between thighs
Confessed in the fire by the end of his cigarette and at the bottom
of bottles
And man and woman understood earth
They created a place between the ultimatums
And drove God back to the heavens

On the seventh day,


God rested for
Man created until
Eternity

እትም-14 ነሐሴ| 2012


13

እትም-14 ነሐሴ| 2012


14

ዲር ፒሰስ...
BEZ BROWN

ፆም ገባ እኮ አትፆሚም ይሉኛል:: እቺን መከረኛ መሀተብ ካንገቴ እያዩ ...በረቡእ


አጣፍጬ በጠበስኩት ጥብስ ጣእም ያጣ ህይወቴን ላጣፍጥ አድፍጬ ሲያዩኝ
ተገርመው

እየፆምኩ እኮ ነው:: አንተ በሌለህበት ምን ፍስክ አለና? ከፍቅር ...ከእቅፍ ...ከመሳም


ከመተሻሸት ...ከድምፅህ ...ከቅርበትህ ...ከጠረንህ ...ከሜንት ትንፋሽህ ...ከቀልድህ
ከንግግርህ .....እየፆምኩ ነው::

ብታይ

(ማህተቤ)መስቀሌ ተሸረፈች

ከሄድክ በሁዋላ ...ካንገቴ ላይ አውልቄ ፀጉሬን ሸብ አደረኩባት... ያንተን ንዴት


በሷ ልወጣ ..ልንቃት ፈልጌ ባንተ የገባሁትን እልህ በሷ ላክክሰው ጨፍራራ ፀጉሬን
ሰብስቤ አንዴ ሸብ ሳደርግባት የትንሽዬ አካሏ ግማሽ እጄ ላይ ቀረ::

ከመሰበሯ በፊት ...የተጣላን ሰሞን አያቴ ቤት ሶፋ ላይ ቀስ አድርጌ ጥያት


ወጣሁ:: እሷን እንዳንተ አንቅሮ መተው ቀላል አልነበረም:: ለምን ብትል ሳትሰለች
አንገቴ ዙሪያ ተጠምጥማ አቅፋኛለች:: ያለ ቦታዋ አንገቴ ላይ ስትቀመጥ
ማንነቴን አታንፀባርቂውም ሀሳብሽ እና እኔ እንቃረናለን ብላ በመስቀልነቷ
አልተመፃደቀችብኝም:: መስቀል ሳልሳለም ቤተስኪያን ደጅ ሳልረግጥ አንድ ሳንሆን
አንድ ላይ ቆይተናል ...ይታይህ እንግዲህ ...ያውም አቅፋኝ እኮ ነው::

እና ልቤ ስብር ያለ ግዜ ... በውስጥ ለውስጥ ብስጭት ራሱን ባልገለጠ ሀዘን


...አይታኝ እንደምታዝንብኝ ነፍስ እንዳላት ነገር ቀስ ብዬ ከኪሴ አውጥቼ ሶፋው ላይ
ጥያት መአት ታክሲ ተሳፍሬ ቤቴ ሄድኩ::
በበነጋታው ከአጎቴ ልጅ የደራ ወሬ መሀል <<እንኪ መሀተብሽን ረስተሽ >> ተብዬ
እጄ መሀል በትዝብት ተመለሰች:: ጡቶቼ መሀል ለብቻዬ ሳይሆን በኩራት ከሹራቦቼ
በላይ አኖራት ነበርና የሚያውቀኝ ያውቃት ነበር:: አንድ ቀን ነው ጥላኝ ያደረች... ከዛ
በሁዋላ ግን ይመስለኛል ቅር ብሏታል ...ሁሌም ፊቷ ወደጀርባ ይገለበጥ ጀመር::

ደሞ ሌላ ግዜ ትዝ ብለኸኝ ጨለማ መሀል ቆሜ ስተክዝ የቅርብ የአንተ ተወካይ እሷ


ነችና አሽቀንጥሬ ወደማይታየኝ ጥቁር ፅልመት ወረወርኳት ..

እትም-14 ነሐሴ| 2012


15

በነጋታው በሬን ስከፍት የጠዋቷ ፀሀይ ሳትስመኝ በፊት የቤቴ በር መክፈቻ ላይ


ተንጠልጥላ አገኘሁዋት.... ስጠይቅ አባቴ ካትክልቱ መሀል አንስቶ እንዳስቀመጠልኝ
ነገሩኝ::
አልቅሳለች መሰል በውሀ ብስብስ ብላለች::

ለመጨረሻ ግዜ ልረሳህ ደቂቃዎች የቀሩ ቀን ባለሁ ግዜ ያልተፃፈልኝ ቅሽርሽር


የይቅርታ ደብዳቤህ ደረሰኝና ምንም የማይለወጥ ስሜቴን የማይመታ ልቤን
እንደበፊቱ የማይርዱ ጣቶቼን እየታዘብኩ አንብቤ ስጨርስ ስለሌለ ነገኣችን
እርግጠኛ እንድትሆን አስቤ ልፅፍልህ በእልህ ጨፍራራ ፀጉሬን በሷው ሸብ አድርጌ
ስክርቢቶ ላነሳ ስል ስሜቴ ላይ ትንሽ ብሽቀት እና ለምስኪን አካሏ የማይገባ ሀይል
ነበረበትና

ቀሽ አለች..
ምፅ

ትንሽዬ ጉማጅ አካሏን መዳፌ መሀል አስቀምጬ ሁለት ነገር አሰብኩ..


1 ልቤን ትመስላለች::(አሰባበሯ)
2 እየበነነ የጠፋውን ላንተ ያለኝን ስሜት..

(የመጨረሻው ቻው)

እትም-14 ነሐሴ| 2012


16

KALKIDAN TADDESSE

ዛሬ ባንዲት የግራር ዝንጣፊ ምርኩዝ ላይ ተመክቶ የሚውተረተር ሰውነቴ ፤ ትላንት


ከመሰሎቿ ተለይታ ሌላ አለም ፍለጋ ልትወጣ ስትል የታሰረች ፤ ግን ከውስጥ መሽጋ
እድሜ ሳይሰባብራት ወጣትነቷ ላይ የቀረች ኮረዳ ሰውነት አይመስልም።

ይቺዋ እኔ ከብዙ አመታት በፊት ከስምንተኛ ክፍል ትምህርቷ ፣ ወንዝ ወርዶ ውሀ


ከማመላለስና ከእናት ስር እየተርመሰመሱ ቤተሰቡን ከመንከባከብ የየቀን ስራዋ
ተመንጭቃ ለባል ስትሰጥ ፤ አልገባቸውም እንጂ አካሏን ለነሱ ሰጥታ በራሷ የነፃነት አለም
ውስጥ የጠፋች በራሪ ናት።

ከለውጥና ከእንቅስቃሴ የራቀ የገጠር መንደር ውስጥ ከትሜ እዚሁ ሳረጅ ፤ ውስጤ ግን
ከመንደሯ ራቅ ብለው ጎጆ የቀለሱ ፤ ማረፊያ ሲያሻቸው ብቅ የሚሉ ከተሜዎችን ሀገርና
ኑሮ ብቅ ሲሉ በጣሉላት አሮጌ መፅሀፍት ውስጥ ተዟዙራ እየታዘበች የምትደመም ተጓዥ
እኔ ተቀምጣለች።

አራት ቆንጆ ልጆችን አሳድጌ ቀን ከሌት እኔ ያላየሁትን አለም እየሰበኩ ሳጎለምሳቸው ፤


የተደላደለ መንገድ ተጠርጎ ይጠብቅልኛል የሚል የሞኝ ተረት አልሜ ሳይሆን ፤ የራሳቸውን
መንገድ በኔ የታሰረ ህይወት ተረማምደው እንዲጠርጉ ነበር።

እድሜዬን ሙሉ ካፈሰስኩት ላብ ባተረፍኩት ትንሽ ገንዘብ ልቤን እየከፋው ወደከተማ


ሳባርራቸውም ፤ ህይወት በሞቀ እቅፍ ታቆይልኛለች ብዬ ሳይሆን ልቤና ሀሳቤ ውስጥ
ታትሞ የቀረውን በመወለድ ፣ መዳር ፣ መውለድ ፣ ማሳደግና መሞት ያልተገደበ አለም
እንዲያስሱ ፈትቼ መልቀቄ ነበር።

እና ዛሬ አንድ ክፍለዘመን ሊደፍን ጥቂት የቀረው የዘመን ቁልል ተሸክሜ እየባዘንኩም ግን


አንቱ መባል ብርቄ ነው። አድጋ ያልጨረሰች ያቺ ትንሽ እኔ ፤ ያልተመለሱ ጥያቄዎቼን አዝላ
ከነወጣትነቷ አለች። ‘እማማ’ ሲሉኝ ስትሰማ ፤ ከዝምታዋ ትባንናለች።

Photo:Kirub El
እትም-14 ነሐሴ| 2012
17

ELROI ASHURO

የወር አበባዬ መጥቷል።እኔ ለምን ሰውዬ እንዳረኩት እንጃ ብዙ ሴቶች ሴታዊ


ፆታ ነው የሚሰጡት።አክስቴ መጣች፣ዘመዴ መጣች ይላሉ።አንዳንዶች ስምም
ያወጡለታል። የትነበርሽ፣ማንጠግቦሽ፣ፍፁም ወዘተ መግባቢያ code ነው።
ምሳሌ; class በር ጋ’ አስተማሪ እስኪመጣ ሰብሰብ ብለው ሲያወሩ
A; ምነው ተደበርሽ
B; ባክሽ ያቺ ማንጠግቦሽ ጋር ተጋጭተን ነው
A; ነው እንዴ? አይዞሽ በቃ እሷንማ ንቆ መተው ነው አለዚያ ፀባዯ ከባድ ነዉ
A; ቀላል በናትሽ
ልክ እንደዚህ ነው እንግዲህ፣ታዲያ ስልኩን እየነካካ ወሬውን የሚያደምጠው
ጓደኛቸው “አዪዪ ምስኪን ማንጠግቦሽ አስሬ ስቅ እያላት ይሆናል.....ሴት ልጅ
ስቅ ሲላት ውበቷ ይደበዝዛል ወይስ ይፈካል?” ብሎ ቢያስብ እንጂ ኮዱን ሊፈታ
አይችልም።

ይሄ የወር አበባዬ ቀን ቆጥሮ እኔ ጋ የሚመጣ ሳምንት “no utreus no opin-


ion” የሚል ጨፍጋጋ ፊት ገትሬ መላው ቤተሰቤ በአራስ ደምብ እንዲንከባከበኝ
አስገድዳለሁ።”ምነው ምን ሆነሻል” ሲሉኝ “መጥቷል” እላለሁ ይሄን ጊዜ አሉኝ
የምላቸው የአጥንቴ ክፋዮች ከወዲህ ወደዚያ እየተሯሯጡ እንዲያስተናግዱኝ
ብጠብቅም ጉዳዩ ‘ሚያረገኝን ሰው አጣለሁ።ያልተነካ ግልግል ያውቃል አይደል
ተረቱ?አንቺ ብቻ ሚደርስብሽ ይመስል አታካብጂ እባላለሁ።ከእናቴ በስተቀር....
እሷ በዘመኗ ዋጥ አድርጋ ባላየ እንዳላለፈችው የኔውን “ተው ልጄን ተው በህግ
ብያለሁ!!” እያለች ትሞግተዋለች።ይሄኔ የማላውቀው ድሮ ጋር በሀሳብ ሄዳለሁ።
..............ድሮ ድሮ ያኔ ስትኮረዳ ሰሞን እናቴ ጋር ለመጀመሪያ ግዜ ሲመጣ እንዴት
ሆና ይሆን?ተማሪ ቤት ቁጭ ብላ መምህር ከለልከኝ እያለች አጠገቧ ከተቀምጠው
ልጅ ጋር ቶሎ ፅፎ ለመጨረስ እየተሽቀዳደመች ሳለ ድንገት ሳይጠሩት እንደመጣ
እንግዳ ከተፍ አለባት ይሆን?ከእህት ወንድሞቿ ጋር ውሀ ቀድታ ስትመለስ አንዲት
አሮጊት ከሗላ አይታ ኖሮ “አንቺ ሸፍኚ እንጂ ኤዲያ” ብለው ምንነቱን ሳይነግሯት
ገሰፁ ይሆን?እሺ እንዴትም ትወቅ ከዛ እናቷ አስረዷት ይሆን?ቤት ውስጥ pad
ነበረን?

.....የወር አበባዬ፣ያቺ የእንጀራ እናቴ ሄዋን(በወዝህ ብላ የተባለው አዳም ሚስት


ናትና) በእባብ ተታላ ከፍሬው በመብላቷ ያመጣችብን ጦስ......እኛ ሴቶች ከወንዶች
በላይ እባብን መፍራታችን ሌላ አበባ ሽሽት ይሆን፣ድጋሚ ተታለን የአስራምስት ቀን
አበባ እንዳይፈረድብን?በስመ አብ!!

እትም-14 ነሐሴ| 2012


18

እትም-14 ነሐሴ| 2012


19

ቡድሀ፣ ኒርቫና እና የልደታ ማህበርተኞች


DAGIM ZERIHUN

በቅድሚያ ይሄ ሀሳብ ከብዙ ማሰላሰል እና ከ70 በመቶ መሰላቸት በኋላ የተገኘ መሆኑን
ማስገንዘብ እፈልጋለሁ (ማስ እና ገንዘብ … ማስ = mass፣ massገንዘቡ = ክብደት
ያለው ገንዘብ ..ምን እያልኩ ነው ዋጋ አለው!)
የዛሬን አያድርገውና በጥንቷ ህንድ የንጉስ ልጅ የዙፋን ተረካቢ የሆነው፣ ልኡል የነበረው
ሲዳርታ ጉተማ ቡድሀ (ስሙ ግን የሶስት ጓደኛሞች አክስዮን ማህበር ይመስላል ሲዳርታ፣
ጉተማ እና ቡድሀ (ሲጉቡ) ሲጉቡ የኑግ ዘይት አከፋፋይ ፕሪቪትድ ሊሚትድ)
አባቱ ከአለም ሰውሮ፣ ከስቃይ ከልሎ… ከመከራ ከድብርት እና ከርሀብ ሸፍኖ …ድሎት እና
ምላስ ሰንበር ብቻ እንዲበላ አድርጎ ያሳደገው ድልቡ ብድሀ (ይመስለኛል ካልሆነማ ታሪኩ
ሲቀጥል የተራበ ሰው አይቶ ..ወደ ውስጥ የገባ ሆዱን በንግስና ዱላው ጠቅ ጠቅ እያደረገ
እየነካካ ‹ሰውየው ካለ አንጀት ነው እንዴ የተፈጠርከው!› ባላለ ነበር) ታስቦና ተወስኖ
ድሎቱን ብቻ እንዲያይ ተደርጎ ነው ያደገው ለማለት ነው
እና በሱ መነጽር በwid እንደጦዘ ራስታ.. በደስታ ቀለማት ብቻ የምትታየው አለም አንድ
ቀን መስታወቷ እረገፈ …ስገምት 18 አመቱ አካባቢ ይሆናል እናም የአገጭ የደረት እና
የብብት ጸጉሩ የበዛለት ሰሞን.. ለንግስናው የምትሆን ቆንጆ ኮረዲት (ቄሮይት) ማየት
ሲገባው የበላው ምሰሳ እንዲፈጭለት ወክ እያደረጋ ሳለ የቤተመንግስቱን አጥር ተደግፈው
ያሉ ጠኔያም ህንዳውያንን ከነስቃያቸው ለመጀመሪያ ግዜ አያቸው(እንተኛው ታሪክ
እህል ሊሰርቅ የገባ ረሀብተና ተይዞ አይ ነው ግን ለኔ ታሪክ ስለማይመች ቀይሬዋለሁ)
እናም የፈጠጡ አትንቶችን ፣ የተጋጡ የተራቆጡ ሰውነቶችን ሲያይ ቡድሀ ክፉኛ ደነገጠ
ከመደንገጡ የተነሳ የበላው ምሳ ተፈጨ.. ደንግጦ አላበቃም እየሮጠ ወደ ክፍሉ ሄደ
(የሚያሳዝነው አጥሩ ጠባቂ ነው ቡድሀ የራበው ሰው እንዳይ የተሰጠውን ሀላፊነት
ባለመፈጸሙ ከደሞዙ ተቆርጦበታል ያውም ከአንገቱ ጋር)
ቡድሀ አለም ተገላበጠበት… ስቃይና ደስታን መመዘን ተሳነው… በኋላ ሲጣራ ድህነትን
ነው ከነአንጀቱ ያየው.. ከሱ ውጭ ያሉት ሁሉም ህንዶች ግን.. ከቆዳቸው አልፎ ድህነትን
በዲኤንኤ በዘረመል እና በዘር ፍሬያቸው ጭምር ተነቅሰውታል
ለማሳጠር ቡድሀ የአባቱ ውሸት እና ድሎት ነዶት ወደ ጫካ ሄደ (የራሱ ሳይሆን
የሰው ብሶት የወለደው ቡድሀ መሳሪያ ሳይዝ ባዶ እጁን ወደ ደደቢት ጫካ ወረደ በሉ
ከፈለጋችሁ.. ደደቢት ግንጫካ ነው)
የሆነ ሆኖ ቡድሀ ድህነትን ለመረዳት እያሰላሰለ እረጅም አመት በጫካው እድሜ
ሲራመድ ከቆየ በኋላ ደከመው ደከመውና ዝሎ ወደቀ ከወደቀበት ሲነቃ የማርያም ልደታ
ከሚከበርበት ቅቤና ቡና ከጠገበ ዋርካ ስር እራሱን አገኘው (ያቺ ዋርካ ቀጥላ በኢትዮጵያ
ታሪክ የኦነግ ባንዲራን ወለደች)
እንግዲህ ቡድሀ ያንን ሁሉ አመት ስለህይወት ትርጉም ሲያሰላስል በርሀብ ያልሞተው
የዋርካውን ቅቤና ቡና እየጠጣ ነበር ለካ .. ይሄ ሌባ! (ከሁሉም ተአምረኛ ቅዱሳን ጀርባ
አንድ የቅቤ ዋርካ እና የልደታ ጽዋ ማህበሮች አሉ የሚሉት ለካ ውሸት አይደለም) …
ወዴት እየሄድን ነው? … አዎ ወደ ኒርቫና … ቀጥሎ ወደ ማህበርተኞቹ ቆይ ደርሰናል
ቡድሀ ከእንቅልፉ ነቃ … አይኑን ገለጠ የጽዋ ማህበርተኞቹ ከዛፋችን ስር ዞር በል አይነት
እትም-14 ነሐሴ| 2012
20
አፍጥጠውበት አየ ‹ኒርቫና› ብሎ ጮኸ …ግራ ተጋብተው አዩት ያስተምራቸው ጀመር
ስለኒርቫና ኒርቫና ሁሉን የተረዳ ሁሉን ያወቀ ሁሉንም የማይሻ መሆን ነው.. መፈለግ
እና ማጣት የሌለበት ህልውና ነው … በዚህች አለም የስቃያችን ምንጭ መፈለጋችን ነው
አላቸው … እነሱ ትእግስት አተው ይመለከቱታል …ከዚህች አለም ስቃይ የምንድነው
ኒርቫናን ስንይዝ ከሁሉም ጋር እንድ ስንሆን ነው የማህበሩ አባላት ‹እኛ በአማላጇ
አንዴ ድነናል… ‹አሁን አንተም ይቺ ኒርቫና የምትላትም ሁለታችሁንም ነርቫችሁን
ሳናጠፋው ከዋርካችን ተነስ› ተጋፈጡት …እነዚህ ድሆች ከነድሪቶዋቸው ከነተጣበቀ
አንጀታቸው በደንብ አጤናቸው .. ቡድሀ ወደራሱ ተመለከተ ቡና እና ቅቤ ያጥወለወለውን
ሆዱን አሻሸ .. የሰውነቱ ቆዳ አጥንቱ ላይ ታጥቦ እንደተሰጣ አንሶላ በንፋስ ይወዛወዛል
… ‹ተነስ እንጂ› ድሆቹ ያላቸው አልራሩለትም … ድህነቱን ጠላውም፣ በቤተመንግስት
ህይወቱ የልጅነት ደስታው በአይኑ ውልብ አለበት ለካ ሁሉም ነገር ነበረው …ችጋር የያዘው
ሰው አይቶ ለምን ህይወቱን እንደጣለ! ለምን የሱ ጥፋት እንደመሰለው ተቆጨ… ከነዚህ
ድሆች ያውም ድሀ መሆናቸውን ከማያውቁ ሊሰውረው የሞከረውን አባቱ ትክክል
እንደነበር ተረዳ… ሲዳርታ ጉተማ ቡድሀ…እጁ ላይ የቀረችውን አንድ ጥሬ ቡና በትግል ወደ
አፉ አስገብቶ ሳይቆረጥም ዋጣት… ኮብል እስቶን የዋጠ መሰለው ጉሮሮው ላይ ተሰንቅራ
ቀረች… እንደምንም ድምጽ አወጣ… ‹የስቃያችን ምንጭ መፈለጋችን ነው› የሚለው
ላይ አንድ አረፍተ ነገር ጨመረ…‹የራሳችን ሳያንሰን የሌላው ስቃይ ምን አገባን› አለ እና
እስከወዲያኛው አሸለበ … ወደ ኒርቫና አለም፣ ምንም ምኞት ምንም ፍላጎት ወደ ሌለበት፣
ማግኘት ማጣት ወደ ማይጨንቁበት አለም … ወደ ሞት … ከዋርካው ስር ተደፍቶ ቀረ
… የቸኮሉት ማህበርተኞች ከዋርካው ጋር የተጣበቀ እግሩን ለስንት ታግለው ከነስሩ ነቀሉት
..ልክ ሲነቅሉት ቡድሀ አካሉ ወደ ደረቀ ዛፍነት ተቀየረ እነሱም ወድያው ወደ ፍልጥነት ወደ
ማገዶነት ቀየሩት …ቄጤማ ጎዝጉዘው ጀበናቸውን ጥለውበት ቡናቸውን ማፍላት ጀመሩ
…እየተሳሳቁ እየተመራረቁ… ቡናው ሲፈላ <ኦኦኦምምምምምም!> የሚል ድምጽ ወጣ።

እትም-14 ነሐሴ| 2012


21

ይፍቱሥራ ምትኩ

ከንግግር ሁሉ ‘ተረት’አልወድም....ከነገር ሁሉ አልወድም ‘ነበር’ ይሉትን ነገር:: ‘አህያና


ጅብ አብረው ይኖሩ ነበር’ የማይመስል ነገር:: ሲተርቱ...አጠገቤ ቁጭ ብለው ሲተርቱ
እየሰደቡኝ ይመስለኛል:: አንቺ አህያዋና እሱ ጅቡ አብራችሁ ትኖሩ ነበር...
ሲኖሩ ሲኖሩ....
ስንኖር ስንኖር....

እኔ አህያዋ...አህያነት ደግነቱ ሳር ሳሩን መጋጥ...ከርስን መሙላት...ከርሳምን መርሳት


ነው:: ረሳሁ ጅቤን... ‘ጅቤ እለዋለሁ:: ሲበላኝ ሳይሆን ሳልቅ ነው ለነገሩ እሱ ጅብ እኔ
አህያ እንደነበርኩ ያወቅሁት:: ሳልቅም ሳይሆን አልቄ ሲተርቱብኝ...

እሱ ጅቡ... ጅብነት ደግነቱ[ክፋቱ] ብድግ ብሎ ጉብ አይደለም:: ጉብ ለአንበሳ ነው::


ጉብ-እንቅ ያንበሳ ወግ ነው:: ጀግንነት ይጠይቃል:: ጅብነት ፈሪነት ነው:: ፈሪነት
ማድባት ይጠይቃል....ያላደባ ጅብ ትርፉ መተረቻ መሆን ነው...ቀንድ መንከስ:: እና
ጅቤ አደባ..አደባ ቀንዴን ሳይሆን ልቤን ሊበላ:: ልቤን አንዷን:: ያህያ ዋናው ስጋዋ
ልቧ ነው...ጮማው::

ስንኖር ስንኖር...
እኔ አህያዋ...
ምነዋ ውዴ?’ አልኩ... ምነው ጅቦ አይደለም.... ምነው ውዴ? አልኩ::
ሳሬን እግጣለሁ:: ሞልቶ የሚፈስሰው ሃብታም ነው:: ብዙ ገባር አህዮች
አሉት...’ማውቃቸውም ‘ማላውቃቸውም::
እሱ ጅቤ.... ‘እኒያን አህዮች እዪ ማደርጋቸውን’ ሲል እሰማ ነበር:: ውዴ ጅቤ
ይህንን ሲል ‘አህያዬ ሆይ...’ እያለኝ ነው ብዬ እንዴት ማሰብ እችል ነበር? ሌሎችን
ሲረግጥ...ሲጭንባቸው ‘...ለኔ ብለህ ስማ’ ሚለውን ተረት እንዴት ረሳሁ? ለካ ተረት
አልወድም...አላውቀውም ነበር ቀድሞውንም::

ስንኖር ስንኖር....
‘አህያና ጅብ ሲኖሩ ሲኖሩ....

አንድ ቀን ጅብ ለአደን ወጥቶ ብዙ ተንከራትቶ ተንከራትቶ ሚበላው ሳያገኝ


ተመለሰ... አህያ ግን ባቅራቢያዋ ካለ ሜዳ ሳሯን ግጣ ተንጋላ ተኝታ ነበር::

አንድ ቀን.... በጠዋት በተኛሁበት ተነስቶ ወጣ:: ሄዶ ቀረ...ዋለ አደረ...ዋለ...አደረ::


ልማዱ ነውና ቅምም አላለኝ::
እትም-14 ነሐሴ| 2012
22

ጅብ ለአደን ወጣ....በለስ ቀንቶት ግዳይ አገኘ:: አህያ ጭና መንገድ ጀመሩ


ወደጎሬያቸው.....

ጎሬያችን... የሱ ቤተመንግሥት የኔ እልፍኝ... የሱን ግዳይ ተሸክሜ ቱስ ቱስ ከፊት


ከኇላው... ቱስ ቱስ ቱስ

ሌላ ቀን...
ጅብ ለአደን ወጣ... እንደወትሮው ወዲያ ወዲህ ቢልም አልቀናውም ያን’ለት::

ጅቤ በጧት ወጣ... እንደልማዱ... ዋለ... አደረ... ዋለ... ቅምም አላለኝ እንደልማዴ::

ጅብ ጅብ ሆኖ መጣ ተርቦ::

አህያና ጅብ ሲኖሩ ሲኖሩ...


ስንኖር ስንኖር...

‘እኔ ጋራ ሜዳውን ኳትናለሁ... አንቺ እዚህ ትደልቢያለሽ’ አለ አሉ ጅብ...


‘ምነዋ አያ ጅቦ.. አለች አሉ አህይት...
‘ምነዋ አያ ጅቦ... የድርሻዬን የተፈጥሮዬን’ንጂ ያንተን ድርሻ መቼ ነክቼ....’ ሳተች
አህያ...
ሳትኩ እኔ ‘ላይ ታችህን አብሬ አላዘገምኩና እንዲህ አልክ?’ አልኩ... ሳትኩ

አህያነት ሞኝነት... ሊበላኝ ሲያመቻቸኝ ውሻ አሰረ ከጎኔ...የሚያባላው...


ጅብነት ደግነቱ[ክፋቱ]... ‘ጠባቂ ያሻሻል’ ነው ማሞኛው... መልዓክነት ሲሾሙት
ሰይጣንነት መመኘት...

‘የግሌን ላይ ታች’ ጥርሱን አግጥጦ...


‘የጋራችንን’ ተንጠራርቼ....

ጅብ ብልህነቱ ማድባቱ... አድብቶ አድብቶ


ከውሻው ተማምሎ ተስማምቶ
‘ልብሽ ልቤ ያለውን ዘንግቶ
ሸነታትሮ በላልቶ
ቆዳዬን..አጥንቴን
ጉበት...ኩላሊቴን
አንክቶ አንክቶ
እትም-14 ነሐሴ| 2012
23

አንክቶ
አንክቶ
ጋብ ሲልለት ራ’ቡ
‘አደራ’ አለ ለአያ ውሾ..
አደራ የልቧን ነገር....

ውሻ ይስቅ ይመስለኛል
ከጉበት ኩላሊት ፊት ልብ ልቤን አጣጥሟል...
ቀረጣጥፎ አጣጥሞ ጠግቧል
ያስባል ኇላ የሚገጥመውን
የሚጠየቀውን
‘ምነው አያ ውሻ ልቧስ?’
ይመልሳል...
ልብ ቢኖራት ቀድሞውን ካንተ ትወዳጅ ኖሯል?
ያብራራል
ያብራራል...

አለቅሳለሁ እኔ...
ወይ ልቤን ልቤን ኩላሊቴን....

እትም-14 ነሐሴ| 2012


24

...HE WALKS AWAY


THE SUN GOES DOWN...
ጭምቱ እብድ
Amy Winehouseን በጡዘት እየሰማሁኝ አለቃዬ ነው መሰለኝ ስልክ ተደወለ። I don’t
know if I am too tired or too lazy, I don’t know ብቻ I couldn’t move my
hands. My phone vibrated and vibrated until it got into the bathtub, it
feels like I watched it in slowmo. Popping off the remaining bubbles
one by one. With every pop you can feel time is ticking till your demise.
Maybe I am overthinking it. But I feel like there should be someone by
your side when we are taking the wrong steps or we gonna plummet
like my phone.

‘ወንበር ላይ እንቅልፍ ሊይዛቹ ብሎ ልትወድቁ ስትሉ የምትባንኑት ነገር’ እንደዛ


እያረገኝ ነው። ሸለብ ነቃ ሸለብ ነቃ ፤ መጨረሻ ላይ ስነቃ ግን there was a dude
in the bathroom. How the fuck does one go in without me listening to
it? I am just glad I don’t have a jacuzzi, imagine him joining me there.
I called out my families name to come and help me, noone answered.
The dude kept smiling. I have seen enough movies not to be at ease
with his smile. Who the fuck smiles while someone is in a tub? Rapists
and lovers. I am not saying rapists can’t be lovers, I mean they make
them scream. I kept screaming names and he without being phased
calmly sat at the bottom end of the tub.

Stop screaming! You little cunት you don’t even remember who I am,
do you? You are so far up your ass that you don’t even remember me!
How long has it been? Try, it has been too long since you used your
brain, but try.

I don’t know.

አንገትህን ከሚከብድህ ጭንቅላትህን ላትጠቀመው ነገር ለምን አትወረውረውም?


You are wasting your life. Remember how you were gonna kill yourself?
It didn’t happen, did it? You just talk big game. Who made you quit
campus? I did, but did you use your opportunity? Nope, you just wast-
ed 5 years of your life. Remember all the youtube tutorial videos stored
in your harddisk? You haven’t watched 1 video, have you? You fucking
useless cunt, you were a prodigy. What is your accomplishment in these
እትም-14 ነሐሴ| 2012
25
5 years? Nothing, absolutely nothing. Imagine your family feeding you
decades and have nothing to show for it. You are too skinny to even be
shown by your family as የተቀለበው ልጃችን። If they invested the money
spent on you on a dog it still would have been a better tradeoff. At least
they would have felt love. If they had a donkey he would have helped
your mother carry her groceries. What did you do? You almost made
your mother bleed to death having you. Tonight’s the night cunት. To-
day is your last day. You have been ሸክም for too long. Of all the good
things that happened in your life, it was I who was responsible. You
just took credit for what I did. You are a parasite cunት and I don’t see
anything changing in your life. Lemme ask you this, do you honestly
believe you deserve to live?

Yes, I can change. Give me a month or two I will be good at something


from one of the tutorials. Trust me I just need 1 or 2 months.

Hahahaha.... you don’t even know what you are going to do. You don’t
even know me. I can’t let you live cunት። This is your last day. You
screamed already shut the fuck up. Life is a game cunት and you have
wasted your lifeline. Noone can hear you dear God. What day is it? Ding
ding ding its Saturday and noone is at home. I chose this day. You still
haven’t figured it out have you, I am you. I am Jigsaw. Shake that dumb
face of yours all day, it ain’t gonna change shit. I finally am here to end
this nonsense. I let you see what I want you to see. I am a salesman re-
member የበአል ታላቅ ቅናሽ ተብሎ ስለተለጠፈ ብቻ ዘው አትበል። Look at your
hands you must like the blood. You were too much of a chicken to do
it. I am here no worries. You see the trick to cutting your wrist is to have
a sharp knife. Even if you have second thoughts it would be too late.
This is your last day cunት, that’s why I chose Amy Winehouse for you.
“Das Ende” cunት። You should have gone when you had the chance like
Heidi Turner.

እትም-14 ነሐሴ| 2012


26

ዘ ሚስካልኩሌሽንስ
AD MINO
አ᎐
“አሮጌዎቹ ዘፈኖችና የሽማግሌዎቹ ተምኔቶች” ሁሌም የሚያጨናንቋት ነገሮች
ናቸው። “ያለፈው” ብላ በነሲብ የምትፈርጀው ጊዜ እና ከሱ እንደምንም ተርፈው
“አሁኗ”ን የሚጋሯት ሰዎች አይመቿትም። ይኸንንም በግልፅ ቋንቋ ለጓደኞቿ
ትናገራለች።
ያየኋት ጊዜ ታክሲ ውስጥ ነበረች። ሰንበት ማለዳ ስለነበር ከባለንጀራዎቿ ጋር ወደ
አምልኮ ቦታ እየሄደች ነበር። ባለንጀራዎቿ ያልኳቸው፣ ዕድሜዎቻቸው አስራዎቹን
ወደ መጨረስ የሚያደሉ አንድ ወንድና ሁለት ሴት ታዳጊዎች ናቸው። በግራ
እጆቻቸው ጥቁር ሽፋን ያላቸውን ሐዲስ ኪዳኖች ይዘው፣ ስለ ሴት ፓስተሮችና ስለ
አክሮባቲስት ጓደኛቸው እያወሩ ነበር።
ወንዱ ጓደኛቸው ብዙ ባያወራም ማሰሪያውን አረፍተነገር ጣል እያደረገ፣ ብዙውን
ጊዜ እየተዋጠ ያወካሉ። የልጁ ነገር ለምን ትኩረቴን በጣም እንደሳበው ባይገባኝም፣
በተለይ ስለ ሴት ፓስተሮች ያወሩትን መርሳት አልቻልኩም።
“ሴቶቹ ፓስተሮች ነብይ ነው ሚባሉት!”
“ሴት ፓስተሮች ያስጠሉኛል። በተለይ ያረጁት!” አለችው። ወሬው የሰለቻት መሰለኝ።
ታክሲው ውስጥ ያለው ሙዚቃ የእጅጋየሁ ሽባባው ዘፈን ነው። ካህኔ ነፍሴ አገልጋዬ
᎐ ᎐ ᎐ ትላለች።
-
ቡ᎐
ከምንማርበት ግዙፍ ሆስፒታል ማዶ ያለው የከተማው ክፍል ገጠር ቀመስ እና
ዘፈቀደ አሰፋፈር ያለበት የተራራ ደረት ነው። እዚህ ፎቁ ላይ ሆኖ አረንጓዴውን ጋራና
የገበሬዎቹን ቤቶች ማየት ቀላል ነው። ከተማው ከዚህ ከሐኪም ቤቱ ፊት ለፊት
ካለው አስፋልት ጀምሮ እየሳሳ እየሳሳ ይሄድና የዳገቱ ሥር ሲደርስ ጥቂት የጨረቃ
ቤቶች ብቻ ያሉበት የእርሻ ስፍራ ይሆናል። ቤቶች፣ ቤቶች፣ የኮካኮላ ሎጎ የተሳለበት
የቆርቆሮ አጥር፣ ቤቶች፣ የዛገ ቆርቆሮ፣ የዛገ ቆርቆሮ፣ አዲስ ቆርቆሮ ᎐ ᎐ ᎐ በቆርቆሮ
የተሰራ ማስጂድ። የቆርቆሮ ሚናራ ያለው። ሌላ የጭቃ ቤት፣ ሌላ የጭቃ ቤት ᎐ ᎐ ᎐
ሌላ የቆርቆሮ ማስጂድ። የቆርቆሮ ሚናራ ᎐ ᎐ ᎐
-
ጊ᎐
ሲ᎐ እና እኔ ብዙ ጊዜ ተከራክረንባቸው ካልተስማማንባቸው ነገሮች አንዱ፣
“ሐይማኖት የዚህች ሐገር ብቸኛው የሞራሊቲ ጠባቂ ተቋም ነው እና አይደለም።”
ነበር። እሱ እንደሚለው፣ የሶስተኛው ዓለም ሐገራት እንዳይበለፅጉ ማነቆ ሆኖ
ያሰራቸው ዋነኛው ነገር የሐይማኖት ገናንነት እና አድሐሪ አዝማሚያ ነው። በርግጥ
ሲ᎐ ማለት የለየለት ኢአማኒ ነው። እግዜርን የካደ ብዬ ብገልፀው በውስጠታዋቂነት፣
እትም-14 ነሐሴ| 2012
27
“እግዜር አለ፣ ሲ᎐ ግን መኖሩን አያምንም።” ማለት ይሆንብኛል። ብቻ ግን ኢአማኒ
ነው።
-
ዳ᎐
አንዳንድ ቀን ከሆስፒታሉ ሶስተኛ ፎቅ ሆኜ ኃይለኛ የተሲያት ንዳድ የሚወርድበትን
የጋራውን ደረት እያየሁ እመሰጣለሁ። ሐኪም ቤት ከማንኛውም ምድር ላይ ካለ ቦታ
በላይ ሰቆቃ የሞላበት ሥፍራ ነው። የሆስፒታል ግድግዳዎች ከየትኛውም ቤተእምነት
በላይ ተስፋ የቆረጡ ፀሎቶችን ሰምተዋል የሚል ጥቅስ ሳላነብ አልቀረሁም። እነዚያ
ማዶ ላይ ጋራውን የሚቆፍሩ መሐይማን ገበሬዎች በየቀኑ ሶስቴ እና አራቴ እዚያ
የቆርቆሮ መስጂድ ውስጥ የፈጠራቸውን ያመሰግናሉ። ምክንያታቸው ደህንነታቸው
ወይም ሶስተኛ ልጃቸው ማግባቱ እና ወግ ደርሷቸው አያቶች መሆናቸው ይሆናል።
በዚያው ቅፅበት ጃፓን ውስጥ ሰዎች ህዋሳት ውስጥ ያሉ ሞለኪዩሎችን በዓይን
ማየት የሚያስችል ማሽን እየመረቁ ነው። ወዲህ ነጩ ግዙፍ ቤት ውስጥ የሆነ ሰው
በፅኑ ደዌ ይማቅቃል። የሆነ ነገር ትክክል ባይሆንም፣ ህማሙን ፈፅሞ ማስቀረት ግን
አንችልም።
-
ሄ᎐
ይቺ ልጅ ሽማግሌዎችንና አሮጊቶችን ብትጠላም እናቷንና አባቷን ግን ትወዳለች።
ቢያንስ እንደዛ ትላቸዋለች። “እማ ስወድሽ እኮ!”
የቤተሰቧ የበኩር ልጅ ናት። ብዙ የምታክመው ነገር ቤቷ እና ሰፈሯ እና አይኗካዋ
እና ከተማዋ ዙሪያ አለ። ዘወትር እንዳረፈደች ይሰማታል። ዘወትር ከጓደኞቿ እና
ከእኩዮቿ ኋላ ናት። (እስከዛሬ አልተሳመችም ሁላ እኮ!) እና የጊዜ ባዝራ ቀድሟት
እየሸመጠጠ እንደሆነ ታስባለች። ጊዜ ለአንዲት ልጃገረድ ምንድነው? ᎐ ᎐ ᎐ ባዝራስ? .
. . አሮጌው የመንዝ እና የደምበጫ ወይ የደምቢያ ሰዎች ቋንቋ?
-
ዉ᎐
ምናልባት የተራራው ልብ ውስጥ ዩራኒየም አለ። አለን ብዬ እንዳላወራ
የሚያደርገኝ “መጤነት” በዚህ አገር አድራጊፈጣሪዎች ግምባሬ ላይ ተለጥፎብኛል።
ልፋለመው አልፈልግም። ግን ገበሬዎቹ ምን እንደሚያርሱ እንኳን አያውቁም።
መሐይምነታቸውን ግን ብልጦች ይጠቀሙበታል። ብልጦቹ ፖሊቲከኞችና
ሐይማኖተኞች ናቸው። ቅድም ስለደሕንነታቸው ሲሰግዱ ቆይተው መስክ ላይ
ስለሚፀዳዱ በኮሌራ ይወድቃሉ። ፖለቲከኞቹ በሽታው ከሌላው ዓለም ስለጠፋና
ሰው ቢሰማው ስለሚስቅባቸው አዲስ ሥም ይሰጡታል። ሐይማኖተኞቹ ደሞ
የሚንቀጠቀጡ ጣቶቻቸውን ፀጉሯን ያልሸፈነችው የሰፈር ኮረዳ ላይ ይቀስራሉ።
ከቆሻሻ ጥፍሮቻቸው መንታ መንታ ፍላፃዎች ይወነጨፋሉ። ከሶስት ኪሎሜትር
ርቀት ዓይኖቹን አጥብቦ አወዳደቃቸውን የሚያየው ታዛቢ ጓደኛዬ ግን በነገሩ
ከንቱነት ደካማ ምፀቱን ይፈግጋል።
ይላልም፡
“ሁላችንም ወደ ሞት እያዘገምን ነው። ይኸ ይኸ ድንቁርና ግን ፍፃሜያችንን
እትም-14 ነሐሴ| 2012
28
ያፋጥነዋል።”
-
ዞ᎐
ስለሷ ሁለት ነገሮች አሉ። አንደኛው ደማም ቆንጆ መሆኗ ነው። ሁለተኛው ነገር ደሞ
የነገሮችን ድብቅ ጎን ማየት የማትፈልግ መሆኗ። ይህንን ቆንጆ ጫማዋን ትወዳለች።
ሲፀዳ የተረፈውን እጣቢ ግን ትሸሻለች። የማይደከምበት፣ የማይሰለችበት፣ እንዳባቷ
የማያንጎላጁበት፣ እንደናቷ የማያንኮራፉበት ዓለም ትሻለች።
ቸርች የደረሱ ጊዜ ወንዱ ልጅ ቀድሟቸው ከታክሲው ለመውረድ ሲያጎነብስ ሱሪው
ዝቅ ስላለ ለአፍታ የመቀመጫውን ስንጥቅ አየች። እና መንግስቷ ፈራረሰ። በሷ
እድሜ እና ጥንካሬ ያለ ሰው ላይ እንደዚያ ያለ እንከን ማየቷ የእስከዛሬው እምነቷ
አሸዋ ላይ የተገነባ ቤት እንደነበረ አረዳት። እንደተከዳች አሰበች።
(ለሷ እንከን ነው የቂጥ ስንጥቅ፣ የገላ ክሽፈት። የሰውልጅ አካል እንደ መላዕክት
ከሥጋዊ ጉድፎችና ፍላጎቶች ነፃ እንደሚሆን፣ በምን እንደሚሆን ባይገባትም፣ ነፃ
እንደሚሆን ታምን ነበር።)

ሁልጊዜም ሞትን የምትፈራ አድርጌ አሰብኳት። ግን አሁን ሳስበው ሳልሳሳት
አልቀረሁም። ሰው ሞትን የሚፈራው ስለ መረሳት አብዝቶ ከተጨነቀ ነው። የሷ
ጭንቀት ስለፍፅምና ነበር። ሞት ከፍተኛው የፍፅምና ክህደት ነው። እሷ እዚያ ረቂቅ
የሃሳብ ደረጃ ላይ ከመውጣቷ በፊት ቀለል ያለው የአካል ድክመት አሸነፋት። ያም
ሆኖ ከሲ᎐ ኢአማኒነት እና ከገበሬዎቹ አሳዛኝ ተረክ በተቃራኒው የምትቆም ናት።

እትም-14 ነሐሴ| 2012


29

THE TODAY JOURNAL


KALKIDAN TESFAYE

As we ride to the turmoil with pieces of cloth,


tapped to our words Rinsing relations off our palms,
We wait for the slant of light at the edge of the iceberg Together,
yet apart Praying to be saved once again Godless,
yet i fear of stepping
on the wrong stone We stand on today Till tomorrow’s gone.

(AUGUST, 2020)

እትም-14 ነሐሴ| 2012


30

የእንባ ዘመኔ አልፏል...


ሳሙኤል: ደረጄ
እሷስ ሎሚ ናት ያባይ ዳር ፥
ሎሚ ናት ያባይ ዳር ፥
የማትጠገብ ጣፋጭ ማር ፥
ሎሚ ናት ያባይ ዳር ......

ማግባቷ አልገረመኝም። .... በአዳም ሄዋን ህግ የሚጣነዱ ሁለቶች ሁሉ ምናልባት


በቅብዝብዝ የልጅ ልብ ወይ የተስፋ ማጣት ህመም ከዘራው ሽሽት በቀር
የማይናፍቁት ጥቂት ይመስሉኛል - ትዳርን።

ሲፍጥረን ሁሉን ማግኘት ባንችል መመኝት ሞልቶ የተሰፈረልን መክሊታችን ነው።


ዘወትር በስኬት ስናጎለዉ በየቀኑ የሚሞላ የመሻት ቋት የሆነ ልብ ተሰጥቶናል -
የብዙ እንስቶች ቋት እኩሌታዉ የትዳር መሻት የሞላበት ነዉ። ለዚህ ይመስለኛል...
የሰርግ ዜማ በሌላ የዜማ ህግ ሳይሆን በዉስጡ በጸነሰዉ የመጣመር ረቂቅ የሚረታ
አቅም ያለዉ።... የእልፍ እንስቶች ልብ ይህን መሻት ያረገዘዉ ከተፈጥሮ ዶግማ
በላይ ሚስጥር ያለዉ የረጉ ልቦች መድረሻ ስለሆነ ይሆናል - መጣመር።

... ደግሞም የኔ አይነት ቅብዝብዝ ልብ የማይፈታው አንድምታ እልፍ ነው...እልፍ


ይመስለኛል...

****

የኛ ሙሽራ ዘመናይ
አበራች እንደጸሃይ....

...ያየኋት ቀን ረጅም ሰአት ትስቅ ነበር። ግሩም ሳቅ አላት። ልጠጣ ያነሳሁትን


የማኪያቶ ሲኒ ከንፈሮቼን እስኪናፍቅ ድርስ ባየር የሚያስረሳ - ግሩም ሳቅ።

ቀለም አመሳስለዉ ሱሪ እና ጫማ ስለሚያረጉ ወንዶች እና እንዴት ጥቁር የልብስ


ማች(match) ማየት ዱዳ ሲናገር ከማየት በላይ እንደሚያስደስታት ብዙ ያወራችልኝ
ጓደኛ አላት ። የተዋወቅን ሰሞን (ከጓደኛዋ ጋር) መጽሃፍ ይዤ አይታኝ ይሆን
ረዣዥም የወንደላጤ እሁዶች እንደማይገፉ አዉቃ በየሁለት ሳምንት እሁድ ቡክ
ክለብ አይነት አንዳላቸዉ ነገረችኝ ...እንድመጣ። ቃል በቃል “ሙት...ብትመጣ
ይመችሃል ስለመጽሃፍ ምናምን እናወራለን” አለች።
እትም-14 ነሐሴ| 2012
31
..ለ9 ሰአት ቀጠሮ 10 ሰአት የሚሰባሰቡ አራት ኮተቶች እና እሷ መጡ - እሁድ።
ለአንድ ሰአት ያህል ልጅ ሆኜ ቤት የነበረንን ቃላስ* የመሰለ ቀለም ያለዉ የካፌ
ጠረቤዛ ላይ አፍጥጬ ሁለት ቡና እንደጨረስኩ።

ብዙ ‘ሚያወሩ አራት ኮተት ጓደኞችቿ (አንድ ወንድ አብሯቸዉ አለ) ፥ እኔ እና


እሷ ሆነን የወረኢሉን ገበያ በሚያስነቅ ግርግራም ካፌ የዉስጥ በረንዳ ላይ
በክብ ተቀምጠን ከፊል የተጋረደ ፊቷን አየሁ.... ከጀርባዋ ዉልብ የሚሉ የካፌ
ተርመስማሾችን አደብዝዛ ሁሉን ቀልቤን ሰረቀች።

ያኔ ሳይት .... ፊቷ የረጋ ነበልባል ስሜት ነበረዉ። በአዲሳባ ስብስቦች ዉስጥ


ያለመድኩት አይነት ... የፍም ፍንጣሪ አላት።... አልፎ አልፎ በረዥሙ ስትስቅ -
በሚጨፈኑ አይኖቿ እና በሚሰረጉድ ጉንጯ....ከነጭ ኮቷ ስር ሮዝ ስስ ቲሸርቷን
በወጠሩ ጡቶቿ.....በቀጫጭን ጠይም ጣቶቿ....ፍሪዝ በሆነ ክምር ጸጉሯ.... ጥላ
ያጠላበት የጥቁር ሃይቅ ቅንጣት ያለዉ በሚመስሉ አይኖቿ....እና በሁሉ አካልቷ
ዉስጥ ያለ...እንግዳ አይነት ነዉ። ደንዝዤ ዋልኩ።

... እሁድ መሽቶ ቤቴ ስገባ ሁለት ሰአት ሙሉ ያወሩት አብዛኛዉ ትዝ አይለኝም።


አብረዉን የነበሩትን እና በጀርባዋ የሚርመሰመስ የካፌ ጋጋታ እና ጫጫታ...
እስክረሳ ድረስ ይዛኝ ነበር።

****

አምሯል ሸገኑ አምሯል ሸገኑ...አምሯል ሸገኑ


መደሰቻችን ዛሬ ነዉ ቀኑ...ዛሬ ነዉ ቀን

...ያቀፍኳት ቀን የጊዜ ጠለል ለዘለላም እንዲቆም ፀለይኩ። ዘወትር አብረን እንዳለን


ምጽአት እንዲደርስ...ጸጉሮቿን እየደባበስኩ...ከጠረኗ እንደተጣባሁ....ጡቶቿን
እንደተደገፍኩ......

ቀና ብላ ጀርባዉ ላይ ብልጭልጭ ኮኮብ ያለበት ፒንክ ቲሸርት አርጋ አልጋዉ


ላይ ቁጭ አለች። ሲነኩ ቲማቲም ይመስል የሚቀሉ ታፋዎቿን አጋልጣ።....ገና
አልጠገብኳትም...

እንደልፍያ በእጄ ጎትቼ በጀርባዋ አስተኛኋት። እጆቿን በእጄ ይዤ ቁልቁል አየኋት...


የቀሉ ጉንጮቿን....የሚያሳሱ አይኖቿን...ታፈዛልለች።

....ልስማት ዝቅ ስል አይኖቿን ጨፍና ሳቀች። ያ ሳቋን።

****
እትም-14 ነሐሴ| 2012
32

እሷስ ሎሚ ናት ያባይ ዳር
ሎሚ ናት ያባይ ዳር
እኔስ መሸብኝ የት ልደር
ሎሚ ናት ያባይ ዳር....

የሄደች ቀን በዝናባም የሃምሌ ሰማይ ስር በካፊያ እየራስኩ ወደኋላ የኖርናቸዉን


ቀኖች ሁሉ መዘንኩ ምንአልባት ያጎደልኳቸዉ ቅጽበቶች ካሉ ብዬ።

ማግባቷ አልገረመኝም....አብራኝ ኖራም መለየቷን እፈራ ነበር።

... ስትሄድ ግን ልቤ እንደጠወለገ ሃረግ ሆነ። ቁልቁል ወርዶ ከመረገጥ ዉጪ ወደላይ


ሊዘም አቅም እንዳጣ የወይን ሃረግ...ብዙ አነባሁ።

ግን በቃኝ....አሁን የእንባ ዘመኔ አልፏል....

አሻ ገዳዎ
በል አሻ ገዳዎ በል አሻ ገዳዎ
አሻ ገዳዎ
ዛሬ ምንድራት
ልጅት የኛ ናት......

________________
* ኒኬል

እትም-14 ነሐሴ| 2012


33
#ColorizingHistory

Time Travelers

Source: https://www.facebook.com/colorizinghistory
እትም-14 ነሐሴ| 2012
34

YIKUNOAMLAK M. GEBREHIWOT

I look to dawn,
... darkness begone.
I’m hopeful for brightness,
... instead I’m met with vagueness.

Will we see better days?


... where we bask constantly in the sun rays.
Or will the days be dark?
... and all our fortunes stark.
I’m more scared of the bland ...
... uncertain days spanned.
Unsure of tomorrow’s fate ...
... not knowing what’s on the other side of the gate.

But one thing is for certain ...


... the beginning or the end don’t draw the curtain.
The best part of the play is the journey ...
... that’s where you expand to the edges of your boundary.

እትም-14 ነሐሴ| 2012


35

SHE’S A REAL WOMAN


IYE TESFAYE
She’s a real woman whose story can’t be told by looking at her face
holding a smile that never reaches her eyes or by her strong brave
look she tends to put on, she’s a real woman who’s always trying to
outdo herself battling millions of wars with her own demons she’s a
real woman with real struggles she wins gracefully she loses quietly
her mind her biggest treat, she’s a real woman not only who feels pain
but brave enough to decorate those pains and carry with grace, she’s
a strong woman with a brave face and weak heart you saw her bravery
but missed her sad eyes you heard her strong words but you missed
her soft mouth you saw her pretty face but you never cared for her
back.

እትም-14 ነሐሴ| 2012


36
BETHLHEM ያስጠላኛል ....
መንገድ ላይ ተዘርፌ ስጮህ አላፊ አግዳሚው ከንፈር
NIKODIMOS መጥጦ ሲያልፈኝ...
የራሱ ሽንት ቤት ያለው ሁለት ክፍል ቤት ለመከራየት አስር
ሺህ ብር ስባል ...
ጫን ያለ ህመም ብታመም መታከሚያ እንደሌለኝ ባሰብኩ
ሰአት...
ያስጠላኛል !
ይቀፈኛል!!
ይነደኛል!!!!
አሁን ባለንበት ቀውስ የሆነ ቀን መንደሩ ቢበጠበጥ በአንድ
አለሌ የመደፈሬ አጋጣሚ ሰፊ እንደሆነ ሳስብ...
ለፖለቲካ ፍጆታ ሰው በወጣበት እንደሚቀር ሳይ...
እርጉዝ የምትገደልበት ወላድ የምትታረድበት ጊዜ ላይ
መድረሳችን...
አባቶች በጠራራ ፀሀይ እየተጨፈጨፉ ሳነባ....
ያስጠላኛል !!!!
ይቀፈኛል!!!!
ይነደኛል!!!!
ግን ... ግን
ድክ ድክ የሚል ህፃን ፈጣሪን ሲያመሰግን ሳይ...
የፈረሰ ቤት መሀል ከስደተኞች ውስጥ ማትሪክን ሁሉንም
A አምጥቶ ያለፈውን ልጅ ሳይ...
ሙሉ ንብረቱ ወድሞበት “ልብ ይስጣቸው “ የሚለውን
የአገሬን ባለሀብት ሳይ...
ለተቸገሩት የወር ቀለብ የሚሰፍሩትን ወጣቶች ሳይ...
ከወፍጮ ቤት የበርበሬ ሽታ ሲያስነጥሰኝ ይማርሽ እኔ
አመጣለሁ የሚለኝን ምስኪን የሰፈሬ ተሸካሚ ሳስብ...
ቋንቋ ላይ ብዙም ባንግባባም እንደወደደኝ በምልክትም
በጥቅሻም የነገረኝን የዋህ የክፍለሀገር ልጅ ሳስታውስ...
ደስስስ ይለኛል !!
እፈነጥዛለሁ!!!
ተስፋ አለን!!!
ሁሉም መጥፎ አይደለም!!!
አገሬ ትቀጥላለች !!!

እትም-14 ነሐሴ| 2012


37

ሮዛ
WILILY BALD
ብግን ቅጥል እያልኩ ዛፉ ስር ሄጄ ተቀመጥኩ። አስጠሉኝ! እዩት ደሞ ናቲን
ይሄ ብሽቅ! እላለው በሆዴ። “ስሙ ምንድነው የሚባለው?” አለች ሮዛ ከጎኔ
እየተቀመጠች። “ሀርሞኒካ ነው የሚባለው። ስሙን እራሱ አያውቁትም እኮ!
ሲያስጠሉ!” አልኩ በንቀት እያየኋቸው። ሮዛ ዝም አለች። ዛሬ ገና ነው ያወራነው።
እሷም ሆነ እናቷ ከሰው አይገጥሙም ለጨዋታ እንኳን ከስንት አንዴ ነው
የምትወጣው። ስትወጣም እዚህ ዛፍ ስር ቁጭ ብላ ሌሎቹ ሲጫወቱ ማየት ነው
ስራዋ። እየተጫወተ ያለ ልጅ ቤት ሲጠራ ወይም ለጨዋታ ሰው ሲያንስ ነው
የምትጠራው ያውም ሰብለ የቄሱ ልጅ እና ፍቅርተ ድፎ እሺ ካሉ። እናቷ ሴተኛ አዳሪ
ናት። አባቷ ከሞተ ቆየ ይላሉ። እናቴ ስትነግረኝ እሱ የሞተ ቀን እናቴ እኔን ወልዳ
ከሆስፒታል ቤት መግባቷ ነበር። ቀበር ካልሄድኩ ብላ አስቸግራ ቤት እንደተቆለፈባት
ነግራኛለች። የሮዛ እናት ቲቲ ነው የምትባለው ድሮ የእናቴ፣ የእትዬ አበዛሽ፣ እትዬ
ፅጌ፣ እና እትዬ ምስራቅ ጓደኛ ነበረች. . .አሁን ከእናቴ በቀር ማንም አያዋራትም። እኛ
ቤት ስለ ሮዛም ሆነ ስለ ቲቲ ምንም አንባልም። እነ ናቲ፣ሰብለ፣ፍቅርተ እና ሰላም ግን
ስድብ ሁሉ ተነግሯቸው ነው የሚመጡት። ሮዛ ከቤት ወጥታ ዛፉ ስር ቁጭ ስትል
የሚዘፍኑት የስድብ ዘፈን ሁላ አላቸው።

ሮዛ ታላቄ ናት ፫ አመት ገደማ ትበልጠኛለች። አዋርቻት አላውቅም። ብዙም የሰፈር


ልጅ አላዋራም። ኳስ ካልሆነ ምንም አብሬአቸው አልጫወትም። ሌላ ነገር ሲጫወቱ
የወርቁ ዘበኛው ቤት ጋር ቁጭ ብዬ አያቸዋለው። ‘ባሪያው ልክፍት አለበት ለዛ
ነው የማይጫወተው’ እያሉ ያሙኛል ሲያሻቸው ትምህርት ቤት በእረፍት ሰዓት
ክፍል ድረስ መጥተው ‘ልክፍት’ ብለው ሰድበውኝ ይሮጣሉ። ስይዛቸው ግን. .
.በቃ ሰፈር ውስጥ ያልደበደብኩት ሰላም እና ሮዛን ብቻ ነው። ሌሎቹን እንዳለ
አቅምሻቸዋለው። ጨዋታ አልወድም ማየትም አልወድም። ሲጫወቱ ሲገለፍጡ
ሰላምን ሲጎነትሉ ሳይ ያሳርረኛል።

ሰላም እኮ ቆንጆ ናት! እሷን ለማየት ነው ሜዳ የምመጣው። እሷም አባት የላትም።


እናቷ ግን የሚከራዩ ቤቶች አሏት ስለዚህ ምንም አትሰራም። ስራዋ ሰላምን ማስዋብ
ብቻ ነው። ሀብታም ነገር ናቸው ሰራተኛ አላቸው፣ ፍሪጅ አላቸው፣ ዴክ አላቸው።
ክረምት ክረምት አስጠናታለው ከዛ ፊልም እናያለን ግን ሁሌ አንድ አይነት ፊልም
ነው Titanic ሲሰለቸኝ ቤት እፈለጋለው ብዬ በጊዜ ወጥቼ አሴ ቪዲዮ ቤት ሽልንግ
ከፍዬ የአሜሪካ ፊልም አያለው። የሰፈራችን ጉልቤዎች ዳንኤል ቁራው እና ሶል ኮብራ
ካሉ ግን እነሱ ይከፍሉልኝ እና መሀላቸው ቁጭ ብዬ እተረጉምላቸዋለው። የህንድ
ፊልም አልወድም። ገና ሲጀምር ነው ሮጬ የምወጣው። ሮዛ ልጫወት ብላ ለምና
አያስገቧትም በዛ ላይ ይሰድቧታል። እኔን ተጫወት ብለው ለምነውኝ እምቢ ስላቸው
እትም-14 ነሐሴ| 2012
38
ይሰድቡኛል፤ ከዛ እመታቸዋለው። ያለቅሳሉ።እዛ ማዶ ሮዛም ታለቅሳለች። የሁሉም
እናቶች መተው ረግመውኝ ይሄዳሉ። የሮዛ እናት ግን በሯን ገርበብ አርጋ እያየች
ትስቃለች። ከዛ ልጇን የሆነ ነገር ገዝታ ለምና ቤት ታስገባታለች። የብዙ ቀን ትዕይንት
እንዲህ ያለ ነበር። ዛሬ ግን ልጫወት ብዬ ለምኜ እምቢ አሉኝ። ነገሩ ጨዋታ
አይደለም ጭፈራ ነው። ሰላም ሀርሞኒካ ተገዝቶላታል እና ወንዶቹ በየተራ ሀርሞኒካ
እየነፉ(አይችሉበትም እኮ) ከሰላም ጋር ይጨፍራሉ። አጫውቱኝ አልኩ እምቢ አሉ
ሶስት ሶስት ዙር ተራ ይዘናል አሉ። እቃጠሉኝ!! በቅርብ ሆኜ አይኔ ስር ከሚጨፍሩ
ትንሿን ሜዳ አቋርጬ ይኸው የዛፍ ጥላ ስር ከሮዛ ጎን ቁጭ ብያለው። “ዛሬ ለምን
አትመታቸውም?” “ዝሬ አባቴ ይመጣል” አልኳት አይኔን ሰላም ላይ ተክዬ። ከገዛ
ወንድሜ ጋር እየጨፈሩ ነው። ንዴት ሊደፋኝ ነው። እናቴ ታላቅ አይመታም ብላኝ
ነው እንጂ አፍንጫውን ነበር ምሰብርለት!! “ታድለህ! እና አባትህ ቢመጣ ምን
ችግር አለው?” “ይመታኛል። ባለፈው ከመጣ ጅምሮ እስካሁን ብዙ ጥፋት አለብኝ
ገና ብዙ እገረፋለው እነዚን ከመታው ደግሞ የሁሏም እናት ቤት እየመጣች ነው
የምትነግረው። ይገለኛል።” “አይዞህ። አንተ ግን ትፈራለህ?” “ምን መገረፍ?” “አይ
እንዲው የምትፈራው ነገር የለም?” “የለም። አባቴ ወንድ ልጅ የሚሞተው የፈራ
እለት ነው ብሎኛል። አልፈራም!” “ታድለህ! እኔ እንዳንተ ባልፈራ ናቲን እቀጠቅጠው
ነበር” “ምን አረገሽ?” “ቅድም ትምህርት ቤት ፓስቲ ልገዛ ስል ‘የሸሌ ልጅ’ ብሎ
አስለቀሰኝ” ዞሬ አየዋት። አሁን እያለቀሰች ነው። አሳዘነችኝ። ማሰብ ጀመርኩ. .
.ትላንት ማታ አምሽቼ ነው ቤት የገባውት. . .እናቴ እስኪያዞረኝ ድረስ ከወገረችኝ
በኋላ አላለቅስ ስላት ቆይ አባትህ ይምጣ ዋጋህን ባላሰጥህ ብላኛለች. . .እሷ ደሞ
አትረሳም. . .ዛሬ የግድ እገረፋለው። ኪሴ ገባው ፤ ቅድም ጋሽ ተካበ ለፓስቲ ብሎ
የሰጠኝ 50 ሳንቲም አለች። አባቴ ቤት ቢቆይ ሁለት ወይ ሶስት ሰዓት ነው ያውም
ሁለቱን ሰዓት እኔን ሲደበድብ እና ሲመክር ነው የሚቆየው። የማታ ፊልም 10
ሰዓት ይጀምራል ቦታ ሳይያዝ ልሂድ። ትንሿን ሜዳ አቋርጬ መሄድ ጀመርኩ። ናቲ
ሰላምን አቅፎ እንደ ባል እና ሚስት ይጨፍራሉ። ብልጭ አለብኝ. . .ስቤ አላቀኳቸው
እና ከዚህ እስከ ኤርትራ የተሰማ ቴስታ ገባውለት. . . ወደቀ...እላዩ ላይ ቁጭ ብዬ
ወገርኩት። ታላቅ ወንድሜ ተሸክሞ አነሳኝ...ተናዷል “ምናባህ ሆነሀል?” እያለ
ይገፈታትረኝ ገባ በዚህ መሀል ነው ያየውት፤ ሮዛ ስትስቅ ለመጀመሪያ ጊዜ ስትስቅ
አየው። ደስ አለኝ። እንደልማዱ የሰፈር ሰው ወጣ ገሚሱ ‘እንደው አረ ይሄ ልጅ’ ይላል
ሌላው ‘ነገር ካልፈለጉት ምንም አያረግም’ ይላል ናቲ አፍንጫው በጨርቅ ተይዞለት
ለምስራቅ አፍሪካ በሙሉ የሚሰማ ተስረቅራቂ ለቅሶ ያለቅሳል እናቱ ፅጌ ጭንቅላቷን
ይዛ ታየኛለች። ወንድሜ እንደ ሌባ አንገቴን ይዞኝ ቆሟል። ይሄኔ ነው መስማት
የምልፈልገውን ድምፅ የሰማሁት። “ምን ሆኖ ነው?” አለ ያ ድምፅ “ጎሽ ዶክተር
መጣህ እስቲ እየው” አለች አንዷ. . .ዶክተር ዝቅ ብሎ ናቲን እያየ ጥያቄውን ደገመ
ፅጌ “ያንተ ልጅ ነዋ ሰይጣኑ ተነስቶበት” ዞሮ አየኝ። የሚገለኝ ነው የሚመስለው።
ያው ዛሬ መሞቴ ነው! ወንድሜን አየውት። ደስ ብሎታል። እኔ ልገደል ስለሆነ ይሁን
አባቱን ስላየ አልገባኝም። እጁን ላስለቅቅ ሞከርኩ ጭራሽ አጠነከረው። ተው የሚል
አስትያየት አየውት። ወይ ፍንክች አለ። አንድ እርምጃ ወደኃላ ተራመድኩና አንገቱን
ይዤ ያቺን ከዚህ እስከ ኤርትራ የምትሰማ ቴስታ አፍንጫው ላይ አቅምሼው ሲለቀኝ
እትም-14 ነሐሴ| 2012
39
እየተንገዳገድኩ ወደ አስፓልት ሮጥኩ። ደግነቱ ወዲያው መንገዳገድ አቆምኩ። ሙሉ
የሰፈር ልጅ ከኋላ ይከተለኛል። መሀል አስፓልት ላይ ስሮጥ ፒክ አፕ መኪና በጎኔ
ሲያልፍ ተንጠላጠልኩ። አመለጥኩ! መኪናው ላይ ሆኜ ተስፋ ሲቆርጡ አየኋቸው።
ደስ አለኝ። ማሰብ ጀመርኩ. . .ፍቅር ይዞኛል ማለት ነው? ፊልም ላይ እንዳሉት
ሰዎች? መልሱ አስፈራኝ፤ ልጅ ፍቅር አይዘውም። ውስጤ ግን አውቆታል. . . ሳቅሁ!
በደንብ ሳቅሁ. . .

እትም-14 ነሐሴ| 2012


40

ትምህርታዊ ጉዞ ወደ ምድር
ቢንያም
ዛሬ በ ፕላኔት G-369 ላይ የሚገኘው svora highschool ጉዞ አዘጋጅተው የ
ዘጠነኛ ክፍል ተማሪዎቻቸውን በህዋ ላይ በማንሸራሸር የሚያስጎበኙበት ቀን
ነው። ተማሪዎቹም ጓጉተዋል። መሬት ላይ የሚኖሩ ሠው ስለሚባሉ ነገሮች ብዙ
ሰምተዋል። ብዙ ተረትም እየሰሙ አድገዋል ቀርበው ግን አይተው አያውቁም ነበር።
ስለዚህ የዛሬዋን ቀን በጉጉት ሲጠብቋት ነበር። ሁሉም በጠዋት ነበር ይዟቸው ወደ
ህዋ በሚበረው የህዋ መርከብ ጋር የተገናኙት። ጉብኝታቸውም በመምህር ጋንቮር
እና በመምህርት ሊቪያር የተዘጋጀ ስለነበር ሁሉም ተማሪዎች ወደ ህዋው መርከብ
መግባታቸውን ካረጋገጡ በኋላ በሩን ጥርቅም አድርገው ዘጉት።
“እሺ ተማሪዎች እንዴት አደራችሁ። ዛሬ እንግዲህ በህዋ ላይ ዞር ዞር እያልን ያሉትን
ፕላኔቶች እና እላያቸው ላይ የሚኖሩትን ፍጡራን እንጎበኛለን።” አላቸው መምህር
ጋንቮር
” መምህርት ሊቪያር የምትጨምሪው ነገር ይኖራል?”
” አዎ። ያው እንደሚታወቀው ጉዟችን ትንሽ ራቅ ስለሚል ሁሉንም ማየት አንችልም
ግን በእናንተ ምርጫ አንዱን ፕላኔት በደንብ እናያለን። ስለዚህ ተማሪዎች አሁን
ፕላኔት ምረጡ።”
ተማሪዎቹም በአንድ ድምፅ ‘መሬት’ አሉ።
መምህርት ሊቪያርም ፈገግ ብላ
” በጣም ጥሩ። ጉዞ ወደ መሬት። ሁላችሁም ቀበቷችሁን በደንብ እሰሩ። እኛ ተነሱ
እስከምንላችሁ ድረስ ቁጭ በሉ።እሺ። ጥሩ። እንሂድ በሉ።” አለችና ጉዟቸውን
ጀመሩ። ወደ መሬትም በተጠጉ ጊዜ የህዋ መርከቧን አቁመው መምህራኖቹ ገለፃ
ያደርጉ ጀመር
“እንግዲህ ተማሪዎች ይህ የምትመለከቱት ትልቅ ሰማያዊ የድንጋይ ኳስ
የሚመስለው ፕላኔት መሬት ይባላል። ከፀሐይ በሶስተኛ ደረጃ ላይ የሚገኝ ፕላኔት
ሲሆን በውስጡም ሠው የተባሉ ትናንሽ ፍጡራን ይኖሩበታል። መልካቸውም ትንሽ
ያስፈራል። እንደኛ ቆንጆ የሚባሉ አይደለም። ኩራታቸው ግን ከቁመታቸው እና
ከእውቀታቸው በላይ ነው። በህይወታቸው የሚገርሙ ህጎችና የአኗኗር ዘዴ አላቸው
። ድሮ ድሮ በቁጥር ብዙም አልነበሩም። አሁን ግን በጣም በዝተዋል።የያዘቻቸው
ምድር ከበቂ በላይ ብትሆንም እነሱ ግን ተደራርበው ተጣበው መኖርን ይመርጣሉ።
ባለቻቸው ትንሽ የእውቀት ብናኝም ይኩራራሉ። ከሙሉ ህዋው ውስጥ ህይወት
ያለን እኛ ብቻ ነን ብለውም ያስባሉ።”
” ለምንድነው እንደዛ የሚያስቡት?” ጠየቀች አንዷ ተማሪ
” ትንሽ ወደ ህዋ ተጉዘው ጓሮ እና ዙሪያቸውን አየት አየት አድርገው ሌላ እነሱን
የሚመስል ነገር ስላጡ በቃ እኛ ብቻ ነን ብለው ያስባሉ። ብዙም አልራቁም። ያን
ያህል የሚያስጉዝ እውቀት ላይ አልደረሱም። ባገኙትም ሌላ ፕላኔት ላይ ሁሉ ለነሱ
እትም-14 ነሐሴ| 2012
41
የሚስማማ መሆኑን እና አለመሆኑን ያጣራሉ።”
” ለምን? እዛም ሊኖሩ አስበው ነው?” ጠየቀ ሌላ ተማሪ
” አዎ። ያሉበት ፕላኔት እየሞተች ነው ብለው ስለሚያስቡ አብረን አንሞትም
በማለት ሌላ መኖሪያ እየፈለጉ ነው።” አለች መምህርት ሊቪያር
” ፕላኔታቸው ለምንድነው የምትሞተው?” የማያልቀው የተማሪ ጥያቄ ይዘንባል
” ራሳቸው በአግባቡ ስላልያዟት ነው። የሚገሏት ራሳቸው ናቸው። በምድር ላይ
የሚገኙት የሚያስቡ ፍጡራን እነሱ ብቻ ቢሆኑም እርስ በርስ ግን አይስማሙም።
በዚህች ትንሽ ፕላኔታቸው ውስጥ ብዙ መከፋፈሎችን ለራሳቸው አዘጋጅተዋል።
በምናባቸው የፈጠሩት ድንበር የሚባል ሐሳባዊ መስመር ስላላቸው በሐገር
ይከፋፈላሉ። በቋንቋ ፣ በሰፈር ፣ ባላቸው ብር መጠን ፣ በፆታ ፣ በሀይማኖት ፣
በሁሉም ነገር እርስ በርስ ተከፋፍለው የሚጣሉበትን ሜዳ በራሳቸው አስፍተዋል።
ሌላው ቀርቶ በቆዳቸው ቀለም ይከፋፈላሉ።”
ተማሪዎቹም ሳቃቸውን ለቀቁት “ማለት?” አለ አንዱ ተማሪ
“ማለትማ የአንዱ ቀለም ነጭ ከሆነ የአንዱ ደግሞ ጥቁር ከሆነ በቃ ይከፋፈላሉ –
ጠላት ይሆናሉ። ” አላቸው መምህር ጋንቮር አብሯቸው እየሳቀ
“ከነሱም ብሶ ደግሞ በቀለማቸው ይጣላሉ ለራሳቸው እኮ ምን እንደሚመስሉ
አላወቁ” ብላ መምህርት ሊቪያርም ሳቀች
“እኛ ለምን ቀርበን አናናግራቸውም ግን?” አለ ፊት ለፊት የተቀመጠው ተማሪ
” ለጎረቤቶቻቸው ያልተመለሱ ከሌላ ፕላኔት የመጣውን እንዴት አድርገው
ይምሩታል። ገና ለመናገር አፋችንን ሳንከፍት ነው ግራ ቀኝ ብለው የሚገሉን። ዝግጁ
አይደሉም። መጀመሪያ የራሳቸውን ችግሮች ከፈቱ በኋላ እኛም ቀርበን ለማናገር
እንሞክራለን። እስከዛ ግን በሩቁ ነው የሚያዋጣን። እንደዚህ ስላችሁ ግን ጥላቻ
ብቻ የተሞሉ ናቸው ማለቴ አይደለም። ስለሚፈሩ ነው። ከነሱ የተለየ ነገር ይፈራሉ።
ግን ጥሩ ነገር ይፈልጋሉ። የሚያደርጉት ነገር ሁሉ ጥሩ ነገርን ፍለጋ ነው። የተሻለ
ለማግኘት ብለው ሲሮጡ ነው ብዙ ነገር የሚደፉት። በቴክኖሎጂ ቢያድጉም ግን
ቴክኖሎጂ ላይ ቀርተዋል። ነገሮችን በመስራት ተራቀዋል። ራሳቸው ላይ መስራት
ላይ ግን ወደ ኋላ ቀርተዋል። እንደውም ከነሱ እንሻላለን ብለው ከሚያስቡት
ከመጀመሪያዎቹ ሰዎች ይልቅ የአሁኖቹ ከቴክኖሎጂው ውጪ ወደ ኋላ የቀሩ
ናቸው። ወደ ውጪ መስራት ላይ ጎበዝ ናቸው። ወደ ውስጥ መስራት ላይ ግን ብዙ
ይቀራቸዋል።” አለ መምህር ጋንቮር
” እሺ ለመዋለድ እንዴት ነው የሚጠራሩት? ማለት ወንዱ ወይም ሴቷ ምን አይነት
ድምፅ ነው የሚያወጡት?” ብሎ አንድ ተማሪ ጠየቀ። ሌሎቹ በእፍረት ሳቁ።
” አይ እንደሱ አይደለም ተማሪዎች። በእርግጥ ለመዋለድ ሲፈልጉ ድምፅ ባያወጡም
የራሳቸው የሆነ መንገድ አላቸው። በፊት በፊት ፈላጊው ወደፈለገው ሰው ይሄድና
ራሱን ያስተዋውቅና የሚፈልገውን ሳይናገር ግን በጊዜ ሂደት እየገለጠ ሲሄድ
ተፈላጊውም ከፈለገ ያው ይስማማሉ ማለት ነው። አሁን ያሉት ደግሞ ከየትኛውም
ትውልድ በበለጠ ከቴክኖሎጂ ጋር ጥብቅ ቁርኝት ስላላቸው ሁሉን ነገር የሚያደርጉት
እጃቸው ላይ ባለች ሞባይል ብለው በሚጠሯት የቴክኖሎጂ ውጤት ነው። በሞባይሉ
ተጠቅመው ወይ በፊደላት ይፃፃፋሉ ወይ ደግሞ በድምፃቸው የፈለጉትን
እትም-14 ነሐሴ| 2012
42
ያስተላልፋሉ ማለት ነው። ግን ደግሞ ኩራት ስላለባቸው የነሱ የመጠራራት
ጨዋታ የሚያመዝነው ማን የበለጠ ያልፈለገ መስሏል ላይ ነው። ግራ ያጋባል
አይደል? እንዴት መሰላችሁ አሁን አንድ የሰው ፍጡር ሌላን የሰው ፍጡር ሲፈልግ
በተቻለው መጠን ያልፈለገ ለመምሰል ነው የሚጥረው።”
“እንዴ እየፈለገ ለምንድነው ያልፈለገ የሚመስለው? ተቃራኒውን?” አሉ ተማሪዎቹ
” አንዳንዴ ግራ የሚገቡ ፍጡራን ናቸው። ያላቸው ኩራት ዘላለም የሚኖሩ ያህል
ነው። ሁሉን ነገር ሳያዩ በፊት የሚያልፉ አይመስላቸውም። አጠገባቸው እንኳን
ሌላው ሲሞት እያዩ በዛው ኩራታቸው ይቀጥላሉ። ጊዜ አለን ብለው ያስባሉ።
ስለዚህ ለመኖር ጊዜን ይጠብቃሉ። ግን ለመኖር መጠበቅ ማለት ለመሞት መጠበቅ
ማለትም እንደሆነ አያስተውሉትም። የገዛ አእምሯቸው ያታልላቸዋል። የገዛ
አእምሯቸው ገዝቷቸዋል። አብዛኛዎቹ ራሳቸውን ይህ የድንጋይ ኳስ ላይ ስላገኙት
ብቻ ነው የሚኖሩት እንጂ ለምን ብለውም መጠየቅ አይፈልጉም። ለምን ቢሉም
መልስ የለውም። ግን መጠየቅ አለባቸው። ራሳቸው ጠይቀው ራሳቸው መመለስ
መቻል እንደሚችሉም ያስተዋሉት አይስልም። አሉ ደግሞ ከመሀላቸው የነቁ የበቁ።
ግን እነሱ ተሸፍነዋል። ብዙ ትናንሽ ነገር የሸፈናቸው ብዙ ታላላቆችም አሏቸው። ግን
አይሰሟቸውም። የሚሰሙት የጮኸውን ነው። የሚያስተጋቡትም የጮኸውን ነው።
በአሁን ሰዓት የሚጮኸው ደግሞ ከሰውኛ አፈጣጠራቸው ውስጥ መበላሸታቸውን
ወይም መንገድ መሳታቸውን በግልፅ የሚያሳየውን ነው። ለነገሩ እኛም ከውጪ
ስለምናያቸው እንጂ ግራ ተጋብተዋል እነሱም። ምንም ነገር ከውጪ ሲታይ ይቀላል
ልጆች። እነሱም ልክ እንዳልሆኑ ሲያውቁ ጊዜው ይረፍዳል። ልክ ሊሞቱ ሲሉ መኖር
እንዳልጀመሩ ይገለጥላቸዋል ያኔ ያልፋሉ። ህይወት ግራ መጋባት ነው – ሞት ሁሉን
ያጠራል።”
“መምህር እሱ ምን ማለት ነው? ሞት እንዴት ነው ህይወት የሚያጠራው?” አለች
አንዷ ግራ የተጋባች ተማሪ። መምህር ሊቪያርም ብትሆን መልሱን ማወቅ ፈልጋ
ስለነበር ትኩረቷን ወደ መምህር ጋንቮር አዞረች።
” ሞት ህይወትን የሚያጠራበት መንገድ እንዴት መሰላችሁ። አሁን ለምሳሌ
ከአምስት ደቂቃ በኋላ ትሞታላችሁ ይባል። ምሳሌ ነው። ምን ሊያስጨንቃችሁ
ይችላል? የቤት ስራ? የለበሳችሁት ልብስ ንፁህ አለመሆኑ? ሰው ስለ እናንተ
ምን እንደሚያስብ? ወይስ ስለ ወላጆቻችሁ? ስለ ወንድም እህቶቻችሁ?
ስለምትወዷቸው ሰዎች? ስለምን ታስባላችሁ? ሞት ሲመጣ ይዞት የሚመጣው
መጥረጊያ አለ። እሱ መጥረጊያ ደግሞ ህይወታችሁ ውስጥ ተሰግስገው ህይወትን
ከባድ የሚያስመስሏት ነገሮችን ጠራርጎ የማስወጣት ሐይል አለው። ስለዚህ ሞት
ህይወትን የማፅዳት አቅም አለው ማለት የማይረቡ እና እግሮቻችሁ ስር የተተበተቡ
ትናንሽ መሰናክሎችን አልፋችሁ ትኩረታችሁ እና ጊዜያችሁ መሆን ወዳለበት እና
ወደሚገባው እንድታዞሩ እድሉን ይሰጣችኋል። ሞት ነፃ ያወጣል። ለዛም ነው
ህይወት ግራ መጋባት ነው – ሞት ሁሉን ያጠራል ማለቴ። ግን ደግሞ ህይወታችሁን
ለማጥራት እስከ ሞት ድረስ መጠበቅ የለባችሁም። አመጣጡ አይታወቅምና
እድሉንም ላይሰጣችሁ ይችላል። ግን እንደሚሞት ሰው ስትኖሩ አኗኗራችሁ ወደ
እውነት የተጠጋ ይሆናል። የሰው ልጆችም ይሄ ቢገባቸው ኑሯቸው ይለወጣል።” ብሎ
እትም-14 ነሐሴ| 2012
43
መምህር ጋንቮር በረጅሙ ተነፈሰ
“እሺ ሌላ ጥያቄ። ያለው አለ?” አለች መምህርት ሊቪያር ሰዓቷን እያየች
” ቀርበን አናያቸውም?” አለች አንዷ ተማሪ
” እሱን እንኳን ማድረግ አንችልም። በአሁን ሰዓት ግራ የተጋቡበት ጊዜ ስለሆነ እኛም
ተጨማሪ ግርታን መፍጠር ስለማንፈልግ ከዚሁ ሆነን ቤታቸውን ብቻ እናያለን።
ስለነሱ አውርተን መጨረስ አንችልም ግን የቻልነውን ያህል ነካ ነካ ለማድረግ ነው
የሞከርነው። ምን እንደሚመስሉ ደግሞ በየመፅሐፍቶቻችሁ ላይ ምስላቸው እና
አፈጣጠራቸው ስለተቀመጠላችሁ እሱን ማንበብ ትችላላችሁ። ሰዓቱም እየሄደ
ስለሆነ እኛም መመለስ አለብን። ግን የመጨረሻ ልላችሁ የምፈልገው ነገር ምንድነው
እነዚህ ሰው የተባሉ ፍጡራን ተስማምተው አንድ የሆኑ ቀን – ወደ ውጪ ሳይሆን
ወደ ውስጣቸው የተመለከቱ ቀን በዚህ ማለቂያ በሌለው ህዋ ውስጥ ካሉት ፍጡራን
ሁሉ የበለጡ ሓያላን ይሆናሉ። በቴክኖሎጂ ብቻም ሳይሆን በ ሁሉም አቅጣጫ
ይበለፅጋሉ። ያኔ እውነተኛ ማንነታቸው ይገለጣል። ይቺን ቤታቸውን አቃጥለው
አመድ ሳያደርጓት በፊት እና እርስ በርስ ሳይተላለቁ በፊት ሁሉም አንድ እንደሆኑ
ቢገባቸውና መሆን እና መድረስ የሚችሉበትን ጥግ የሚያሳያቸውን ከነሱ መሐል
የሚገኙትን መከተል ቢችሉ ብዙ ነገር ላይመለስ ከመበላሸቱ በፊት ሊያድኑት
ይችላሉ።” አለች መምህርት ሊቪያር
“በሉ አሁን መመለሻ ሰዓታችን ደርሷል። ሌላ ጊዜ ሰፋ ያለ እና ምናልባትም ከሆነልን
እነሱ እንዳያዩን አድርገን ከመሐከላቸው ሆነን በቅርበት ስለ ሰው ልጆች እናጠናለን።
እሺ ተማሪዎች? በሉ አሁን ቀበቷችሁን እሰሩ” መምህር ጋንቮር ተኔገረና እሱም ቁጭ
ብሎ ቀበቶውን አሰረ። መንቀሳቀስ ሲጀምሩ ግን ተማሪዎቹ አዘኔታ ውስጥ ነበሩ።
“ሲያሳዝኑ ግን ” አለች አንዷ ተማሪ
ሁሉም ሐሳቧን ተጋሯት። ዞር ብለውም ወደ ምድር እያዩ ከንፈራቸውን መጠጡ።
ሲያሳዝኑ።

እትም-14 ነሐሴ| 2012


44

እትም-14 ነሐሴ| 2012

Das könnte Ihnen auch gefallen